>
5:13 pm - Monday April 19, 3683

የፋሺዝም ፖለቲካችሁን አቁሙ!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

የፋሺዝም ፖለቲካችሁን አቁሙ!!!
ኤርሚያስ ለገሰ
 
* Tom Gardner is in my mind!
   ባለፈው ሁለት ሳምንት የውጭ ሚዲያ ወኪል የሆነው ቶም ጋርድነር በኦሮሚያ ጉጂ ዞን ካሉት 200 ቀበሌዎች 197 ያህሉ ምክርቤቶች በኦነግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን በቲውተር ገፁ ዘገበ። እኛም ሁለት ሳምንት ጠብቀን መንግስት ( በተለይ ኦዴፓ) ለውጥ መኖር እና አለመኖሩን ምላሽ ይስጥበት ብለን ጠየቅን።
ትላንት የካቲት 25/2011ዓ•ም• መንግስት በመከላከያ የጦር አዛዦች በኩል ምላሽ ሰጥቷል። የጦር አዛዦቹ ከፍተኛ ዝግጅት በተደረገበት ከ17 በላይ የደፈጣ ውጊያ ከአስር ወረዳዎች 8ቱን ከኦነግ ማስለቀቃቸውን ነግረውናል። በስምንቱ ወረዳዎች ኦነግ መደምሰሱን፣ መመሰረኩና  ፈርጥጦ እንደጠፋ በወታደራዊ ኩራት ገልፀዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም በአካባቢው ወጥቶ መግባት የማይቻልበት፣ የሰው ልጅ የሚታፈንበት፣ አሰቃቂ ወንጀል የሚፈፀምበት ሁኔታ በመከላከያ ሰራዊቱ ምክንያት ቀንሷል ብለዋል።
በሽምግልና ሳይሆን ሱሪው ዝቅ ተደርጐ ሲገረፍ “ነጭ ባንዲራ” እያውለበለበ ወደ ካምፕ የገባውን ኦነግ ለጊዜው እንተውና ሌላ መሰረታዊ ጥያቄ እናንሳ። ከትላንትናው የኢቲቪ ዘገባ እንደምንረዳው ከሆነ በምስራቅ ጉጂ ዞን ሁለት ወረዳዎች አሁንም በኦነግ ቁጥጥር ስር ናቸው። በሌላ አነጋገር በአማካይ 20 ቀበሌዎች ኦዴፓ አያስተዳድራቸውም። በህዝብም እናስላው ከተባለ ከ400ሺህ በላይ ህዝብ ህገወጥ በሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ይገኛል። እናም ኦዴፓ ለዚህ እና ተያያዥ ጉዳዬች ( እንዴት በዚህ አካባቢ ህዝብ ቆጠራ እንደሚካሄድ) ምላሽ ሊሰጥ ይገባል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አዲስአበቤ ማወቅ ያለበት የሽምግልናው ፊትአውራሪ ሆነው ዱብዱብ ሲሉ የነበሩት የፋሺዝም ፓለቲካ አራማጆች ስላልተሳካላቸው አጀንዳ ለማስቀየር ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን ነው። ለዚህም ፊትለፊታቸው ያገኙት “የኮንደሚኒየም ፓለቲካ” ሆኗል። ይህን መገንዘብ ያስፈልጋል። እነዚህ የፋሺስት ፓለቲካ አራማጆች ቀናቶች በተቆጠሩ ቁጥር ሽፍንፍናቸው ተገላልጦ እውነተኛ ገፅታቸው አግጦ እየታየ ነው። መቼም ከዚህ በኃላ አዴፓ ባህርዳር ጠርቶ ቀይ ጃኖ ያለብሳቸዋል ተብሎ አይጠበቅም። መቼም የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ምሁራን “የፓለቲካ ሳይንቲስትነት” ዲስኩር ከእነዚህ ሰዎች ለመስማት ወደ አዳራሽ አይመጡም። መቼም አዲስአበቤ ሱሪ ለብሶ እየሄደ እነዚህ ዘረኞች በመሃል ፒያሳ በነፃነት አይንጐማለሉም። አዲስአበቤ እንደ መስከረም አምስቱ የመከላከል እርምጃ ይወስዳል። ጊዜው ሲደርስ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ይሸጋገራል።
Filed in: Amharic