>

የቁጥሩ ምልክት እና የንስሯ ኢትዮጵያ ትንሳኤ!! (ዘመድኩን በቀለ)

የቁጥሩ ምልክት እና የንስሯ ኢትዮጵያ ትንሳኤ!!!
ዘመድኩን በቀለ
በዚህ ዓለም በአሁኑ ጊዜ ምንም ነገር ባጋጣሚ የሚከሰት ብሎ ነገር የለም። በተለይ አሁን በምንገኝበት በጨለማው የዓለም መንግሥት ዋዜማ ላይ የሚፈጸሙ አሰቃቂ ተግባራቶች ሁሉ በቀመር የሚፈጸሙ ናቸው።
•••
ተመልከትልኝማ ሲጀመር አውሮጵላኑ ወደቀ የተባለበት ስፍራ ካልጠፋ ቦታ በቢሾፍቱ አካባቢ ነው። ቢሾፍቱን ያዝልኝ። ቆሪጥንም አስታውስ። አንድ አልክልኝ።
•••
ሲቀጥል ደግሞ የመንገደኞቹን ብዛት ስንደምር የ157 ሰው ቁጥር እናገኛለን። 157 መንገደኞች። ይሄን ቁጥር በደንብ ያዝልኝ። እነሱ በGemeteria ማለትም የፊደላት ቊጥርን ካልኩሌት በሚያደርጉበት መንገድ ስንተነትነው። 1 + 5 + 7 = 13 ቁጥርን እናገኛለን። 13 ቁጥር ደግሞ የአጅሬ የዲያቢሎስ የግብር ቁጥሩ ነው።
•••
እንቀጥልና አውሮጵላኑ ግኑኙነትን ያቆመው ወይም በእነሱ አጠራር connection lost ያደረገው በ 6 ተኛው ደቂቃ ነው ብለውናል። 6 ቁጥርን ያዝልኝ። ከዚያ አውሮጵላኑ ይበር የነበረው 600 ኪሜ በሰዓት ነበር ተብሏል። ተመልከት አሁንም ከ6 አልወጡም። ሁለቱን ዜሮ አጥፋውና 6 ትን ያዝልኝ። በ6 ደቂቃ ውስጥ በሰዓት 600 ኪሎ ሜትር መብረር እንዴት እንደሚቻል አላውቅም። በመጨረሻም አውሮጵላኑ የተከሰከሰው ከአዲስ አበባ 60 ኪሜ በቢሾፍቱ ዙሪያ ነው ተባለ። አሁንም ከዜሮ በፊት 6 ከተፍ ትላላለች። ቢሾፍቱም ተደጋግሞ በመላው የዓለም ሚድያ መጠራቷን ልብ ይሏል። ቢሾፍቱን ስታስታውስ አደራ የቆሪጥንም ታሪክ እንዳትረሳ አስታውስ። ለማንኛውም።
•••
አሁንም በጂኦሜትሪያ አቆጣጠር የቢሾፍቱን ጠቅላላ ድምር እንደሚከተለው ስታሰላው 6 ትን ከፊት ጉብ ብላ ታገኛታለህ።
B= 12
I = 54
S= 114
H= 48
O= 90
F= 36
T= 120
U= 126
ጠቅላለ ድምር = 600
157 መንገደኞች = 1+5+7= 13✖
connection lost = 6 ተኛ ደቂቃ
የበረራው ፍጥነት በሰዓት = 600
ከአዲስ አበባ ርቀቱ = 60 ኪሎ ሜትር።
እነዚህን ሦስቱን የመጀመሪያዎቹን 6 ቁጥሮች ወደታች ወስደህ ስትደምራቸው ቁልጭ ያለውን 666 ን ታገኘዋለህ።
•••
ይሄ የኦርዶ አብ ኬዮ የመጀመሪያው እና የሁለተኛ ደረጃ ነው። ኦርዶ አብ ኬዮ ማለት
“ expression, meaning Order out of Chaos. A motto of the Thirty-third Degree, and having the same allusion as lug e tenebris, which see in this work. The invention of this motto is to be attributed to the Supreme Council of the Ancient and Accepted Scottish petite at Charleston, and it is first met with in the Patent of Count de Grasse, dated February 1, 1802. When De Grasse afterward carried the polite over to France and established a Supreme Council there, he changed the motto, and, according to Lenning, Ordo ab hoc, Order out of This, was used by him and his Council in all their documents. If so, it was simply a blunder.
– Source: Mackey’s Encyclopedia of Freemasonry
•••
በዚህ መሠረት መጀመሪያ problem ይፈጥራሉ። ከዚያ reaction ይከተልና በመጨረሻም solution የሚባለው ደረጃ ይከተላል። ይህም ማለት የጨለማዉ መንግሥት የሚፈልገውን የሚያደርጉበት በዚህ አሳበው የሚፈልጉትን የሚፈጽሙበት ደረጃ ነው።
•••
በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ላይ የዓለም ዐይኖች አፍጥጠዋል። ካልጠፋ ሀገር የሶሪያ ስደተኞች ተብለው አዲስ አበባን ከወረሯት አረቦች ጀርባ ያለውንም ነገር መመርመሩ ተገቢ ነው። አሁን የሦርያ ስደተኞች የተባሉትና በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የሚርመሰመሱት ዐረቦች ከምር ስደተኞች ናቸው ወይ? ስደተኛ ከሆኑስ ለምን የስደተኛ ካምፕ አይገቡም?
•••
ሌላው ዐረቦቹ የሌለ ደግ ሆነው በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር በእርዳታ ስም ማፍሰሳቸውንም ልብ በሉ። መሃል አዲስ አበባን ያውም ለገሃርን በግልጽ ገዝተውታል። ይሄ ሌላኛው ምልክት ነው። ከ150 ዓመት በፊት የነበሩት የወሎው ሼክ ሁሴን ጂብሪል ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ማለታቸውን አስታውስ።
180. አረብ አገራችን ሳይለምድም አይቀር
         ወልደው ይከብዳሉ ያደርጋሉ አገር
•••
ቀጥሎ በብላክ ቦክሱም ሆነ በሌላ ከፍተኛ ጭቅጭቅ ሆን ተብሎ እንዲፈጠር ሊደረግ ይችላል። በዚህ ጉዳይ አሜሪካ ነው የሚመረመረው አይ አውሮጳ ነው ጭቅጭቅ ተጀምሯል። ከዚያ ምን አባክ ምን አባሽ ይከተላል። ከዚያ ሃያላኑ ሀገራት ግማሹ የኢትዮጵያ ወዳጅ መስሎ፣ ገሚሱ ደግሞ ጠላት ሆኖ ይሰለፋል። ከዚያ በውጤቱ ሶርያን ማስታወስ ነው። አሜሪካና ሸሪኮቿ በአንድ በኩል። ሩሲያና ሸሪኮቿ በሌላ በኩል ሆነው ሶሪያን ያደረጓትን፣ የአዳዲስ የጦር መሣሪያ መፈተሺያ፣ መሞከሪያም ያደረጓትን የመንንም ማስታወስ ነው።
•••
በመጨረሻም ማስተዳደር አልቻልኩም ይመጣል። ከዚያም እባካችሁ አግዙኝ ይከተላል። እነማን ለማገዝ እንደሚመጡ ግን መድኃኔዓለም ነው የሚያውቀው። ሳዑዲ ቀብድ ከፍላለች። ፈረንሳይ ከአሁኑ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ለማገዝ ጦሬን አዲስ አበባ እልካለሁ ብላለች። አሜሪካ ጠንካራውን የኢትዮጵያ የደኅንነት መሥሪያ ቤት እንደተረከበች ይቆጠራል የሚሉ አሉ። የልብ ወዳጃችን አጅሪት ግብጽም የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽንን ለመግዛት መጎምዠቷ እየተነገረ ነው። ጠቅላያችን እንደሆነ ወላሂ፣ ወላሂ ግብጽን የሚጎዳ አንዳች ነገር አላደርግም ሲል በአደባባይ ምሎ ተገዝቶ ቃልኪዳዱን አጥብቆላቸዋል።
•••
የሚገርመው ነገር ግን እኛ ስለወደቅን ነው ኢትዮጵያ የወደቀችው እኛ በንስሐ ታድሰን ስንነሳ ኢትዮጵያም ፈጥና ትነሳለች። ይሄ የተረጋገጠ እውነት። በበረሃ የወደቁ፣ ሳርም ያበቀለባቸው አባቶች ከዘንዶው መንፈስ ጋር ውጊያ ላይ ናቸው። እስከ አሁንም በትንቅንቅ ላይ ናቸው። እኛ አላገዝናቸውም እንጂ እነሱስ እየደከሙ ናቸው። ወጣቱ ጫት ላይ ዘመቻ ቢጀምር፣ ጭፈራና ዳንኪራው አንቡላ መጋፉ ቢቀር። ቅጥ ያጣው ዘማዊነት ቢወገድ፣ ማስቀደስ፣ መጾም የሁሉም ድርሻ ቢሆን፣ ሁሉም ክርስቲያን ንስሐ ቢገባ፣ ጎላ ጎላ ያለ መስቀል ሁሉም በሚታይ መልኩ ደረቱ ላይ እያንጠለጠለ ቢሄድ የአውሬው መንፈስ ይታወካል። ልብ ብላችሁ ከሆነ በኢትዮጵያ በአንዳንድ ክልሎችም ሆነ በመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች መስቀልና ማዕተብ ማሠር የተከለከለ ነው። በጥሱልኝ የሚሉትም ለዚያ ነው።
•••
የምናየው የምንሰማው ነገር ሁሉ እንደ ማዕበል ያለ፣ እንደ ደራሽ ጎርፍም ያለ ድንገቴ ነገር ነው። ቆይቶ እኛም በመንፈሳዊነቱ ከበረታን የምናየው ማዕበለም ሆነ ጎርፉ ፀጥ ይላል። ደራሽ ጎርፉም የጠረገውን ያህል ቆሻም፣ ግንዲላም ጠራርጎ በጊዜው ያልፋል። እኛም ከሚመጣው ደራሽ ጎርፍ ከመወሰድ፣ ከሚመጣው ማዕበልም ከመጥለቅለቅ አምላካችን ይሰውረን።
እደግመዋለሁ። 100000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000000 % እርግጠኛምሆኜ እነግርሃለሁ ኢትዮጵያ ትነሳለች። እንደ ንስርበታድሳ ትነሳለች። ድልም ታደርጋለች።
ሻሎም !  ሰላም  !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
መጋቢት 5/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic