>
10:28 am - Wednesday December 7, 2022

በትግላችን መዳረሻ ነፃነትን ለማምጣት:-  ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የምር"አዙሪቱ"ገብቷቸዋል።  (አቢይ ኢትዮጵያዊ..)

ትግላችን መዳረሻ ነፃነትን ለማምጣት:- 

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የምር”አዙሪቱ”ገብቷቸዋል። 

አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

ሳይገላገለው ሽሉን በሆድ ይዞ፤⟨²⟩
እሚረዳው አጥቶ ብቻውን ተክዞ፤
ተክዞ ተክዞ፤ስንቱን በሆድ ይዞ፤
የወገቡን እሳት ካፎቱ ላይ መዝዞ፤⟨²⟩
ጠጥቶላት ሞተ ክንዱን ተንተርሶ
አያሳዝንም ወይ ኽርርርርር….
ኽርርርርርርርርር….
ዝግባ የሚያሳክለው አንዲት ፍቅር አጥተን፤
ዝግባ የሚያሳክለው አንድነትን አጥተን፤
ከፊት የነበርነው ከሰውኋላ ቀርተን፤
አናሳዝንም ወይ?????….
ኽርርርርርርርርር…. (ከቴዲ አፍሮ ዘፈን የተወሰዱ ስንኞች) 
   የእነዶ/ር ዐቢይ+ለማ “ቲም”የፋሺሽት-ወያኔ ከተጨማለቀበት የሕዝብ ደም ውስጥ ተንፈራግጠው እና የደረቀ ደም አንኳሩን ፈንቅለው በመውጣት:- የጨቀየውን የንፁሃን ደም እያዩ ግፋቸውን በዐይነ-ህሊና በመሳል በፀፀት ስሜት ነብሳቸው ቆርጠው አጋር ፈልገው ነው ከመቅፅበት ለሕዝቡ ነፃነት ሲሉ አዲስ ጎዳናን  የመረጡት።እነርሱ በጥድፈት ከአዙሪቱ የጉልበት መጠን በመላቅ የሚጓበትን አቅጣጫ በቅፅበት በማወቅ ተስፈንጥረው ወጥተዋል፤ለዚህም ነው ፋሺሽት-ወያኔ ሥልጣኑን እንዳጣ አፉን አፍኖ ይዞ በቁሙ ቀልጦ የቀረው።
       ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተሸከሙት የኢትዮጵያዊነት ኃላፊነት መሠረቱ ይኼው ነው።ከሕዝቡም መካከል ያሉትም ተቆርቋሪዎች  ሕዝቡን እናውቅልሃለን የሚሉት ፖለቲከኞች ግን:-ከየራሳቸው አመለካከት አንፃር እንጂ ከአገሪቱ ተጨባጭ   ችግሮች አንፃር ሁኔታውን አገናዝበው አይደለም።ቁም ነገሩ እና ዐቢይ ምክንያቱ ከዘመናዊው የዘመነ-ባላባትነት ጦርነት መውጣት ብቻ ሳይሆን:- ራሱ የዘመናት ቋንቋችን በጦርነት  አዙሪት ውስጥ  የበቀለ በመሆኑ በፍቅር ትግል በነፃ ውይይት   መንግሎ ለመጣል ነበር ፤የፈፀሙትም ይሄንኑ ነው
      ኢትዮጵያ አገራችን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የምታድለው እና በልቶም እንዲያድር ለማድረግ የሚያስችላት  የተፈጥሮ ፀጋ ሞልቷታል።እንኳንስ ለሕዝቦቿ፣ለአራዊቶቿና ለፍጥረታቱ ሁሉ “ተመስገን አምላካችን እግዚአብሔርን ሆይ” ሊያስብላቸው የሚችሉ ብዙ ምክንያቶች ለመኖራቸው እኛ ብቻ ሳንሆን የሌሎች አገሮች መንግሥታት በግልፅ የሚመሰክሩት ሐቅ  ነው።ይሄንን   ሐቅ የሚያውቁት የታሪክ ጠላቶቻችን ሳይቀሩ፤እርጉም ባዕዳንና ራሱ ሠይጣንም ሆነ ዲያቢሎስ እንኳ የሰዎችን ሥጋ እየለበሰ   በቅናት መንፈስ የማይፈፅመው  አረመኔያዊ ተንኮል የለም።
    ቢያንስ እያንዳንዱ ዜጋ እንደሰው እንዳይግባባና የዕለት እንጀራውን በልቶ እንዳያድር ቅራኔዎችን በመፍጠር፣አንዱ በሌላው ላይ ተነስቶ ሠይጣናዊ ያገር ጥፋት በኢትዮጵያችን ያልተደረጉበት ዘመናት አልነበሩም።በእኛው ዘመን እንኳ ያየነው ቢሆንም፤ “ጥንትስ በኢትዮጵያውያን ጉዳዮች ላይ ችግሮቹ ነበሩ ወይስ አልነበሩም?”በማለት በአሁን ጊዜ በእነርሱ ላይ ጉልበት፣ገንዘብ እና ጊዜ ማጥፋት ፍፁም አያስፈልንምእነርሱን ለተመራማሪዎች እንተዋቸው፤ምክንያቱም ምን መቅደም፣ኋላም ምን መከተልና በመጨረሻም በምን  መጠናቀቅ እንዳለበት  ጠንቅቀን እናውቃለንና ነው።
  ስለዚህም ቀጥታ እኛ  ወደተነሳንበት ርዕስ እንመለስና፣በመጀመሪያ ከአዙሪት ለመውጣትና ወደነፃነት ለማምራት፤አዙሪትንም ሆነ አዞአሪን( አዝዋሪትንም)በሚገባ ልንረዳው  ይገባናል።እናም ነገሮችን በቅርፃቸው በመቀያየር ብቻ ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖራቸው በማድረግ፣በይዘታቸው ግን አንድ እንደሆኑ እያወቅን፣ዳሩ ግን በአማርኛ ቋንቋ ቃሎቻችንን ስናጠማዝቸው  ክፉ መንፈስ እንደጣለው ሰው ዐይናችንን በቁማችን እናዥገረግራለን።እናም አርቀን ማሰብ ተስኖን በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠራችንን እንዘነጋና”በአዙሪት ጉልበት ስሌት”ተምሳሌነት ከአዝዋሪት(አዙሪት)ተመላልሰን በሰዎች ደም-ዕዳ  እንገባታለን።በታሪክም የተመዘገበው ሐቅ ይሄው ሲሆን ያሻሻልን መስሎን ዳሩ-ግን እያደረግን ያለውም ያንኑ ጥፋት በይዘቱ በመድገም እንዲፈፀም ለማድረግ ነው።
   ይሁንና የእነዶክተር ዐቢይ ለማ ቲምን እና የወቸገል-ዜናዊ ስብሃት ነጋን ቡድኖችን ብቻ የአንድ ዓመት የቅርፅ እንቅስቃሴን  በአንፃራዊነት ስንመለከት፤በይዘት እና በሂደት የተለያዩም ቢሆኑም ሁለቱም”በአዙሪት ጉልበት ስሌት”ውስጥ ያሉ ናቸው። ልዩነቶቻቸው በይዘት ውስጥ የሚታዩ ቢሆኑም፣የግዝቨታቸው መጠን እንዳለ ሆኖ፣የጥዽፈታቸው ስሌት ግን የተለያየ ሆኖ ቁልጭ ብሎ እናገኘዋለን፤ይህንን ሐቅ ከ”አዙሪት ጉልበት”በስሌት ለምን መውጣት እንደሚያስፈልገን በዝርዝር ስንመለከት እናየዋለን፣ በቅድሚያ ግን አሁን ያለንበትን ሁኔታ እናገናዝብ።
   አሁን ያለንበት ሁኔታ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት “ያለምንም ደም…” ማለታችንን በወታደራዊው መንግሥት ሰምተን ነበር፤ “ሰላምና መረጋጋትንም…” በደም ተጨማልቆና በሠይጣናዊ ተግባር ተደብቆ በይደር ተቋጭቷል።አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ደግሞ የተለየ የትግል ውጤት ለማስመዝገብ “የግልፅነት ዘመን”ፕሮትራይስካን በመሰለ ደረቅ ዐይን-አውጣ የትግል ስልት እነዶ/ር ዐቢይ ለማ ቲም ትግሉን በድንጋጤ ተያይዘውታል።
        እነዚያ የትግል ድሎች በሰዎች መልካም ፈቃድ ታስበውና ታቅደው የመጡ እንደአልነበሩ ሁላችንም ባንሆን በታሪኮቹ ውስጥ ዕድሜና ጤና እግዚአብሔር ሰጥቶን ያየን ሁሉ ምሥክሮች ነን።{እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤
ሰው ግን አያስተውለውም።መጽሐፈ ኢዮብ ፴፫፥፲፬ }“እኔ አሸናፊ ቡድን ነኝ ያለው”ሕዝቡን እንዴት እየገደለ ከወቅታዊው መንግሥት የሕዝብ ሥልጣን መንጭቆ ሲወስድ እንደነበረ በአይናችን በብሌኗ አይተናል። ቡድኖቹ እንደምንም አጭበርብረው የአንዲት ዓመት ሥልጣን ልሰው ከቀመሱ በኋላ ሲያጣጥሙት ሠይጣን ልባቸው ውስጥ ድንገት ገብቶ ቁጭ ማለቱንም የተረዳነው በአዋጆቻቸው ብዛት ነው።የሥልጣንን በዕርኩሳን ቶሎ መለክፍ አስቀድሞ ያወቀ፣በደምብ ከሚያምንበት ሐይማኖተ ትምህርት ቀድሞ አውቋልና ፈተናውን ይወጣል፤ያላወቁት ግን ወደ ክፉ-አምልኮ ሄደው የባሰ የማይታረም ጥፋት እንደሰሩ እኛም ምሥክሮች ነን።
         ድርጊታቸው እንደ እሳት አፈጣጠር ነው፤እሳት ምን ያህል የሰውን ልጅ ሊጎዳም ሆነ ሊጠቅም እንደሚችል ስለምናውቅ፣      በሥልጣኔ መሳሪያዎች እየታገዝን ለምንፈልገው ጉዳይ ብቻ መገልገያ አድርገን እንደፈለግነው እንጠቀምበታለን፤ ምርጫው የእኛው ብቻ ነው።እሳትን በጥንቃቄ እንደምንይዘው ደግሞ ሥልጣንንም ከእሳት ባላነሰ ደረጃ ይበልጥ ልንጠነቀቀው ይገባናል፤ ምክንያቱም  የሚያጠፋው በሰዎች እጅ ላይ ገብቶ ነውከዚህም አንፃር አሁን ምን ማድረግ እንድሚገባንና ለወደፊቱስ የምናቅደው ምን መሆን እንዳለበት በቀላል አቀራረብ ላስቀምጠው።
      በእኔ ዕምነት(መተማመን)ዐቢይ-ለማ ቡድን በብዙ አጋጣሚዎች በአደባባይ የገቡልንን ቃሎችና የሚያደርጓቸውን   ጅማሮዎች ስመለከት በየትኛውም አቅጣጫ ሆኜ አይቻቸዋለሁ፤፹፭ % በትክክል አንድ ዓይነቶች ናቸው፤ እንደሚወራው  መሰሪዎች አይደሉም፣ስለማለያየት የሚያወሩት ራሳቸው የሚያለያዩት ሰዎች ናቸው።እኔም ሆንኩ ሌላው ይሄ ቢቀድም ያኛው ቢከተል እያልኩ እንደሌላው የማስባቸው ብዙ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ሞልተዋል።አንድ ትልቅ ነገር ግን ብዙዎችም የማይገነዘቡት እና ሁላችንም በትግሉ ውስጥ ያለነውም ሆነ ትግሉን በርቀት ሆነን የምንመለከተው”የትግሉ ሜዳ”ምን ዓይነት ሁናቴ እንዳለው አለመረዳታችን ነው።የችግር አፈታታችን፣አቀራረባችን፣አነጋገራችን፣የሕሊና ዳኝነታችን እና እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ ይቆጠራሉ።
