>
5:13 pm - Monday April 19, 0202

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አርፈዋል!

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አርፈዋል!!!
መሳይ መኮንን
በጀርመን አገር በሕክምና እየተረዱ ነበር።
..
የኢፌዲሪ ፕ/ት በመሆን ያገለገሉት፣ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘውን ሕገ–መንግሥት ያጸደቁት፣ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት፣ በመንግሥት የጡረታ መብታቸው ተገፎ ከፍተኛ ስቃይና መከራ የተቀበሉት ከለውጡ በኋላም የኦሕዴድ/ኦዴፓ አመራር ሊረዳቸው ቃል ገብቶላቸው ድርጅቱ ቃሉን እንዳልጠበቀ በምሬት የተናገሩት የኢትዮጵያን የግማሽ ክፍለ–ዘመን ምስቅልቅል ፖለቲካ የተካፈሉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አርፈዋል።
አንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን ”ቁርጥ መንግስቱን መሰልከኝ” ብለው ፊት ለፊት ከተናገሩበት አጋጣሚ አንስቶ፡ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የነበራቸው ሚና፡ በኋላም ምሽግ ውስጥ የተፈጠሩ የብሄርተኞችን ትርክት በማርከስ እውነተኛ የኢትዮጵያ ታሪክን በአደባባይ በመመስከር የሚታወቁ ታላቅ ሰው ናቸው።
 ዶ/ር ነጋሶ “ዳንዲ ነጋሶ –የነጋሶ መንገድ” በተሰኘ ግለ–ታሪካቸውን በሚተርክ መድብል በሽግግሩ ዘመን የአማራ ሕዝብ የደረሰበትን ስደት፣ እንግልት፣ መፈናቀል፣… ወዘተረፈ ሰንደው አስነብበውናል።
ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት አማካኝ ሰው ማጣቷ ጥሩ አይደለም። ልዩነትን የሚሰብኩ፡ ባልተፈጠረ ታሪክ የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ውስጥ ለመክተት ከየአቅጣጫው ጩኸቱ በበረከተበት በዚህ ዘመን ዶ/ር ነጋሶን ማጣት ከባድ ነው።
* እውነት ለመናገር ነጋሶ ከኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃን መካከል የአኖሌን ትርክት በጥፊ ያጮሉና ተስፋዬ ገ/አብን ” ከኦሮሞ የበለጠ ኦሮሞ ነኝ ባይ መርዛማ ” በማለት በተደጋጋሚ የገሰፁ ሰው ነበሩ።
 
* ሲጀመር_ቱለማው ጐበና እንጂ ምኒሊክ ራሱ አርሲ አልዘመተም።
 ጐበና ጡት ቆረጠ ለማለት ደግሞ ታሪክ ማስረጃ የለንም። ዶክትሬት ዲግሪዬን (PHD) የሰራሁት የኦሮሚያ ታሪክ ላይ ነው።
     አንድም የታሪክ ማስረጃ የሌለበት ወሬ ነው፣ መነሻውም  ከንቱ ጥላቻ ነው ባይ ነኝ።
                 ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
        የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚደንት
አገሬ እና ህዝቤ እንዲህ አይነት የእውነት መስካሪ ነው ያጡት…

            ነ ፍ ስ   ይ ማ ር!

Filed in: Amharic