>
9:04 pm - Tuesday July 5, 2022

በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ራሱን የገደለው  ሕውሃት ማን እንዲገድለው ይሻል?ዋ!ሰበብ ነው። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ.. )

በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ራሱን የገደለው 

ሕውሃት ማን እንዲገድለው ይሻል?ዋ!ሰበብ ነው።

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመመንፈሳዊ
 
ለቀድሞ፡ሰዎች፡በሕልማቸው፡

መጪውን፡ዅሉ፡ገልጾላቸው፥

ያላዩት፡የለም፡ከኾነው፤

ዅሉ፡እንዳለሙት፡ነው።

—ooo–

ዓለምን፡ከሩቅ፡ለሚያያት፡

እጅግ፡ታምራለች፡ለንብረት፤

ውስጧ፡ተባይ፡ነው፡ወደ፡ማታ፡

ወከንቱ፡ቀሪቦታ።       አለቃ፡ተገኝ፡ታምሩ ፲፱፻፷፩፡ዓ.ም

 

         ህውሃት የዛሬ ሃያ ሰባት ዓመታት የመንግሥት ስልጣኑን ያዘ፤”እኔ እንደ ኢሠፓ መንግሥት አልገድልም፤አባላቱ የገበሬው ልጆች ናቸው”ብሎ ብዙ ተገዘቶ መሪዎቹም ከዩኒቨርስቲ የሸፈቱ ናቸው አለን።ከመጀመሪያው”ገዳዮች ናቸው”ያላቸውን ከያሉበት ለቃቀመ፣ራሱም አብሮ ሲገድል የነበረውን፣የኢሕአፓ ጅምላ መጠፋፋት ለመረጃነት እያስቆፈረ ራሱ ክየተቀበረበት አስወጥቶ፤እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ ብሎ ግፍ የተፈፀሙበትን ቦታዎች እያነፈነፈ ሬሳ አከማችቶ፣”የደርግ ሠይጣናዊ ተግባሮች”እያለ በየፈርጃቸው አስቀምጦ ሙዚየም ከፍቶ ለዓለም እና ለማያውቁት “ኑ ጉዳቸውን እዩልኝ”አለ፤የራሱን ሠይጣናዊ ጉድ ደብቆ።በምትኩም የኢትዮጵያ ሕዝብ:-አዲስ የሰላም እና መረጋጋት የዕድገት ምዕራፍ ተጀመረ ብለን ተሞኝተን ነበር፤ለካንስ ከእነዚያ አንዳንድ በሁለት ሹካ ከሚበሉት የደርግ ባለሥልጣናት ጀርባ ነው የተጣበቁት።

           {ብዙም አልቆየም ከራሳቸው የተንኮል ግድያ በታምር የተረፉ እና ያመለጡ፤መሪያቸው ወቸገል ዜናዊን አምርረው ሠይጣን እንደሆነና፤ተከታዮቹ ደግሞ አጋንንት እንደሆኑ እንደነገሩን፤በአይናችንም እያየን ውስጡም ኖርንበት።}ይሄን ሠይጣን አይደለም የሚፈፅመው ምክንያቱም ሠይጣን በጥቅም እየተገዛ ለሰውም ስለሚያገለግል፤ዲያብሎስ ብቻ ነው ብለን አመንን፤ሠይጣኑንም ሆነ ዲያቢሎሱን ዶግ-አመድ ለማድረግ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ትግል በፆምና በፀሎት ሱባዔ ተይዞ በስግደት እየተለጉ፣ሁለቱም ርኩስ መንፈሶች ፈርሰው(የአባ ዲያቢሎስና የወቸገል ዜናዊ ሬሳዎች)በጭፍራዎቻቸው ተሸኙ፤ታሪክ ነው ይቀመጥ።

   እናም ተስፋችን እንደተጠበቀው አልሆነም፤እንደውም ከኢሠፓ በከፋ የተረገምን እስኪመስለን ከውርደትም በላይ ተንቀንንና ተዋርደን፣ በአደባባይ የዓለም ሕዝብ እያየን ሰላሳ ኢትዮጵያውያንን አሳረድን።የሚያሳዝነው ሠላሳው መታረዳቸው ብቻ አይደለም፤”ያገባኛል”የሚል መንግሥት  ጠፍቶ በተጻራሪው”አርፋችሁ ተቀመጡ ገና ኢትዮጵያዊነታቸው አልተረጋገጠም”የሚል መንግሥት ነኝ ባይ ከአንድ ግለሰብ የመረጃ ዝቅጠት የገዳይ ቡድን ማየቱ ደም-ዕምባ የሚያስወጣ ክስተት አሳየን።ለካስ ሕገ-መንግሥቱ የዜጋን መብትና ግዴታን ይቅርና፤ሕልውናውንም ከግለሰብ ጀምሮ ጭርግድ አድርጎ በልቶታል!ይልቅስ በግፍ-ደም የተፃፈው የመንግሥት ሕግ፣ሕዝብ ያላፀደቀው የዘረኞች የዜሮው ውጤት ሕገ-መንግሥት ነው።

