>
5:42 am - Friday July 1, 2022

የአማራ ክልል ህዝቦች ያለፉት አባቶቻችን የጣሉብንን ኢትዮጵያዊነትን የማጠናከርና ከፍ የማድረግ አደራ እንወጣ (መንገሻ ዘወዱ ተፈራ)

የአማራ ክልል ህዝቦች ያለፉት አባቶቻችን የጣሉብንን ኢትዮጵያዊነትን የማጠናከርና ከፍ የማድረግ አደራ እንወጣ
መንገሻ ዘወዱ ተፈራ
አዎ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ” ሱስ ግን በመላመድ ከጊዜ በኃላ የሚገኝ ሲሆን፤ኢትዮጵያዊነት ለኢትዮጵያዊያን ግን፤ከሱስ ያለፈ “አጥንት ስጋና ደማችን የተፈጠረበትና የተዋቀረበት ተፈጥሮአዊ ነው”።በተለይ ለአማራ  ክልል ኢትዮጵያዊያን ደግሞ፤ከክልሉ የመሬት አቀማማጥ፤ስን ምህዳረዊ ተፈጠሮ ጋር በተያያዘ፤ከሌላው አካባቢ የሚገኙ፤ኢትዮጵየዊያን ወገኖች፤ሲብሳቸውና ሲከፋቸው፤መሬቱ የኩርፊያቸው መሽሽጊና መወጫቸው፤ህዝቦቹ ደግሞ የተከፋ ኢትጵየዊያን ወገኖቻቸውን፤አስተናጋጅና፤ለነፃነት በግምባር ስጋነትና፤አብረው በመቆም መስዋዕት በመሆን፤አብረው የዘለቁ አሁንም ድረስ አበረው የሚገኙ ናቸው። አሁን ላለው ለውጥ መምጣትና የመቀጠል ሂደትም በግምባር ቀድምትነትና በአጋርነት  ተዋናይ ሆነው የሚገኙ፤ስለ ኢትዮጵያዊነት በአንድነት የሚዘምሩ ናቸው። ነገር ግን ከመላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር፤የለወጡን ቀጣይነት ለማረጋጋጥ እየጣሩ ባለበትና፤የለወጡን መቀጠል የሚያሰዩ አመላካች አንቅስቃሴዎች፤ማየት በሚጠብቁበት ስዓት፤እየተሰሙ ያሉት የወሬ ሽውታዎች ተስፋ አስቆራጭ ባይሆኑም ስጋት ጫሪ ናቸው።
ብዙ ጊዜ ሰዎች ይህችን አገር ፈጣሪ ይጠብቃታል ይላሉ። አንደተባለውም  ትላንት የካቲት 29/2011ዓ/ም፤በዕለተ “ባዕለ እግዚአብሔር” “ጁማኣ” የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ምክር ቤት የስተላለፋቸው፦
ባለማወቅ፣አቅም ውሱንነት፤ይሁን በመልካም አስተዳደር ማጓደልና፤ሙስና እጠየቃለሁ ፍርሃት፤በተደበቀ ቅሬታ፤በመላው የአማራ ክልል፤አሰከ አሁንም ድረስ፤የአስተዳደር ብሉሹነትና ሙስና አንደቀጠለ ነው። በተጨማሪም፤ፍፁም ሊከሰት የማይገባው፤አሁንም እንኳ፤ተፈናቅለው አብረው እየኖሩ ያሉ። ወንድማማቾች፤አንዲገዳደሉ፤ንብረታቸው አንዲወድምና፤አሁንም ድረስ በመጠለያ አንዲገኙ እያደረገ ያልን፤እኔን አይንካኝ አንጅ፤የራሱ ጉዳይ፤አይነት አስተሳሰብ የተጫናቸው፤ኃላፊነት የጎደላቸውና፤በቸልተኝነት የሚገኙ ደካማ፤የሰው ኃብት ስምሪት፤አብዛኛው የክልሉ ህዝብ በሚመኛቸውና፤ተስፋ ባለው የሰው ኃብት የመቀየር፤ 2. አንደ ሌሎች በእድገታቸው፤ከብረት የጠነከሩ አገሮች፤ለምሳሌ ጀርመን በአሏት፤የምሁራን ስብስብ በመጠቀም፤ህዝቧን መሰረት ያደረገ አመራር መስጠት ተመክሮ፤ለመጠቀም የሚያስችል፤የክልሉን የምሁራን መማክረት፤ማቋቋሚያ፤ማፅደቅ፣ውሳኔዎች ሲሰማ፤እውነትም ይህችን አገር የሚጠብቃት ፈጣሪ  ነው የሚለውን ኃሳብ የሚያጠናክር ነው።
ሰለዚህ ፈጣሪ፤”ፈልጉ ታገኛላችሁ” “አንኳኩ ይከፈትላችኃል”፤እንዳለው ከፈጣሪ ጥበቃ በተጨማሪ፤ አነዚህን ከላይ የተከሰቱትን ስህተቶች፤በለውጥ ጊዜ አንደሚከሰት ክስተት በመቁጠርና፤ከዚህ ትልቅ ትምህርት አግኝቶ ይህንን ስህትት ዳግም ባለመድገም ቀጣዩን ጊዜ በውጤትና ተስፋ እየደረደሩ ለማሰቀጠል፦
ከትላንቱ አዲስ ተሿሚዎች፤ነገና ከነገ ወዲያ፤ከዶ/ር አምባቸው መኮነን የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳር፤ ያስተዋወቁናል ብለን ከምንጠብቃቸው አዲስ የካቢኔ አባላት ጭምር፤
ከክልል አስከ ቀበሌ ነገ ለውጡ፤ከቀጠል በአቅም ማነስ ቦታየን አጣለሁ፤በኃላ ታሪኬ፤መልካም አስተዳደር ማጓደልና፤በሙስና እጠየቃለሁ ፍርሃት፤በእከክልኝ ልከክልህ ቃልኪዳን፤አንደ ሐረግ ተያይዞና፤ተሸሽጎ የሚገኝን የቡድን ዝሃ፤በመበጣጠስ ከሚተኩ አዲስ ንፁህና፤የማስፈፀም አቅም ካላቸው አስፈፃሚዎች፤
በተለይ ከክልሉ የአስተዳደር ፀጥታ ሰላም ቢሮ፤የልዩ ኃይል አዛዥ፤ሁለቱ ጀኔራሎች፤
ከእኛም መላው የአማራ ክልለ ህዝብ፤በጓዳ ጎድጓዳው፤ከምናወራውና፤ከመብሰከሰክ አለፍ ብለን፤እኔ ምን ተወጣሁ በሚል የኃላፊነት መንፈስና ስሜት እራሳችን እየጠየቅን፤
ከጎንደር ህዝብ፤ተሞክሮ በመውስድ፤በመደራጀት አቅማችን በሚፈቅድው የድረሻችን በማበርከት “ሳንጋፋና ሳንገፋ”ከሌላው አትዮጵያዊ ወገናችና ጋር በመሆን “ሰላምና ልማትታችን” ለማረጋገጥ በመጣር፤ የአማራ ክልል ህዝቦች፤ያለፉት አባቶቻችን የጣሉብንን፤ ኢትዮጵያዊነትን የማጠናከርና፤ከፍ የማድረግ አደራ እንወጣ”።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለዓለም ትኑር
Filed in: Amharic