>

ዩኒቨርሲቲው በድጋሚ "ለጸጋዬ አራርሳ የዶክትሬት ዲግሪ አልሰጠሁም!፣ ሰራተኛዬም አይደለም!" አለ!!! (አበበ ገላው)

ዩኒቨርሲቲው በድጋሚ “ለጸጋዬ አራርሳ የዶክትሬት ዲግሪ አልሰጠሁም!፣ ሰራተኛዬም አይደለም!” አለ!!!
አበበ ገላው
የሜልበርን ዩኒቨርሲቲ (University of Melbourne) ከጥቂት አመታት በፊት ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ያሰናበተውን ተማሪ አቶ ጸጋዬ አራርሳን በማስመልከት በሰጠው መግለጫ ግለሰቡ ጀምሮት የነበርውን ትምህርት ማቋረጡን፣ ከታዋቂው የዩኒቨርሲቲው የህግ ት/ቤት (Melbourne Law School) PhD አለመቀበሉንና በዩኒቨርሲቲውም እንደማይሰራ በድጋሚ አረጋግጧል።
ምንም እንኳን ዩኒቨርሲቲው ከጥቂት ወራት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ የግለሰቡን ዶክትሬት ዲግሪም ይሁን ቅጥር በይፋ ባወጣው መግለጫ አላውቅም ቢልም አቶ ጸጋዬ አራርሳ ባልተለመደ ሁኔታ እሳካሁን ድረስ በአደባባይ የዩንቨርሲቲው ምሩቅ እና በዩኒቨርሲቲውም ተቅጥሮ እንደሚያስተምር ከመዋሸት አልተቆጠበም።
በጉዳዩ ላይ ለውጥ ካለ ማብራሪያ እንዲሰጡበት የሜልበርን ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ዲን የሆኑትን ፕሮፌሰር ፒፕ ኒኮልሰንን ከጥቂት ቀናት በፊት በኢሜይል ጥያቄ አቅርቤላቸው ነበር። ፕሮፌሰሯ ጉዳዩ ተጣርቶ ምላሸ እንዲሰጥ አደርጋለሁ ባሉት መሰረት የዩኒቨርሲቲው ቃል አቀባይና ከፍተኛ የሚድያ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት  ኤማ ሰን ዛሬ ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚሁም መሰረት አቶ ጸጋዬ ትምህርቱን ማቋረጡን፣ ከዩኒቨርሲቲውም የዶክትሬት ዲግሪ አለማግኘቱንና ተቀጥሪም አለመሆኑን በድጋሚ ቃል አቀባይዋ አረጋግጠዋል። በጉዳዩ ላይ አቶ ጸጋዬ አስተያየት እንዲሰጥበት ላቀረብኩት ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በዘር ግጭት ቅስቀሳ የሚከሱት አቶ ጸጋዬ፣ እኤአ በ2003 በአምሰተርዳም ዩኒቨርሲቲ (University of Amsterdam) የዶክትሬት ትምህርት ፕሮግራም ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ከጥቂት አመታት በሁዋላ በተመሳሳይ ሁኔታ ሳይጨርስ ማቋረጡ ታውቋል።
—-
አቶ ጸጋዬ ሆይ፣ ትግል ከራስ ይጀምራል ይባላል። ከሁሉም በላይ አቶ ወይንም ዶክተር መሆንህን የማታውቅ ከሆነ የምትሰብከውና የምታምታታውን ምስኪን የፖለቲካ ምእመናን ልትታደግ አትችልም።
Mr. Ararsa, Please don’t lie to your own self so that you will start telling truth to others. You cannot award yourself a PhD. You need to have the courage to liberate yourself from self-deception.
If you don’t know who you really are, why do you bother about the affairs of others? As Virginia Wolfe says, “If you do not tell the Truth about yourself you cannot tell it about other people.” This is true because you can never have the moral authority to blame others for their lies and misdeeds.
Filed in: Amharic