>

በኦነግና በዐቢይለማ ጥምር መንግሥት  እየተጨፈጨፈ ያለው የኮሬ ህዝብ የድረሱልኝ ጥሪ!!!  (ዘመድኩን በቀለ)


በኦነግና በዐቢይለማ ጥምር መንግሥት 
እየተጨፈጨፈ ያለው የኮሬ ህዝብ የድረሱልኝ ጥሪ!!! 
ዘመድኩን በቀለ
 
~ በደቡብ የሚገኙ በቁጥር አናሳ የሆኑ ነገዶች በአህዴድኦነግ፣ በ ዐቢይለማጃwar ጥምር መንግሥት እንዲጠፉ የተፈለገ ይመስላል። 
 
#ETHIOPIA | ~ እዚህጋ ደግሞ ሌላ ትኩሳት። እሳት፣ እሳት እሳት። ኧረ አይነጋም ወይ ሌቱ ኢትዮጵያዬ አለ ቴዲ አፍሮ። 
 
መረጃው የደረሰኝ ከጌዲኦዎቹ ሰቆቃ እኩል ጊዜ ነው። እናም ከመረጃ አድራሾቼ ጋር ተመካከርን። የማንኛው ይቅደም ተባባልን። የጌዴኦ ይቀድም ዘንድ ተስማማን። እናም እሱን አስቀደምን። የጌዲኦ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ከሆነ በኋላ በስምምነታችን መሠረት አሁን ደግሞ የኮሬን ህዝብ ሰቆቃ ላረዳችሁ እነሆ ብቅ ብያለሁ። እናም ወገን ተረባባረብ
•••
ዘመዴ ይላሉ ኮሬዎች። ዘመዴ እኛ እንደ ጌዲኦ ህዝብ ርስታችንን አለቀቅንም። አጋዥ አጣን እንጂ ከኦነግኦዴፓ መንግሥት ጋር እየተዋደቅ ነው። ድሮ ድሮ ከኦነግ ጋር ስንዋጋ ዩኒፎርም ስላልነበራቸው በቀላሉ አንመክታቸውና እናባርራቸው ነበር። አሁን ግን ኦነግ የሀገር መከላከያ አዳዲስ ዩኒፎርም ከዘመናዊ መሣሪያ ጋር መንግሥት ስላስታጠቃቸው መከላከያውንና የኦነግን ሠራዊትን ለመለየት ተቸግረናል። እሱ ነው ያቃተን። እኛ ከሩቅ አይተናቸው የመንግሥት ወታደሮች ናቸው ብለን በደስታ ስንጠብቅ እነሱ አጠገባችን ከደረሱ በኋላ በጅምላ ያለ ርህራሄ ይጨፈጭፉናል። እሱ ነው የቸገረን።
•••
ይሄን ይሄን ስናይ በደቡብ ለምንገኝ በቁጥር አናሳ ለሆንን ብሔር ብሔረሰቦች መጥፋት የዐቢይና የለማ መንግሥት ለኦነግ ጭፍጨፋ ይሁንታ የሰጡ ይመስለናል።አሁን የኦነግ ሠራዊት መንደሮቻችንን በማቃጠል። ማሳዎቻችን በማውደም። የምንበላው አጥተን በረሃብ እንድናልቅ የእንሰት ተክላችንን በመጨፍጨፍ፣ አቅመደካሞችን ሳይቀር በቤት እንደተቀመጡ በመጨፍጨፍ ታላቅ የሆነ የዘር ማጥፋት እየተደረገብን ይገኛል።
•••
የኮሬ ህዝብ በደቡብ ክልል በቀድሞው ሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን አማሮ ወረዳ የሚገኝ ህዝብ ነው። አማሮ ብሔሩ የሚኖርበት ምድር መጠሪያ ሲሆን ኮሬ ደግሞ የብሔሩ መጠሪያ ነው። በዞኑ የሚካተቱት ኮንሶ፣አማሮ፣ ደራሼ፣ ቡርጂና አሌ ወረዳዎች ነበሩ። ሆኖም ግን ዞኑ በቅርቡ በህዝብ አመፅ ሲበተን ከኮንሶ ውጭ የተቀሩት እስካሁን መዋቅር አልባ ናቸው። አከባቢው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር የሚታይበት ነው። በአማሮ ችግሩ የተጀመረው ሐምሌ 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የኦነግ ወታደሮችና የጉጂ ወራሪ ኃይል ዳኖ ቡልቶ በተባለችው የገጠር ቀበሌ ያልታሠበ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት ነው። በዚህ ቀን ሦስት በማሣቸው የእርሻ ሥራ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ሞተዋል።
•••
በመቀጠልም በ19/11/2009 ዓ.ም በቆሬ ቢቆ ቀበሌ ታይቶ የማይታወቅ ዓይነት ተኩስ በጣም ብዙ በሆኑ የኦነግ ሠራዊትና ኦነግ ባስታጠቃቸው የጉጂ ኦሮሞ ሚልሻዎች ተከፈተ። ህዝቡ ሣያስብ የተከፈተ ተኩስ በመሆኑ ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤልን ክብረ በዓል ከሚያከብርበት ለቅቆ ተበታተነ (ቆሬ ቅዱስ ገብርኤል ወቅዱስ ቅርቆስ ቤተክርስትያን) በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት በዕለቱ የቀበሌው ልቀ መንበር መቁሰል እንጂ የሞተ ሰው አልነበረም።
•••
እንግዲህ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ይኸው እስከ አሁን ነፍስ እየጠፋ ነው።  ይህ እየሆነ ያለው በኦሮሚያ ክልል የአማሮን ወረዳ ከሚያዋሰነው ምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ የመሸገው ኦነግና ኦነግ በሚመልምላቸውና በሚያሰለጥናቸው የጉጂ ሚልሻዎች ነው። ይህንንም በዋናነት የሚያስተባብረው የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳደር አቶ አበራ ቡኖ ይባላል። የምዕራብ ጉጂ ዞን መቀመጫ ቡሌ ሆራ ነው። በዚህ ዞን የሚገኙ አብዘኞቹ ወረዳዎች እስከአሁን በኦነግ ሥር ናቸው። ለምሣሌ አባያ፣ ገላና፣ ሱሮ ባርጉዳና ቡሌሆራ ናቸው። አማሮ በጥቅሉ 35 ቀበሌያት አሏት። ከነዚህ ውስጥ 16ቱ ቀበሌያት የኦነግና የጉጂ ሚልሻዎች በየሰዓቱ ጥቃት የሚያደርሱባቸው አከባቢዎች ናቸው።
•••
በእስካሁኑ የኦነግና ጉጂ ህዝብ ወረራ የዘር ጭፍጨፋ በኮሬ ህዝብ ላይ የደረሱ በደሎች
•••
፩፦  በተጨባጭ ከ98 በላይ ንፁሃኖች(በማሣቸው ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች፣ መንገደኞች በመኪና ውስጥ፡ ሾፈሮች፣ ወጣቶች) ህይወታቸውን አጥተዋል።
፪፦ ሁለት ቀበሌያት ማለትም ጀሎና ዶርባዴ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። በእነዚህ ቀበልያት የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት፡ ት/ቤትና ጤና ኬላን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በኦነግ ወድመዋል።
፫፦አማሮ ወረዳን ከሀዋሳና ከአ.አ በዲላ በኩል የሚወስደው ብቸኛው መንገድ ከ16/11/2009 ጀምሮ ዝግ ነው። በዚህ መንገድ ለፀጥታ ወደ አማሮ ተልከው የሚመጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም የኦነግ ጥቃት ሠለባ ናቸው።
፬፦ ታቦት ብቻ ለማስገባት በዝግጅት ላይ የነበርነው የጀሎ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እንዳልነበረ ሆኗል። የኪዳን ቆርቆሮው ተገንጥሎ በኦነጎቹ ተወስዷል። በሮቹ ሁሉም ተወስደዋል። ጉልላቱንም ሠብረውታል።
፭፦ በ16 ቱ ቀበሌያት የሚገኙ አርሶ አደሮች ሙሉ በሙሉ እርሻቸው ወድሟል። በዚህ ለከፍተኛ ረሃብና እንግልት ተዳርገዋል። በአጠቃላይ ከ25000 በላይ ህዝብ ከቄየው ተፈናቅሎ የሚያየው የለም። ከቡሌሆራና ሞያሌ ኮሬ በመሆናቸው ብቻ የተፈናቀሉ ህዝቦች በጊዜያዊ መጠለያ ናቸው ያሉት። የሚቀመስ ነገር የላቸውም። በብርድና በሃሩር እያለቁ ናቸው።
፮፦ ከአማሮ ዲላ ሐዋሳ የሚወስደው መንገድ በኦነግ በኃይል ቢዘጋም ህዝቡ በአማራጭ ከአማሮ-ኮንሶ ከኮንሶ -አርባምንጭ- ከአርባምንጭ ሶዶ- ከሶዶ ሐዋሳ እየተጠቀመ ቢገኝም በቡርጅና ኮንሶ መካከል በሚገኘው በተለምዶ ሠገን በረሃ ውስጥ ኦነግ በዚያም ምሽግ ሠርቶ እስካሁን 6 ንፁሃንን ገድሎብናል ( ዘመዴ በፎቶው የላኩልህም ከሣምንታት በፍት በዚያ በረሃ ኦነግ የገደላቸው ንጹሐን ወንድሞቻችን ናቸው።)
•••
ዘመዴ ኦነግ መንገዱን ባይዘጋብን ኖሮ ከአማሮ ዲላ 65 ብር ነው። በኮንሶ በኩል ግን እስከ 500 ብር ያስወጣል። በዚህም በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በህዝቡ ላይ ተከስቷል። ጤና ጣቢያዎቹን ስላቃጠሏቸው በሽተኞች በቤታቸው እየሞቱ ነው። ተማሪዎች ተመርቀው ወጥተው ሥራ መፈለግ እንኳን አልቻሉም።
•••
በአጠቃላይ በህይወት ያለውም ከፍተኛ የሥነ ልቦና ችግር ውስጥ ነው። መች እንደሚሞት አያውቅምና። ምክንያቱም ሌሊቱን ሙሉ ከኦነግ የሚተኮሰው የክላሽና የመትረየስ ድምፅ አያስተኛህም። ሌሊት ገብተን ከተማችሁን እናቃጥላለን የሚል ዛቻ በየጊዜው ከኦነግ የሚሰማ ነው እናም ህዝቡ ጫካ ሲያድር ይኸው ድፍን ሦስት ዓመት ነጎደ። መከላከያ ቢሰማራም እየተዋጉ ብዙዎቹም የመከላከያ አባላት ሞተዋል።
•••
ዘመዴ አንተ ዘረኛ አይደለህም። አንተ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነህ። በመሆንህም የጌዲኦ ህዝብን ሰቆቃ ልከንልህ በገጽህ ላይ በማውጣትህ ይኸው ዓለምአቀፍ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። እናም ዘመዴ ይሄን የእኛንም ሰቆቃ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን አሰማልን፣ የዓለም ህዝብ ይድረስልን። ዘመዴ፣ ዘመዴ፣ በምትወዳት ሃገርህና ዘወትር ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ በምትላት የአምላክ እናት በደንግል ማርያም ስም እንማጸንሃለን።
•••
ያው እኔ በበኩሌ የወገኖቼን ሰቆቃ ለእናንተ ጆሮ አድርሼላችኋለሁ። ይሄን ለዓለም ህዝብ ካደረስኩኝ በኋላ ደግሞ ሌላ የተደበቀ ሰቆቃ ሰሞኑን አረዳችኋለሁ። እኔ የዜግነት ግዴታዬን እየተወጣሁ ነው። እናንተስ?
•••
በነገራችን ላይ ይሄን ጥረቴንና ተጋድሎዬን በሚዲያ መልክ ከፍ ለማድረግ እያሰብኩ ነው። ስለዚሁ ጉዳይ ከጀርመን መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋርም በሕጋዊ መንገድ ቢያንስ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩቲዩብ ለመከሰት እችል ዘንድ እየተነጋገርኩ ነው። ከብዙ ንግግር በኋላ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ መግባባት ላይ ደርሰናል። አንዲት የውይይት ቀጠሮ ብቻ ነው የሚቀረን።
•••
ከዚያ ወደ ቴሌቭዥን እና ወደ ራዲዮም ከፍ ለማድረግ እሞክራለሁ። ለጊዜው ጀርመኖቹ ለሥራህ የሚያስፈልግህን ማቴሪያሎች በዝርዝር ጽፈህ አቅርብልና የምንችለውን ያህል ልንረዳህ እንሞክራለን ብለውኛል። እሱን በሚቀጥለው ወር መግቢያ ላይ በቀጠሮአችን ዕለት አቀርብላቸዋለሁ። እነሱ ካሟሉልኝ አሟሉልኝ። ካላሟሉልኝ ግን ነግሬያቸዋለሁ። ለህዝቤ፣ ለወገኔ ነግሬ ለሥራው የሚያስፈልጉኝን መሣሪያዎች ራሴው አሟላለሁ ብያቸዋለሁ። እናም ተዘጋጁ። አንድ አስር ሰው ብቻ ቢረዳኝ ይበቃኛል። የምፈልገው ማቴሪያል እጅግ በጣም ጥቂት ነው። በዚያ መልኩ ለመከሰት ከጫፍ ደርሻለሁ። በጸሎታችሁም አግዙኝ። ይኸው ነው።
ሻሎም !  ሰላም  ! 
መጋቢት 6/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic