>

"ገጄራ :ሜንጫና ሽመል ይዞ  የሚትገለገልን መንጋ በሀሳብ እና በብእሩ ብቻ ያንቀጠቀጠ ጀግና!!!" (ቬሮኒካ መላኩ)


“ገጄራ :ሜንጫና ሽመል ይዞ  የሚትገለገልን መንጋ በሀሳብ እና በብእሩ ብቻ ያንቀጠቀጠ ጀግና!!!”
ቬሮኒካ መላኩ
እስክንድር ነጋ  የአዲስአበባ ህዝብ ባልሰለጠኑና የከተማ ስነልቡና መጋኛ በሆነባቸው ባርባሪያንስ  ተስፋው በጨለመበት ወቅት እንደ  ታላቁ ኮንፊዩሸስ፤ “ሁሌ ስለ ጨለማ ከማውራት አንዲት ሻማ ማብራት ይበልጣል” በማለት የአዲስ አበባን ህዝብ ያነቃነቀ ኬኛዎችን ደሞ ያርበደበዴ እናቱ የወለደችው ነብር ነው ።
.
ፍሬደሪክ ኤንግልስ ወዳጁና ጓዱ ስለነበረው ካርል ማርክስ በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ላይ ሲናገር  ” The best hated man  ብሎት ነበር አሉ ። ማርክስ ግን በወቅቱ በተፈጠሩም ሆነ በኋላ በተነሱ ትውልዶች ዘንድ   The best loved man ብቻ ሳይሆን   The most genius man መሆኑ ተረጋግጧል።
የብራ መብረቅ የሆነው ታላቁ እስክንድር ለስግብግቦቹ ኬኛዎች The best hated man ሲሆን ለአዲስአበባ ህዝብና ለ85 ብሄር ብሄረሰቦች ደሞ”  The best loved man” መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል።
.
ማንደላና ጋንዲ፤ አንዲት ጥይት አልተኮሱም፣ ጎራዴ አልመዘዙም፣ ጦር አልሰበቁም፡፡ ሃሳባቸው ግን አለምን አስገብሯል፡፡ ትልልቅ ጦረኞች ሲንበረከኩ፣ እነሱ አሸንፈዋል፡፡ ትልልቅ ጦረኞች ከታሪክ መስመር ሲሰረዙ፣ እነሱ ታሪክ ሆነዋል፡፡  ታላቁ እስክንድር ገጄራ :ሜንጫና ሽመል ይዞ  የሚትገለገል መንጋ በሀሳብ እና በብእሩ ብቻ ያንቀጠቀጠ ጀግና ነው።
በነገራችን ላይ ባልድራስን ከፈጠሩት ጀግና ሌላው መረሳት የሌለበት ስንታየሁ ቸኮል ነው ። ስንታየሁ ቸኮል  ጋር በብዙ ነገር ባልስማማም የወንዶች ቁና የሆነ ጀግና መሆኑን ግን አልክድም ። ስንታየሁ ቸኮል ለማንም ቦቅቧቃ ግንባሩን የማያጥፍ አንበሳ ነው ። የዜግነት ፖለቲካ የሚያራምዱ ፓርቲዎች አምቡላውንና እብቁን ሁሉ ከሚሰበስቡ እንደ ስንታየሁ ቸኮል አይነቱን የማደራጀት አቅም ያለው ጀግና አባል ቢያደርጉ ኖሮ ስንቱን ወንዝ በተሻገሩ ስንቱን ዳገት በወጡ ነበር ። ለማንኛውም አዲስ አበቤ ውድ ልጆችህን ለደቂቃም ቢሆን ሳታሸልብ ጠብቃቸው”።
Filed in: Amharic