>

አትሳሳቱ! አታሳስቱንም! አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ከተሞችም የተለየች ነች! (ጌታቸው ሽፈራው)

አትሳሳቱ! አታሳስቱንም! አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ከተሞችም የተለየች ነች!
ጌታቸው ሽፈራው
ትንሽ ቆይተው ደግሞ “አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዱባይ፣ ዋሽንግተን፣ ካርቱም፣ ሞቃዲሾ ሄዶ እንደሚሰራውና እንደሚኖረው የሁሉም መኖርያ ነች” ይሉናል!
በዚህ ንግግር አዲስ አበባ እንደ ኦሮሚያዋ ከተማ ነቀምት ዜጎች ሄደው የሚኖሩባት የኦሮሞ ከተማ ነች ነው የተባለችው። ጭራሹን “ፊንፊኔ የኦሮሞ ናት”  የሚሉት ይሻላሉኮ። ስግብግብነታቸውን አይደብቁም!
አዲስ አበባ ለአዲስ አበባውያንም ለኢትዮጵያውያንም ከነቀምትም፣ ከጅማም፣ ከመቀሌም የተለየች ነው። ዋና ከተማ እና የክልል ከተማም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠፋው ይመስላቸዋል።
ለመረጃ ያህል ጠ/ሚ “እኔ ወለጋ ብሔድ ይገድሉኛል” ብሎ ነበር።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳይመጣባት የምትባለው ነቀምት ዜጎችማ ሰርተው መኖር እንደማይችሉ ግልፅ ነው። አዲስ አበባ ግን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳትሆን ለአፍሪካውያንም ልዩ ነች።
ነቀምትን ተውት! አዲስ አበባ ለአፍሪካውያን ከካይሮ የተለየች ነች። ምክንያቱም መዲናቸው ነች። ከመቀሌ ጋር አታወዳድሯት። አዲስ አበባ ለአፍሪካውያን ከናይሮቢ የተለየች ነች። ምክንያቱም አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና ነች። አዲስ አበባን ከባሕርዳር ጋር አታወዳድሯት። ለአፍሪካውያንም ብቻ ሳይሆን ለዓለም እንኳ ከካርቱምም፣ ከኪጋሊም፣ ከጁሃንስበርግም ከካርቱምም፣ ከካይሮም…… የተለየች ነች። ምክንያቱም የአፍሪካ ዋና ከተማ ነች!
አዲስ አበባ ለኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ ከተሞች የተለየች ነች። አዲስ አበባ ለአፍሪካውያንም ለቀሪው አለምም ከአፍሪካ ከተሞች ሁሉ የተለየች ነች! አንድ ኢትዮጵያዊ ነቀምት ሄዶ ሲኖርና አዲስ አበባ ሲኖር እኩል አይደለም። ምክንያቱም ነቀምት የጅማው አብይ እንኳ ለመርገጥ የፈራው የወለጋ ከተማ ነች። አዲስ አበባ ግን የነቀምትም፣ የጅማም፣  የሀዋሳውም፣ የባህርዳር፣ የመቀሌው………የቀሪው ኢትዮጵያውያንም ዋና ከተማ ነች!
 በተመሳሳይ አንድ ናይጀሪያዊ ካይሮ ሲኖርና አዲስ አበባ ሲኖር እኩል አይደለም። ካይሮ የግብፅ ዋና ከተማ ናት። አዲስ አበባ ግን የናይጀርያውያን፣ የአፍሪካውያንም ዋና ከተማ ነች። አንድ አውሮፓዊ ካርቱም ሲኖርና አዲስ አበባ ሲኖር እኩል አይደለም። ምክንያቱም ካርቱም የሱዳን ዋና ከተማ ስትሆን አዲስ አበባ የሱዳናዊያን ጨምሮ የአፍሪካውያን ዋና ከተማ ነች!
Filed in: Amharic