   የግፎቹ ዓይነቶች ደግሞ ተዘርዝረው አያልቁም፤ከፍናፍንታዊነቱ፣ቤተሰቦችን ከመበተኑ፣በዘር-አምክን መርፌ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ እናቶችን ማስወጋቱ፣ጀምሮ ከጅምላ ግድያው ጎን፣የሰዎችን ሬሳ በመሰወርና በየቤተ ክርስቲያኑ የቀብር ቦታዎች በጨለማ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ፣በፈሪነት  ከሚመነጩ ሺህ ተግባሮች ጥቂቶቹ፤በአደባባይ ሴትና ሕፃናትን ሳይቀር ባነጣጣሪ መሳሪያ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ጭንቅላትን ቦርቅሶ መግደል ናቸው።ከላይ የተዘረዘሩትን ወንጀሎች ጨምሮ የሕዝብን ገንዘብ በሚሊዮን መዘረፉ ሳያንሰን፣ወጥቶ ቤት መመለስ ትርጉም አጥቶ የሕዝብ ስጋት ትርጉም አጣ።ተራ የንብረት ዘረፋውማ፣ጭልፋና ዘነዘና ሳይቀር ከየፋብሪካዎቹ ጥፍጥሬን ጨምሮ መጅ እንኳ ሳያስቀሩ፤ክጎጃም፣ከአቃቂ፣ከድሬድዋ፣ ከጎንደር፤ከስንቱ የፋብሪካ፣መሳሪያዎቹን እያስነቀሉና ካቻቢቴና ጉጠት ሳይቀር እየሰረቁ በአደባባይ አጋዙ።

       ለሃያ ሰባት ዓመታት እነዚህን ተራ ወንጀሎች ሳይቀር ሲፈፅም የነበረን ቡድንም ሆነ የቡድኑን አባል ወንጀለኛ መሆኑን ደጋግመን ብንገልፅም፣በተግባር ግን ሳይወገዝ በዕርቀ-ጉባኤ ሥም በፓርቲነት ማውደሙን ቀጥሏል።ዕርቁ ዘግይቶ ጉባኤውም ሳይደረግ እስከዛሬ ድረስ እየትጓተተ ምንም አለመደረጉ ሳያንስ በወንጀለኛው አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ሹመቶች መፈንዳት ጀምረዋል፤እናም ከመቀልበሻዎቹ ምልክቶች አንዱ መረጃ ሹመት ነው፤የኢንጅነር ታከለ ኦማ’ን ሕገ-ወጥነት ዝም ብለን መሆኑ ነው። 

           ይህ እየታወቀ ለወንጀለኞች እንደአዲስ ሥልጣን መስጠት መጀመሩ የዶክተር ዐቢይ አህመድ ጅማሮ በአቶ ሕፃናትን በየትምህርት ቤቱ እየተሹለከለከ በፈንጂ ሲገድል የነበረ፦አቶ አስመላሽ አያበቃምና:-መጀመሩ ወደክህደት ጉዞ እንዳያመራን ሊ.ገ.ታ ይገባዋል፤አለበለዚያ ሕገ-መንግሥት የተባለው ቢኖርም በአንፃራዊነት ሕገ-ሕዝቡን አሁን በውሳኔ-ህዝብ ልናፀድቅ ይገባናል።እስከመቼ ድረስ፣መንግሥት በሌለ ሕገመንግሥት እያማካኘ የሕዝቡን ነጻነት በመሸራረፍ እንደልቡ በመፈንጨት የፈለገውን ሲሾም እና ሲሽር ሕዝቡ ተመልካች ብቻ ይሆናል? አለበለዚያ በሕገ-ሕዝቡ አናቱን እንቀጠቅጠዋለን፤ ይጠልዝማል።ለነገሩማ፦ዶክተር ዐቢይ አህመድ የጊንጦችን ራስ እንደረገጠልን ተሰምቶን፤ወደ ትንሳኤ አውድማ ተሰባሰብን፤እርሱም በልቡ እግር ከሕዝቡ ጋር ዓለም ተጉዞ በያንዳንዳችን ህሊና ውስጥ ሰርፆ በትዕግስት የጥላቻችንን ስሜት በፍቅር እሳት አቃጠለ ብለን እንጂ፤ለኢሃድግ ፍጆታ ብለን እንዳልሆነ ራሱ ሕውሃት ያውቀዋል።ዶክተር አቢይ አህመድ ለምን እኛ ኢሃድጎች ይሉናል?ለመሆኑ ሕውሃት ስንት ጊዜ ራሱን እስኪገድል ድረስ ነው በኢትዮጵያ ሕዝብ ሥም አሁን ያለው መንግሥት ጤናማ የሆነ ርምጃ የሚወስደው?የነገም ምርጫችን ዐቢይን ብቻ ይሆናል እንጂ፤እንደተጠቀለለ መርዝ ከውስጡ ህውሃት የሚሉትን የወንጀለኛ ቡድን ይዞ ከሆነ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ”ለፖለቲካ ጌም” ስሌትዎ “ቼክ ሜት”ከመባልዎት በፊት ሁለቴ ሊያስቡ ይገባዎታል።

           ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ሆይ፦ልብ ይበሉ ራሱን የገደለውን ሕውሃት እርስዎ ሊገድሉት አይቻልዎትም፤ሰበብ ሊያደርጉብዎት ይሆን እንጅ ሕውሃት ራሱን የገደለው ያኔ የምትመሩበትን ርዕዮት-ዓለም ከሦስታችሁ ድርጅቶች ተለይቶ  የወሰነ ጊዜ ነው።ኢሃድግ የሚባል የለም፤ሦስታችሁ”እኛ የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ርዕዮት ከእንግዲህ አንከተልም”ብላችሁ ስትወስኑ፤ያኔ ነው ያበቃው።ሕውሃት ግን ሊያስገ ድዳችሁም ታገለ፤አሸነፋችሁት”ልቀቅ እኛን አትጎትተን፤ሃያ ሰባት ዓመታት ያልሰራ ርዕዮት ዓለም ውስጥ እንደገና ወደ ማጥ አንገባም”ብላችሁ ቆራጥ ርምጃ በመውሰዳችሁ ነው።”የኔን ጥፋት አልደገሙም”ብሎ የክህደት ታቤላ ለጠፈባችሁ፤እናንተ ግን፣በዲሞክራሲ ገርፋችሁት ራቁቱን አስቀራችሁት እናም ሕዝቡ ከጎናችሁ በመቆሙ ከእንግዲህ ወደፊትም ለሰው ልጆች ነፃነት፣ፍቅር እና ሠላም ለመታገል ቆራጥ መሆን አለባችሁ። 

 ይሁን እንጂ፣ሕውሃት ግን በፍፁም(ሦስተኛ እጅ እየሆነ)አያራምድዎትምና ወደ ሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ አያረማምዱን፤አያሸጋግሩን፤በካድሬዎቹ  ሊዘረጥጥዎት እግርዎ ሥር ነው ያለው።ሲያዩት እንደወደቀ ያስመስላል(ወርቅነህ ገበየሁ)፤እንቅስቃሴዎን ሲጀምሩ(አስመላሽ ወ/ሥላሴ)በአርምሞ ያዳምጣል፤ከሩቅ ደግሞ(አርከበ ዕቁባይ)በአራት ዐይኖቹ ያነጣጥራል፤አባይ ፀሐዬ ያስቆሰቁሳል፣አባ ዱላ ገመዳ ያሳምፃል(በጁዋር ሴራ)፣ስብሃት ነጋ (ለጀሌዎች ይከፍላል)፣ተፈራ ዋሉዋ(ደቡብን ያሳምሳል)አዲሱ ለገሠ አማራን ያናክሳል፤ስንቱ ግፍ ይነገራል?ሕዝብ ግን ዛሬም ፈጣሪውን ይዞ፣በተስፋው-ሀብት ለነፃነቱ ይዘምራል፣ብችግሩ ይስቃል፣በደስታውም ያለቅሳል፤ካልሞላለት ይነሳል፣ወደ አመፅ ያመራል፤ካልተሳካ መች ይቀራል???!!!…..መረቅ አታብዙበት።

 

“ኢትዮጵያ ለዘላለም በነፃነት ትኑር!!!

Filed in: Amharic