>

ልዩ ጥቅም ልዩ ጥቅም... እረ ደነቆርን?!?  (ቬሮኒካ መላኩ)

ልዩ ጥቅም ልዩ ጥቅም… እረ ደነቆርን?!? 
ቬሮኒካ መላኩ
~እነዚህ “ሰወች” ለአዲስ አበባ ሁሉንም ነገር እነርሱ ብቻ የሚያቀርቡላት አስመሰሉት እኮ፡፡ ሺ ጊዜ “ልዩ ጥቅም፡ ልዩ ጥቅም”  እያሉ ያደነቁሩን ያዙ፡፡
~የአፋር ጨው እየዛቀ ፣ የሶማሌን ነዳጅ አንቧቆ እያዬ ፣ የቤንሻንጉልን እምነ በረድ ና ወርቅ ዝም ብሎ እያፈሰ ፣ ከአባይ ና ጣና በረከት የሚገኘውን የሕዳሴ ግድብ ለአህጉር አቀፍ ገበያ በመልቲ ሜጋ ዋት ሀይል ለመሸጥ እየተደራደረ ፣ የከፋን ፡ ጌዲዮን ና ይርጋ ጨፌን ቡና አፍሶ አየሸጠ ፣ ከቅዱስ ላሊበላ ፣ ከጣና ገዳማት ፣ ከአክሱም ሀውልት ፣ ከፋሲል ግምብ ፣ ከሰሜን ብሄራዊ ፓርክ ና ዳሽን  ተራራ ፣ ከኤርታሌ ፣ከቂያ…የሚገኘውን የቱሪት ገቢ እንዳሻው  እየዛቀ ዝም ያለው….ኦሮምያ ምን የተለዬ አቅርቦት ኖሯት ነው “የልዩ ጥቅም” ዳረጎት አፋሽ ምትሆነው ?  አንዳንዴማ ግራና ቀኙን ማስተዋል ይበጃል እኮ ጓዶች፡፡
~ ግዴላችሁም  “ጥቅመኞች”  ሆይ ይህ ወንዝ የማያሻግር እና ውሃ የማይቋጥር ትርክታችሁን አቁሙ ና ሁሉም ዜጋ ና ህዝብ እኩል ተጠቃሚ የሚሖንበትን አስተሳሰብም ሆነ ስርአት ዘርጉ/እንዘርጋ፡፡
~ነገሩ እናንተ “ልዩ ጥቅም” የሚል የልጅ እራት አቀረባችሁ እንጅ ትልቁ ህልማችሁ  የናንተ ያልሖነችዋን አዲስ አበባን በሴራ ለመውረስ ነው፡፡
~ ግዴላችሁም አዲስ አበባን  ለባለቤቷ ተዋት ፡፡ የጅል ቅዤታችሁንም  አንሱ /እርሱ፡፡ ካለያ ይህ በስስት የተነቀረ የ ሁሉም  “ኬኛ” እነቶፈንቶ ወደ ሁሉም “እንጅሩ” እንዳያደርሳችሁ ፍሩ፡፡
Filed in: Amharic