አህመዲን ሱሌይማን
ሀበሻ አሁን ላይ የሚያስፈልጋት አፄ ሚኒሊክን የመሰለ መገረፍ ያለበትን እየገረፈ የሚያባር፣ ሰላም የሚፈልግን አቅፎ የሚያስጠጋ ፍርሃ አምላክ የሆነ አባት መሪ ነዉ!!
—
ከጨለንቆዉ ሽንፈት አንድ ወር በኋላ፣ የሐረር ሽማግሌዎች የሐረር ከተማን በማስተዳደር ላይ ንጉሡን ለማወያየት ወደ አፄ ሚኒሊክ መጡ። የሚከተለዉ ሰነድ ዉይይታቸዉን በተመለከተ በፅሁፍ የተስማሙበትና የተቀመጠዉ ሰነድ ነዉ። ስምምነቱ በግርድፍ ትርጉሙ እንደሚከተለዉ ይነበባል። አረብኛ የምታዉቁ የተቀመጠዉን ትርጉም ማመሳከር ትችላላችሁ። የኦሮሞና ቄሮ በደል ያንገሸገሻቸዉ የሀረር ልጆች፣ ያበጠዉ ይፈንዳ ጠላት ተብሎ ሲነገረን የኖረዉ የዉሸት ትብታቦ እዉነቱ ይዉጣ በማለት ወደ እንግሊዘኛ ተርጉመዉ በትዊተር ላይ ያስቀመጡትን ነዉ እዚህ ወደ አማርኛ የገለበጥኩት።
****
የሀረር አባቶች ሀጂ ዩሱፍ በርክህድሌ፣ መምህር ሸህ አሊ አቡበክር ቢን አብዱልሸኩር፣ ዳኛ አብዱላህ ቢን አልቃዲ አብዱራህማን፣ ጋራድ አብዱራህማን አልከኑቅ፣ ጋራድ አብዱልወሀብ፣ ሸህ ሙሀመድ አማንና ሌሎችም መልዕክተኞች ያሉበት ልዑክ፣ ከአቢሲኒያዉ ንጉስ ጋር ሰላምን ፈልገዉ መጡ።
መልዕክተኞቹ ንጉሱን ድሬ ሻምብራ? በሚገኝ መጠለያ ሸህ ጀበል አቡበክር በተገኙበት ተገናኟቸዉ። ንጉሱም እንግዶቹን ለማስተናገድ ፍቃደኝነታቸዉን ገለፁ።
በመጀመሪያም ለደህንነታቸዉ ዋስትናን ከንጉሱ ጠየቁ። ንጉሱም ዋስትናን ሰጧቸዉ።
በማስከተልም እንዲህ ብለዉ ተናገሩ፣
ንጉስ ሆይ እየጠየቅን ያለነዉ ሊሆን የሚችልን ነገር ነዉ።
አንደኛ ሀይማኖታችንን ያለ ገደብ ለመተግበር የምንፈልግ መሆናችን ይታወቅልን።
ሁለተኛ የዉስጥ ጉዳያችንን እራሳችን እየፈታን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እራሳችንን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን።
ሶስተኛ የሀረር ህዝብ መሬት ቤት ሀብትና ንብረቱ የሚገባዉን ሙሉ ጥበቃ ይደረግለት ስንል እንጠይቃለን አሉ።
ንጉስ ሚኒሊክም ወደ ሸዋ ከተመለሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ መልዕክተኛን ወደ ሐረር ልከዉ ሀጂ ዩሱፍ በርክህድሌ፣ መምህር ሸህ አሊ አቡበክር ቢን አብዱልሸኩር እና ዳኛ አብዱላህ ቢን አልቃዲ አብዱራህማን አለም ማያ ላይ እንዲገናኟቸዉና በሚመጡም ጊዜ #ቅዱስ ቁርዓንን አብረዉ ይዘዉ እንዲመጡ መልዕክት ላኩባቸዉ። እንደተባሉት ንጉሱን ሊገናኙ መጡ።
ስብሰባዉ ላይ ንጉስ ሚኒሊክ የሐረር ሽማግሌዎች በሶስት ነገሮች ላይ እጃቸዉን በቁርዓኑ ላይ በማድረግ ቃል ኪዳን እንዲገቡ ጠየቁ። ሽማግሌዎቹም ተስማሙ።
አንደኛ ለግብፅ መንግስት ስለከፈልነዉ ወይም እኛ ከግብፅ መንግስት ስለተከፈለን ግብር የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ እንደማንደብቅ ቃል እንገባለን በማለት በቁርዓናችሁ ማሉ።
ሁለተኛ በሀገራችን ላይ የተቃጣና የሚጎነጎን ማንኛዉም አይነት የዉጭ ጠላት ሴራን እንደምታጋልጡና እንደማትደብቁ ቃል ኪዳን ግቡ።
ሶስተኛ ህዝቡ በደል ደረሰብኝ ካለ ለሚመለከተዉ አካል በሰልፍም በተቃዉሞም ድምፁን ማሰማት የሚችል እንደሆነና የሚመለከታቸዉ አካላት የህዝብን ጥያቄ መመለስ የማይችሉ ከሆነ ለንጉሱ ቅሬታቸዉን እንደምታስተላልፉ ቃል ኪዳን ግቡ አሏቸዉ።
በሁሉም አንቀፆችና በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ተስማሙ። ቃል ኪዳናቸዉንም በሀይማኖታቸዉ መፅሀፍ ማሉ። ሁለቱም አካላት ተፈራረሙበት። ሰነዱም ተከደነ። ይሄ ስምምነት ከጁማዱል አወል 1304 (Feb, 4 1887) ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባ ይሆናል።
*********
ሀበሻ አሁን ላይ የሚያስፈልጋት አፄ ሚኒሊክን የመሰለ መገረፍ ያለበትን እየገረፈ የሚያባር፣ ሰላም የሚፈልግን አቅፎ የሚያስጠጋ ፍርሃ አምላክ የሆነ አባት መሪ ነዉ።
ይሄንን ሰነድ የጀዋር መሀመድ አጋፋሪ የሆኑት አህመዲን ጀበልና አፈንዲ ሙተቂ አዉጥተዉት አላየሁም። አሁን እንኳ አፈንዲ ሙተቂ በኦነግና ቄሮ በተባለ የጃዋር ሚሊሻ፣ የሐረር ህዝብና ዘመዶቹ መታመስ ከጀመሩ ጀምሮ ጠላትና ወዳጁን በመለየቱ ቶብቷል የሚሉ አሉ።
ለሀገራችን ለኢትዮጲያ ለአቢሲኒያ ለሀበሻ ዱዓ ዱዓ ፀሎት ፀሎት ሱባኤ ጩኸት ከምንግዜዉም በላይ ያስፈልጋል።
****
መልካም ጁምአ