>

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!!! ኤርሚያስ ለገሰ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

 

ዛሬ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ከተጫኑበት የአዲስ አበባ ህዝብ ጫንቃ ላይ መውረዳቸው ተሰምቷል። ይሄ ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጥ የሚችል ነው። የአዲስአበቤን ስር ነቀል ጥያቄ ግን አይፈታውም። ከፓሊስ ተቋሙ አኳያ የአዲስአበቤ ለድርድር የማይቀርበው ጥያቄ፣

1ኛ: አዲስ አበባ የራሷ የፓሊስ ኮሚሽን ይኑራት። የከተማው ፓሊስ ለሉአላዊ ባለቤቱ ይመለስ።

2ኛ: ከየክልሉ በፓርቲ ውክልና ተመልምሎ የመጣው ፓሊስ ወደመጣበት ይመለስ።

3ኛ: አዲስ አበባ በራሷ የሚተዳደር የፓሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ይኑራት።

4ኛ: የአዲስ አበባ የፓሊስ አባላትም ሆነ ተመልማዬቹ በሙሉ አዲስአበቤ ይሁኑ። በምልመላ መስፈርቱና ሂደቱ አዲስአበቤ በሙሉ ቀጥተኛ ተሳታፊ ይሁኑ።

( በድጋሚ ” አዲስአበቤ” ማለት ዘር ቀለም ሳይለይ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጐች ሆነው ኑሮአቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ናቸው።)

እነሆ ከስምንት ወር በፊት (Sep25, 2018) ተፅፎ ድሬ ቲዩብ ያነበበውን መጣጥፍ በድጋሚ ተጋብዛችኃል።

Filed in: Amharic