>

"ህገ መንግስቱ" በህገ-ኢትዮጲያ ይለወጥ!!! (ኤፍሬም ለገሰ)

“ህገ መንግስቱ” በህገ-ኢትዮጲያ ይለወጥ!!!
ኤፍሬም ለገሰ
ህገ-ኢትዮጲያ ይገባኛል፣ የኛ፣ ኬኛ፣ ልዩ ጥቅም፣ ፊንፊኔ-አዲሰ አበባ  ወዘተ የጎጥ አስተሳሰብ ብሄርተኞች  ታሪክን እያዛቡ ህዝብን በመሰሪ ሴራዎች ወደ ግለሰቦች ጥቅምና ጥላቻ በመውሰድ ዓላማቸውን እንዳያሳኩ በህግ ይደነግጋል!!!
በሃሰትና በመሰሪነት ላይ የተመሰረተው ትላንት ህወሃት ያመጣብን የጎጥ ፖለቲካ ዛሬም በሌላ መልኩ የአገራችንን አንድነት ለማጥፋትና ህዝባችንን ለማመስ እየተሰራ ያለው ሴራ ችግሩ የሚጀምረው በጉልበት የህወሃት- ኢህአድግ ገዢ ቡድን የጫነብን የኢፌዴሪ “ህገ መንግስት”ና እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የተሰገሰጉት የህወሃት ስራ አስፈፃሚዎች እስካሁን በስልጣን ላይ መሆናቸው ነው።  ለዚህ መፍትሄ የሚሆን በመላው የኢትዮጲያ ህዝብ ተጠንቶ ህዝበ ውሳኔ ተሰጥቶበት የአገራችንና የህዝባችንን አንድነት ማዳን የሚያስችለው ህገ-ኢትዮጲያ ነው። ህገ-ኢትዮጲያ በተለያዩ ባለሙያዎች እህት ወንድሞቻችን ለዓመታት ሲጠናና ሲሰራ የቆየ ነው።
ህገ-ኢትዮጲያ ከጎጥ ፖለቲካና ከሶሻል ኢንጂነሪንግ ነፃ የሆነ አብሮነትን ፍቅርን አንድነትን ሰላምን የሰውን እኩልነት መከባበርን የሚያበረታታ ነው። የአስተዳደሩን  ክፍፍል አንቀፅ እንደ ምሳሌ ብንጠቅሰው  በጥንት ጊዜ የነበረን የክፍለ ሃገር አስተዳደራዊ ክፍፍል ወደ ሬዴሬሽን በመቀየር ሁሉም ኢትዮጲያዊ በአገሩ ጉዳይና ስራ ላይ  በብቃቱ እንጂ በጎሳው እንዳይፈረጅና አብሮነትን ዛሬም እንደጥንቱ  ፍቅርን በማስፈን  አገርን ማዳን ይቻላል።
ህገ-ኢትዮጲያ ይገባኛል፣ የኛ፣ ኬኛ፣ ልዩ ጥቅም፣ ፊንፊኔ-አዲሰ አበባ  ወዘተ የጎጥ አስተሳሰብ ብሄርተኞች  ታሪክን እያዛቡ ህዝብን በመሰሪ ሴራዎች ወደ ግለሰቦች ጥቅምና ጥላቻ በመውሰድ ዓላማቸውን እንዳያሳኩ በህግ ይደነግጋል።
http://ethioprovinces.org/constitution/ ሊንክ ላይ በመግባት ህገ-ኢትዮጲያን በአማርኛ ወይም በኢንግሊዘኛ አውርደው ሊረዱትና አስተያየቶውን መስጠት ይችላሉ በርከት ያሉ መረጃዎችንም ያገኛሉ።
የህወሃት የጎጥ ፖለቲካ ለ27 ዓመታት በአንድነታችን በአብሮነት ሰላማችን ላይ በሃሰት በመሰሪና በፅንፈኛ ተግባሩ የመረዘን ዛሬም  እንዳይቀጥልና የአገራችንና የህዝባችንን አንድነትና ሰላም ለማዳን እንስራ።
1–እንደ መፍትሄ “ህገ መንግስቱ” በህገ-ኢትዮጲያ ይለወጥ
2–በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ ህወሃት የሰገሰጋቸው አስፈፃሚዎቹ ከቦታው በአስቸኳይ ይነሱ ( ለውጡ ወደታች ይድረስ)።
3–ፖለቲከኞቻችን በሁለት ምላስ አታምታቱን ህዝባችን የሚፈልገው በሰላምና በፍቅር በመከባበር በመተባበር በመረዳዳት ዛሬም እንደጥንቱ አብሮ መኖርን ነው።
ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት ይብዛልን!!!
ኢትዮጲያ ሃዱርሲቱ!!
ኢትዮጲያ ከጎጥ ፖለቲካው ትቅደም!!!
Filed in: Amharic