>
10:49 am - Monday August 15, 2022

የኦዴፓ - ውንብድና እና  ሽብር በቄሮ ሽፋን!!! (ሲሳይ አበበ)

የኦዴፓ – ውንብድና እና  ሽብር በቄሮ ሽፋን!!!
ሲሳይ አበበ
* መንግስታዊ መዋቅርን ለወንጀል ተግባር ማዋል 
* ኦሮሚያን ለማፍረስ የተጠነሰሰ የኦዴፓ ሞኛ ሞኝ ሴራ
 
 ኦዴፓ የሚጠቀማቸው ተንኮሎች በሙሉ ከህውሀት ጓዳ የተቀዱ ናቸው።ለምሳሌ ህውሀት የሆነ ነገር ሲያደርግ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተቃወመው : ይል የነበረው “የትግራይ ህዝብ ተነካ” ብሎ በትግራይ ህዝብ ሽፋን ይሰጥ ነበር።አሁን ደግሞ ኦዴፓ/ ኦነግ ሁሉን ነገር ከቄሮ ወይም ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያላትመዋል።ያ ማለት ኦዴፓ የዘቀጠ ድርጅት እና በዘቀጡ ሰወች የታቀፈ መሆኑን እያየን ነው።
***
የኦሮሞን ህዝብ ነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል በመቀልበስም ሆነ የኦሮሞን ሀብትና ንብረት በመዝረፍ የካበተ ልምድ ያለው ኦዴፓ ዛሬ ይህን ክህደት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቢፈጽም ሊደንቀን አይገባም፡፡ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት የቆዳ ስፋት ያለውን ክልል ማስተዳደር ተስኖት ያለፉትን ሀያ ሰባት አመታት ትእዛዝ ተቀባይ ሆኖ እንዳልከረመ አሁን የተሰጠውን የህዝብ ሀላፊነት መሸከም አቅቶት አፈር ለአፈር እየጎተተው ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይበቃው ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ለኦሮሚያ ክልል ያቀረቡ ማህበረሰቦችን መንግስታዊ መዋቅርን በመጠቀም  የተደራጀ የቄሮ ሀይል እና የኦነግ ታጣቂ በመላክ በባንጋ እና በገጀራ ሲያስጨፈጭፍ እንደከረመ የጌድዮ ህዝብ ተወካዮች ተፈናቃዮችን ለማየት ለሄደው ለኦዴፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚሩ የተናገሩትን ይኸው ሰምተናል፡፡
ለተጎጂ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደርስ እርዳታ መንገድ ላይ እያዘረፈ በጌድዮ ህዝብ ርሀብና ሰቆቃ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ ይህ ብቻ ሳይበቃ ለችግር የተጋለጡ የህበረተሰብ ክፍሎች ጉዳት ደረጃ እንዳይታወቅ ሲያሻጥር ታዝበናል፡፡
በስልጣን ላይ ለመቆየት እና ቀጣዩን ምርጫ ለማሸነፍ ከማሰብ ብቻ በመነጨ ስግብግብነት ቀን የህግ ሽፋን ለሊት የዘራፊና ነፍሰ ገዳይ ቡድን እየተጠቀመ የሌላ ብሄር ተወላጅ ኢትዮጵያውያንን ከክልሉ ማሳደድና ማፈናቀልን ህጋዊ ተግባር አድርጎታል፡፡
የክልሉን ወጣት ወደ ስራ የሚያስገቡ መልካም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እድሎችን በሙስና፣ በአሻጥር አመጽ የባለሀብት ንበረት አውድሞ ባለሀብት በማሸሽ በማባከኑ የደረሰበትን ውድቀት ለመሸፋፈን ውጫዊ ጠላት እየፈለገ የኦሮሞ ወጣቶችን አለመረጋጋት ውስጥ እያባከነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁን ሠዓት ክልሉ ከሱማሌ፣ ከአማራ፣ ከቤንሻንጉል፣ ከሲዳማ ፣ከጋንቤላ፣ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች ሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ህዝቦች ጋር ያለው ማህበራዊ መስተጋብር በኦዴፓ ስሜታዊ እና ልፍስፍስ አመራር በስጋት፣ በቅራኔ እና በጥርጣሬ የሚታይ ነው፡፡
በከፍተኛ ደረጃ ለሀገሪቱ ኦኮኖሚ ለክልሉ ወጣጥ እና ቡና አብቃይ ገበሬ ሊጠቅም የሚችል የቡና ምርት በክልሉ ካሉ የከተማ ደላሎች ጋር በየመሸታ ቤት እየተደራደሩ በየድንበሩ የማሸሻ መረብ የሚዘረጉ የአንድ ሳምንት አስመሳይ የዛፍ ላይ ሀቀኞች ናቸው፡፡
ፍትህን በሁለትና ሶስት ሺህ ብር የሚቸረችሩ፣ ህጋዊና ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት ካለገንዘብ የማይንቀሳቀሱ የፍትህና የፖለቲካ ስርአት ክልሉ ላይ ተንሰራፍቷል፡፡ ለሚቆርጡት ስጋ እና ለሚጠጡት ውስኪ እንጂ ለእውነት ደንታ የሌላቸው የራሳቸው የትግልም ሆነ የፓርቲ ዲሲፕኪን የሌላቸው ሆዳም ስብስብ ሆኗል፡፡
የነፍስ አባታቸው እንዳለው በርግጥም ወለጋ ላይ ከተዘረፈው አስራ አንድ ባንክ ጀርባ ኦዴፓ እራሱ እንዳለ ፍንጭ እየወጣ ነው፡፡ የክልሉ ፖሊስ ፣ መረጃና ደህንነትም ሆነ ፌደራል ፖሊስ በኦሮሚያ ባንኮች  ዝርፊያ የፈጸሙ ግለሰቦች እንዴት እስካሁን ተሰወሩባቸው ብለን ስንጠይቅ መልሱ ገንዘቡን የተከፋፈሉት አፋላጊ ሆነው እንዳለ ይጠቁመናል፡፡
አዲስ አበባን ውጬ ልተርተር  ያለው ኦዴፓ በዚህ ታሪካዊ እና ሀላፊነት የጎደለው ስህተት ምናልባትም የክልሉን ህዝብ ለክፍፍል ብሎም ኦሮሚያን ለመፍረስ የሚዳርግ የፖለቲካ ውድቀት ወደ ኦሮሞ ልጆች ቤት እየጠራ ያለ ሞኝ ሆኖ ተግኝቷል፡፡
ክልሉ ያለው ውድ እና የከበሩ ማእድናት በአግባቡ ለጥቅም እንዳይውል  ከኮንትሮባንድ ነጋዴ ጋር ተመሳጥረው በቦርደር የሚያሸሹ ኦዴፓ መዋቅር ውስጥ ያሉ አባላት ናቸው፡፡ ለምሳሌ የጉጂ ወርቅና ኤመራልድን ጨምሮ በኬንያ እና በሱማሌያ በኩል በየእለቱ የሚወጣው ማእድን ከጀርባ የሚዘወረው በኮንትሮባንዲስት ኦዴፓዎች እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
አዲስ አበባ ላይ የሚሰጠው የነዋሪነት መታወቂያ ለንጹህ የኦሮሞ ልጆች ሳይሆን ይህንኑ የኮንትሮባንድ፣ የማፊያ፣ የድለላ እና የመሸታ ቤት ወዳጅነትን መረብ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ይህን መታወቂያ ካርድ በማይገኝበት አድራሻ ማን ለምን ጉዳይ  ይጠቀምበት የእነሱ ጉዳይ አይደለም፡፡
ስለሆነም አለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀር ከለማ መገርሳ ጀምሮ ያሉ እንደ አዲሱ ረጋሳ እና ታዬ ደንደአ አይነት ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በሰው ልጅ ላይ በሚፈጸም ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሊጠየቁ ይገባል፡፡ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊትም ሆነ የፌደራል ፖሊስ ሀገሪቱን እና ዜጎችን የመጠበቅ እንጂ ወንበር የያዘ ወንጀለኛን  በዝምታ የማየት  ተግባር እንዳልተሰጣቸው ከትናንቱ ስህተት ተረድተው አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰብ ግድ ነው፡፡ መሬትም፣ ሀገርም፣ ክልልም ሰው ልናኖርበት እንጂ ሰው ልናሳድድበት አልተሰጠንም፡፡
Filed in: Amharic