>
9:30 pm - Tuesday July 5, 2022

እንግሊዛዊው እንዲህ እያለን ነው!! "ድሮ ድሆች እንጂ ባለጌ አልነበራችሁም! አሁን ግን ድሀም ባለጌም ሆናችሁ!!"

እንግሊዛዊው እንዲህ እያለን ነው!!
“ድሮ ድሆች እንጂ ባለጌ አልነበራችሁም! አሁን ግን ድሀም ባለጌም ሆናችሁ!!”
ተስፍሽ  ከራማ ሚዲያ
እንግሊዛዊ ባለቅኔ እና የቋንቋ ተመራማሪ ነኝ ስሜ ዋልተር አዳም እባላለሁኝ እድሜዬ 76 ነው እንደ አምላክ ቃል ካየነው የሰው እድሜ ቢበዛ 70 ከዛ በኋላ ድካም ነው እንደሚል ሁሉ 6 አመት በትርፍ እየኖርኩኝ ነው!!
.
ታዲያ በዚህ እድሜዬ በመላው አለም ስለሚኖሩ የሰዎች ቋንቋ በተለያየ ግዜ ለማጥናት ሞክሬአለሁኝ የኔ አባቶች በድህና ግዜ በቀኝ ግዛት ብዙ ሀገሮችን ስለገዙ የፈለኩበት ሀገር ሄጄ የፈለኩትን ተናግሬ የፈለኩትን ሰርቼ እንደልቤ ተመራምሬ ተመልሻለሁኝ።
.
እስካሁን ያልሄድኩባት ሀገር ግን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ነች እዝች ሀገር የመሄድም ሆነ የማየት እድል ከአንዴም ሁለት ግዜ ገጥሞኝ ቢያውቅም በጭራሽ ግን መሄድ አልፈልግም ነበር። ገና መሄድ ሳስብ እፈራለሁኝ ወዲያው ይርበኛል!!
.
ምክኒያቴንም ሳስበው ገና የ 30 አመት ጎልማሳ እያለሁኝ እርሀብ ምን እንደሚመስል ያየሁትኝ ኢትዮጵያውያን ተርበው በየሜዳው ሲያልቁ ነበር በወቅቱ የሀገሪቱ ንጉስ ሀ/ስላሴ ነበር በዛም ወቅት ህዝቡ ትንሽ ቢሆንም እርሀቡ ግን እጅግ ትልቅ ነበር። ያም ሆኖ በንጉሱ ዙሪያ እና በመላው ሀገሪቱ ትልቅ የፖለቲካ ሽኩቻ ነበር ዘርን ጨምሮ
.
በድጋሚ ስለ ኢትዮጵያ የሰማሁትኝ ከ 12 አመት በኋላ የ 42 አመት ጎልማሳ ሆኔ ነው በወቅቱ ለሁለተኛ ግዜ ኢትዮጵያ በድርቅ ተመታ ህዝቦቿ በየሜዳው አስከሬናቸው ተዘርግቶ አለም እጁን እንዲዘረጋ ሲለመን ነው በዛን ግዜም ደርግ ወይም መንግስቱ ሀይለማሪያም የሚባል ወታደራዊ አገዛዝ ነበር!! ያም ሆኖ በወታደራዊው መንግስት እና በዙ ዙሪያ በርካታ የፖለቲካ እና የዘር ሽኩቻ ነበር!!
.
ለሶስተኛ ግዜ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ የሰማሁትኝ የ 52 አመት ሽማግሌ ሆኜ ነው በዚህም ግዜ ከ 13 ሚሊዮን በላይ እርሀብተኛ እና አስቸኳይ ምግብ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን በመጠለያ ሆነው አስከሬናቸው ሲጎተት ነው በዚህም ወቅት መለስ ዜናዊ የሚባል መሪ እንደነበር አስታውሳለሁኝ !! ይሄም ሆኖ አሁንም በርካታ የፖለቲካ ሽኩቻ ብሄርተኝነት ዘረኝነት በጣም በስፋት ነበር!!
.
ዛሬ ደግሞ በ 76 አመቴ ስለዚች ጉደኛ ሀገር ስሰማ ከየተኛውም ግዜ አሁን ብሶባቸው በየ ክልላቸው ሲፈናቀሉ ከሀገር ሀገር ሲንከራተቱ ብሄርተኝነቱ እና ዘረኝነቱ ከየተኛውም ግዜ በላይ ጨምሮ እና ሰፍቶ በቀደሙት መሪዎች ግዜ ያላየሁትን እና ያልሰማሁትን ነገር በዚህ እድሜዬ የሰማሁት ደግሞ በጎልማሳው የሀገሪቱ መሪ በ ዶ/ር አብይ አህመድ ግዜ ነው!!
.
እናንተ ኢትዮጵያውያን ሆይ!!!!
.
ይህ እንግዲህ እጅግ በጣም በጣም ጥቂት የሆነው የስደት እና የርሀብ ታሪካችሁን ነበር በእድሜዪ የማስታውሰውን የነገርኳችሁ!! ስለ እናንተ ሲነሳ አለም ቀድሞ የሚያውቀው እርሀባችሁን ስደታችሁን እና አለመሰልጠናችሁን ነው!!!
.
እናንተ በትንሽ ነገር ብቻ አለም ስለ እናንተ የሚያወራ የመስላችሁላ!! በየ 4 አመቱ በሚዘጋጅ ኦሎምፒክ ላይ ኑሯቸውን ለመለወጥ የሚሮጡ ጥቂት እሯጮቻችሁን ስታዩ እና ወርቅ ካሸነፉ አለም ሁሉ ስለ እናንተ የሚያወራ ይመስላችሁላ!! ግን ተሳስታችኋል አለም የሚያውቃችሁ በኋላ ቀርነታችሁ በድህነታችሁ እና የርሀባችሁን ታሪክ ነው!!
.
ይሄን የርሀብ የድርቅ የኋላ ቀርነት ትሪካችሁን ቀይራችሁ ለአለም ማሳየት ሲጠበቅባችሁ እናንተ ኢትዮጵያውያን ግን ውሃ ቢወቀጡት እንቦጭ እንደሚባል ሁሉ አሁንም አድራችሁ እዛው ናችሁ አሁንም በዘረኝነት በብሄርተኝነት እና በአስተሳሰብ ድህነት ተወጥራችሁ ከአለም ድሀ ሀገሮች ተርታ እንዳላችሁ ናችሁ!!
.
በመበታተን ማንም አታሸንፉም ስትበታተኑ ለጠላቶቻችሁ ለጥርሳቸው ንክሻ እጅግ ትቀርባላችሁ በዙሪያቹ ሊውጧችሁ የተዘጋጁ እንደተከፈተ መቃብር ሊውጧችሁ የሚቋምጡ ብዙዎች ናቸው ይሄን ለብዙ አመታት ሞክርው ባይሳካላቸውም አሁን ግን እየተናዳችሁ ወደ መረባቸው እየገባችሁ ነው!!
.
ብዙ ያልተነካ የወጣት ጉልበት አላችሁ ወጣቶቻችሁን ከሱስ ከአደንዛዥ እፅ ብቻ ሳይሆን በመካከላችሁ ስር ከሰደደው ብሄርተኝነት እና ዘረኝነት ከኋላ ቀር አስተሳሰብ የተዛባ ድፍን አመለካከት እስካላወጣችሁ ድረስ እድሜ ሰጥቶኝ 80 አመት ከሞላሁኝ ኢትዮጵያ ከሚለው ስም ይልቅ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ የሚለው ስም የበለጠ የሚገልጣችሁ ይመስለኛል!!
.
ለመስማት ቢያስጠላችሁም እንኳን አንድ እውነት ልንገራችሁ እና ልጨርስ ስለ እናንተ ከዛሬ 50 አመት በፊት ስናወራ ኢትዮጵያውያን እኮ ድሮ ድሆች እንጂ ባለጌ አይደሉም እንል ነበር አሁን ግን ድሀም ባለጌም እየሆናችሁ ነው ስለዚህ ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው ተነስታችሁ ለማስተዋል ሞክሩ አለበለዚያ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ነበርች ይሆናል ታሪካችሁ!!
Filed in: Amharic