>

¨ይድረስ ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ጳጳሳትና መምህራነ ወንጌል¨ ( መ/ር ታሪኩ አበራ )

ቤተ ክርስቲያንን በቦንብ አወደሟት፣ 
 ዘረፉት፣ አቃጠሏትም!!! 
 መ/ር ታሪኩ አበራ
የኤፍራታና ግድም ወረዳው በቦንብ የተቃጠለው የቤተ ክርስቲያንን እንባና የዐይን እማኞችን ምስክርነት የሚያሳይ ቪድዮ ተያይዟል!!
~ ስደት ~ ልቅሶ ~ ሞት~ በመጨረሻም ድልና ትንሣኤ!!
 
   *ይድረስ ለኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ጳጳሳትና መምህራነ ወንጌል* 
**በግብፅ እና ሳውዲ የሚደገፈው IFLO /ኢስላማዊ የኦሮሞ  ነፃ አውጪ ግንባር/ በቤተክርስቲያን ላይ ጦርነት ጀምሯል።**
 
**ባለማወቅ ከፀረ ቤተክርስቲያን ኃይሎች ጋር የተሰለፈውን የኦሮሞ ክርስቲያን በሚገባው ቋንቋ እያስተማራችሁ ከጥፋት መንገድ መልሱት**
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሦስት ሺ ዘመን ታሪክ ያላት ከዘመነ ብሉይ  ጀምሮ አሁን እስካለንበት ዘመነ አዲስ ድረስ  እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ  ስትማለክ የቆየች፣ትውልድን በምግባርና በሃይማኖት እያነጸች ያለች  ታላቅ የሃይማኖት ተቋም ነች።
ቤተክርስቲያኒቱ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ጎንለጎን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ጸንታ እንድትቆም አዕምሯዊና ቁሳዊ አንጡረ ሀብቷን  በማፍሰስ ትውልድና ታሪክ መቼም  የማይረሳውን ታላቅ የታሪክ አሻራ አስቀምጣለች።ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ብራና ዳምጠው፣ቀለም በጥብጠው፣ብዕር ቀርጸው ከቤተክርስቲያኒቱ ባገኙት ጥበብ  ዕውቀትን ለትውልድ በማስተላለፍ ኢትዮጵያውያን በራሳችን  ፊደልና የዕውቀት ብርሃን ከዓለም እኩል እንድንራመድ አድርገውናል።ከዚህም ባሻገር መንፈሳውያን አበው  ከመንፈስ ቅዱስ ባገኙት ጸጋ ዓለምን የሚያስደምም የኪነ ጥበብ ትሩፋቶችን በተለያየ ዘርፍ አበርክተው ኢትዮጵያን በክብር ማማ ላይ ከፍ አድርገዋታል።ዛሬም ድረስ በሥነ ሕንጻ፣በሥነ ጽሑፍ፣በሥነ ስዕል፣በሥነ መለኮት፣በሥነ ከዋክብትና በሌሎችም ዘርፎች ቤተክርስቲያኒቱ ለኢትዮጵያ ያበረከተችው ሀገራዊ አስተዋጽኦ ኢትዮጵያን የቱሪዝም መስዕብ እንድትሆንና የብዙ ተመራማሪዎች ቀልብ ኢትዮጵያን እንዲመኝ አድርገዋታል።
በዘመናችን ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ በሚባለው ቱሪዝም ሀገራችን ከፍተኛ የኢኮነሚ ተጠቃሚ እንድትሆን እያደረገች ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነች።
ቤተክርስቲያኒቱ ጥንትም ሆነ ዛሬ የኢትዮጵያን አንድነትና ብልጽግና ከፍ ለማድረግ በብሩህ ራዕይ ስለምትተጋ ይህ የኢትዮጵያ ሕብረትና ፍቅር የማያስደስታቸው የውጭ ጠላቶች በሀገር ውስጥ የሚፈጠሩ አንዳንድ አለመግባባቶችን እየጠበቁ በወንድሞች መካከል የከረረ ጸብና ጦርነት እንዲነሳ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያ ሁሌም ኋላቀርና ደሃ ሀገር ሆና እንድትቀር ትናንትም ዛሬም እየሰሩ ይገኛል።
በቅርቡ እንደምንመለከተው ሀገራችን ወደ ተረጋጋ ሰላምና ልማት ፊቷን ባዞረችበት ወቅት በብሔር መካከል የሚነሱ ጥቃቅን አለመግባባቶች መልክና ይዘታቸውን ቀይረው ወደ ከፋ ግጭት እንዲሸጋገሩ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው። በተለይም ራሱን ኢስላማዊ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ብሎ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ክንፍ  በግብጽና  በሳውዲ በሚገኙ የእስልምና አሸባሪና አክራሪ ቡድኖች በሚደረግለት የገንዘብና የቁሳቁስ ዕገዛ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የመጀመሪያ ዓላማ አድርጎ የተነሳው የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በከፍተኛ አደጋ ማጥፋት ነው።ለዚህም  ነው በተለያየ ጊዜ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ምንም ያላደረገችውን ሰላማዊ  ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመ ያለው።
አባቶቼ ጳጳሳት፣ካህናትና ወንድሞቼ መምህራነ ወንጌል እባካችሁ ዝምታውን ሰብረን በቤተክርስቲያን ላይ የተከፈተውን የጦርነት አዋጅ ጠንክረን እንቃወም ፣አባቶቻችን የደም ዋጋ ከፍለው በብዙ ድካምና መከራ ያወረሱን የቤተክርስቲያን ክብርና አንጡረ ሀብት በዲያብሎስ መንፈስ በሚመሩ አሕዛብ ሲደፈር ዝም ብለን አንመልከት። በተለይም የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆናችሁ አባቶችና መምህራነ ወንጌል ባለማወቅ በኦሮሞ ብሔርተኝነት ስም  ከቤተክርስቲያን ጠላቶች ጋር የተሰለፈው ክርስቲያን ቆም ብሎ እንዲያስብና በህዝበ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት፣ በቤተክርስቲያን ላይ የሚፈጽመውንም ግፍ በአስቸኳይ እንዲያቆም ይልቁንም በክርስቶስ ደም ሕይወትና ድኅነት ላገኘባት ቤተክርስቲያን ከለላ በመሆን በአክራሪ ሙስሊሞች የሚመራውን ኃይል እንዲከላከል በቋንቋቸው ተስተምሩ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።
የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆናችሁ  ክርስቲያኖች እባካችሁ እናንተም በጣም አስተውሉ ክርስትና ከብሔርተኝነት በላይ ነው።ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ ቤተክርስቲያንን እያቃጠለ ክርስቲያኖችን ከሚገድል የአጋንንት ጭፍራ ጋር  አብራችሁ አትሰለፋ ይልቁን አብዝታችሁ ተቃወሙት ክርስቶስ ሕይወቱን በመስቀል ላይ ሰጥቶ ከዘለዓለም ሞትና እርግማን ነጻ አውጥቶ ለመንግሥተ ሰማያት ክብር በደሙ እናንተን ያጨበትን መለኮታዊ ውለታ ከንቱ አታድርጉ።ለዝህች ለምታልፍ ከንቱ ዓለምና ነውረኛ ምድር ብላችሁ ዘለዓለማዊ ቅጣትና  ፍርድ በነፍሳችሁ እንዳይጠብቃችሁ በጣም በማስተዋል ተጓዙ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንደ ወንዝ ዳር ሳር ነች ወጀብና ማዕበል ፣ጎርፍና ቋጥኝ በላይዋ ላይ እያጓራ ያልፍባታል የጠፋች መስላ እንደ ሳሩ አንገቷን ሰብራ ዝም ብትልም የጽድቅ ፀሐይ ሲወጣ ዳግም በክብር ቀና ብላ እንደ ለምለም ሳር ለሀገርና ለሕዝብ ዳግም ውበት ሆና ትቀጥላለች ።
#ኦሮሞ ሙስሊም ወገኖቻችን እናንተም በጣም  አስተውሉ በጽንፈኞችና በአክራሪ የውጪ ኃይል በሚታገዙ የጥፋት ኃይሎች መንገድ አትሂዱ። ድሃው ክርስቲያን ወገናችሁ እንደናንተው ለፍቶ አዳሪ ነው።ልጁን እየገደላችሁ ቤቱን እያቃጠላችሁ ግፍና መከራን ለልጆቻችሁ አታስቀምጡ የሰማይ አምላክ በእናንተና በዘራችሁ ላይ በቁጣ በትር ይፈርዳል።ቢዘገይም  እግዚአብሔር በእውነት ይፈርዳል ዝምታው የንስሐ ዕድሜ እየሰጣችሁ መሆኑን አትርሱ።
ቤተክርስቲያን አልበደለቻችም  አትንኳት ስለ ሀገር ሰላምና ስለ ሕዝብ ፍቅር ጠዋት ማታ በምትጸልይ ቤተክርስቲያን ላይ እሳት ለምን ትለቃላችሁ ? ምንስ በደለቻችሁ? ጾም አዳሪ ካህናቷን አትደሉ፣የዋሕና ምስኪን ምዕመኗን አታሰቃዩ ።ትናንት አብሯችሁ እጁን እያጣመረ በየአደባባዩ የጮኽው እውነተኛ ክርስቲያን  ወንድማቹ ላይ ዛሬ ኦሮሞ አይደለህም ብላችሁ በጥይት አትህደሉት ቀና ብላችሁ ፈጣሪን ተመለከቱ በእናንተና በትውልዳችሁ ላይ ፍርድ ይመጣል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግራኝ መሐመድ ያልቻላት፣ዮዲት ጉዲት ያላጠፋቻት፣ጣሊያን ያልተቋቋማት የሚጠብቃት እግዚአብሔር ስለማይተዋት ነው።ጠላቶቿ ሁሉ እንደ ጢስ ተነው እንደ ጉም በነው ጠፍተዋል ቤተክርስቲያን ግን ዛሬም እንደ ብርሃን ደምቃ ታበራለች።ኦነግና ሠራዊቱ ነገ ዶግ አመድ ሆኖ ይጠፋል በክርስቶስ ደም የተመሰረተችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ግን ሕያው ሆና በክብር ትቀጥላለች።ኋላ በእግዚአብሔር ሚዛን ቀለን  እንዳንገኝ የቤተክርስቲያን አባቶችና መምህራነ ወንጌል ሕዝቡን እያስተማርን ከጥፋት መንገድ እንመልስ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ሰላምንም በምድራችን ያብዛ።
Filed in: Amharic