>

የለማና አብይ  አብዮት ተቀልብሷል!!! [ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም]

የለማንና አብይ]  አብዮት ተቀልብሷል!!!
  ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
“…..ነገሩ በንግግር ደረጃ: ለማ መገርሳንም ስሰማ (በተለይ ለማ መገርሳ!) በዘር ፖለቲካ ላይ: በጣም ጫን ብሎ: ተቃውሞ ድምፅ ያሰማ ይመስለኛል–እኔ እንደሰማሁት:: አብይ እንደሱ [እንደ ለማ] ያህል ባይሰማኝም: እሱም አንድ ላይ ናቸው ያሉት::
ነገር ግን ይህ ዲስኩር ነው:: በዲስኩር ደረጃ ግሩም ናቸው:: በተግባር ደረጃ ግን: የሚሰራው: የምናየው ሹመቱንም: ምኑንም ስንመለከት: የምንገንዘበው እልተለውጥንም:: ያው ነው:: መንግዳችን ያው ነው:: የዘር መንገድ ነው የያዝነው:: ላለፉት 40 ዓመት ከሄድንባቸው ጉዞ: እንዲያው መንጥቆ የሚያወጣን: ደረጃ ላይ ደርስን ስንል: ቀስ ቀስ እያለ እንደገና የሚደፍቀን ሁኔታ ውስጥ እየገባን ነው:: እናም አሳዛኝ ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ ይመስለኛል::
የእነ ለማና አብይ አብዮት እተቀለበሰ ነው ለማለት ይቻላል [ይመስለኛል]:: ደግሞ ሌላ ስው ቀልብሶባችው አይደለም:: እራሳቸው [ለማ+ አብይ] እየቀለብሱት ነው:: “
Filed in: Amharic