>

ለውጡ እንደጤዛ ነው ታይተው የሚጠፉ ችግሮችን ያመጣል - ዝናቡን ፈርተን ክረምቱን ማስቀረት ግን አይሆንልንም!!! (ጠ/ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ )

ለውጡ እንደጤዛ ነው ታይተው የሚጠፉ ችግሮችን ያመጣል – ዝናቡን ፈርተን ክረምቱን ማስቀረት ግን አይሆንልንም!!!
ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ
በድልነሳ ምንውየለት
– በዚህ ዓመት በሄድኩበት የደገፋችሁኝ፣ ሰኔ 16 ቀን ተደግሶልኝ የነበረውን ሞት ተሻምታችሁ በመውሰድ የሞታችሁልኝ፣ የቆሰላችሁልኝ፣የደማችሁልኝ ወገኖቼ  እናንተ ያለኔ መኖር ትችላላችሁ እኔ ግን ያለ እናንተ ምንም ነኝ።
– በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስአንጀለስ፣ በሚኒሶታ፣ በፍራንክፈርት በዚያ ብርድ ሙሉ ቀን መሪያችን ይመጣል፤ እናደምጠዋለን ብላችሁ ከነበራችሁበት ተሰባስባችሁ በአንድነት ኢትዮጵያ ብላችሁ ያዜማችሁ በሙሉ እናንተ ያለኔ መኖር ትችላላችሁ እኔ ግን ያለ እናንተ ምንም ነኝ።
– ኢትዮጵያዊነት ዘመም ካለበት ቀና እናድርገው የሚለውን ፕሮጀክት አብረን ስንጀምር ኢትዮጵያዊነት ታክቲክ ወይም ቴክኒክ መሆን አይችልም።
– ለውጡ እንደጤዛ ነው ታይተው የሚጠፉ ችግር ፈጣሪዎች ያመጣል፤ ነገር ግን ዝናቡን ፈርተን ክረምቱን ማስቀረት አይሆንልንም።
– ለውጥ የሚከብደው ባልተለወጠ ባህል ውስጥ ሲሆን ነው፤ ለውጥ የሚያስቸግረው ባልታደሰ ተቋም ሲጀመር ነው።
– ባለፈው አንድ አመት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የነበረበትን አደገኛ አደጋ ለመከላከልና ፕሮጀክቱን ለመጨረስ የሚያስችል ቁርጠኛ አመራር ሰጥተናል።
– ባለፉት 7 ወራት ብቻ 13 ቢሊዮን ዶላር አምጥተናል።
– ድሉን በጋራ እንዳመጣነው ሽንፈቱንም በጋራ ልንቀበለው ይገባል፤ ከሁሉም የከፋው ደግሞ የወረስነው የሴራ ፖለቲካና መጠራጠር ነው።
– ታላቅ ሀገር ይዘን ታናሽ እንዳንሆን፤ ጀግና ህዝብ ይዘን ሰነፍ እንዳንሆን፤ በአንድ ማዕድ ማብላትና መብላት ለአለም ያስተማረ ህዝብ ጥላቻና ስድብብን፣ መፈናቀልና መገዳደልን ለሌላው አለምና በተረጋጋ ሁኔታ ወደመኖር የመጣውን አፍሪካ የሚያስተምር እንዳይሆን ኢትዮጵያዊውያን በአንክሮ ልንመለከተው ይገባል።
Filed in: Amharic