>

የሀገር ውስጥ ፖለቲካ እየተጋጋለ በሄደ ቁጥር እየጣሉ መዞር ዋጋ ያስከፍላል!!! (ሚኪ አምሀራ)

የሀገር ውስጥ ፖለቲካ እየተጋጋለ በሄደ ቁጥር እየጣሉ መዞር ዋጋ ያስከፍላል!!!
ሚኪ አምሀራ
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ በኤርትራ አድሮጎ ደቡብ ሱዳን አሁን ወደ ኬንያ ከሶማሌዉ ፐርዝደንት ጋር አመሩ የሚል ነገር እያየሁ ነወ፡፡ ዶ/ር አብይ በሁለት ምክንያት ይመስለኛል ይሄን ጉዞ የሚያደርገዉ፡፡
1). ግልጽ ተወዳዳሪ በሌለበት የኖቤል ሽልማት ላይ ዶ/ር አብይ ትልቅ ተስፋ አድርጓል፡፡ በእርግጥ በዚህ አጭር ጊዜ ዉስጥ ሽላመቱን ለመስጠት የሚቸገሩ ቢሆንም ነገር ግን ለሽልማት የታጩት ግለሰቦች ያን ያህል የሚባሉ ናቸዉ፡፡ ይሄም  ምናልባትም ወደ ድርጅቶች እንዲዞሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሰሞኑን በለጋጠፎ ቤት መፍረስ ላይ የአለም ታዋቂ ጋዜጦች የዘገቧቸዉ ዘገባወች የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ስም የሚያጠፉ እና በእጅጉ ዉድድሩን የሚጎዱ ናቸዉ፡፡ ይሄን ነገር ለመሸፋፈን ወይም ስሙን ለማደስ ይመስላል back to back ጉዞ እያደረገ ያለዉ፡፡ ሲጀመር እንዲህ አይነት በመሪዎች ደረጃ የሚደረጉ ድርድሮች መጀመሪያ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸዉ አማካኝነት ወደ ሚያስማማ ሁኔታ ሲቃረቡ እንጅ በጨበጣ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ሰሞኑን የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመደራደር ሄዶ ተዋርዶ በሚባልበት ሁኔታ ነዉ የተመለሰዉ፡፡ ተንታኞች አንዱ ድክመት ያሉት ቀድሞ ድርድር ያልተደረገበት እና በሌሎች ባለስልጣኖች አማካኝነት ስምምነት ሳይደረስ በመሄዱ ነዉ በሚል ነዉ፡፡
ለምሳሌ ዶ/ር አብይ ኢሳያስ አፈወርቂን ይዞ ሱዳን ካርቱም መገኘት ፈልጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢሳያስ አልፈለግም፡፡ ቀድሞ ለመስማማት የሚያስችሉ ስምምነቶች ካልተደረጉ በቀር ኪሳራ ነዉ፡፡የሱዳን ጉዞ መሰረዝ አንዱ ምክንያቱ ይሄዉ ነዉ፡፡
2. የሀገር ዉስጡ ፖለቲካ የመሸሽ  (avoidance) ወይም ደግሞ በዉጭዉ አለም በደንብ እዉቅናን አትርፎ ከዚህ እዉቅና ተነስቼ የዉስጡን እቆጣጠረዋለዉ፡፡ አለበለዚያም የዉስጥ ፖለቲካዉ በራሱ ጊዜ ይረግባል እና አቋም ይዤ ደጋፊየንም የማይደግፈኝንም ከማበሳጭ በራሱ መንገድ ይሂድ ነዉ (ይህ አደገኛ አካሄድ ነዉ). ዉስጥ ላይ እየተብላላ ያለዉን ፖለቲካ እንዲሁ ሻርታ እየዞሩ ማየት ዉጤቱ ምን እንደሚሆን የምናየዉ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አንድ ቀን ጉዞ አድርጎ የማይመለስበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡
ወጭዉም ቀላል አይደለም፡፡ አየር መንገዱ የሚያወጣዉ ወጭ፡፡ አብረዉት ለሚጓዙት የሚወጣዉ ወጭ፡፡ ብቻ በዚች ደሃ ሀገር ይሄን ያሀል ወጭ አሳዛኝ ነዉ፡፡ አስቡት አንድ አዉሮፕላን ከአስመራ ተነስቶ ጁባ ሁለት መሪወችን ብቻ ይዞ ሲጓዝ፡፡
ብቻ የሀገር ዉስጥ ፖለቲካ በሚጋጋልበት ወቅት እየጣሉ ዞር ማለት መፍትሄ አይሆንም፡፡
Filed in: Amharic