        እንደ የእግር ኳስ ሜዳም የተመቻቸና የፀዳም አይደለም፤ወይም እንደባቡር ተሳፋሪዎች የምንጓዝ ልንሆን አንችልም፤ አሊያም በመንገድ ላይ እንደሚሽከረከር አውቶሞቢል ብቻ አይደለም።እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ አባባልን(http://ethioforum.org/amharic/)ይመስላል፤ከትግላችን ምስል ጋር የተቀራረበ እይታ ያገኘሁት የእርሳቸውን ነው፤ትክክል ባይሆኑም።ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምም(https://www.tzta.caወዲያ ወዲህ ይላል ሲሉ ትክክለኛ ናቸው ሁለቱም አባት ምሁራኖቻችን።አንድ ዓይነት አመለካከት ነው ያላቸው፤ምክንያቱም ስለኢትዮጵያ የመቆርቆራቸውን እይታ ስመለከት  መጓዣቸው ላይ ተቀምጠውና በአዙሪቱ ውስጥ ሆነው መፍትሄውን ስለሚያስቡ ነው።ትክክል እንዳሰቡት በመጀመሪያ ግን “ከአዙሪቱ መውጣት አለብን”ማለት አለባቸው።
    በመረጃ ላስደግፈው፣የዐቢይ ለማ የትግል ቡድን “ያለምንም ደም አላሉም”፤”በለስላምና መረጋጋት ሥም”ሕዝብን ለማጭበርበር መጥተናል አላሉም፤ለሕዝቡ ግን መሆን ያለበትንና መብታችን የሆኑትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባለማስቀመጥ የራሳችንን የተፈጥሮ መብት ኣውጥተው ሰጡን።እነዚያ ከደርግ በባሰ ሁኔታ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና አገር የዘረፏትና ድራሿን ሊያጠፉት ቀን ሰው እየመሰሉ ማታ የሰው ጅብ የነበሩ የአንድ ጎሳ ቡድኖች የሌላውን ጎሳ አባል በእንቁልልጬ ዝርፊያ እየበከሉ በተንኮል እየቋጠሩ በፈንጂ መልክ አደለዋቸዋል።ይኼው ዛሬ ዛሬ በሕዝቦች መሃል እየፈነዳ፤   ያጋድላል፣ያፈናቅላል ለረሃብና ለመከራ ይዳርጋል።እነርሱ ግን የዘረፉትን ዘርፈው፣ልጆቻቸውን ወደውጭ ኣገር ልከው እያኖሩ:- በማን አለብኝነት አሽከሮቻቸው በነበሩት ጀሌዎቻቸው አማካኝነት የኢትዮጵያን ሕዝብ እያጋደሉ በዋሻቸው ውስጥ ይኖራሉ።
         በዚህ የፈተና አዙሪት ውስጥ ሆነን ነው እንግዴህ ለቂምበቀል ጮክ ብለን የምንናገረው።ጊዜውም ሆነ ትግሉ ይፈጥናል፣ ምን ላይ እንደተሳፈርን ብናውቀውም ባናውቀውም፤መገመት ግን አያስፈልገንም።አሁን አሁንማ ልጆቻችን በልጠውን ከመሻልም በላይ የሃምሳ ዓመታት ግድፈታችንን አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሲለውጡ ስናይ ልናበረታታቸው ሲገባ በተጠመዱ ተንኮሎች ደደብ ሰው እየመረጥን በመልዕክተኞቻችን በነገር እናስጠቀጥቃቸዋለን፤በዚህ ላይ ክፉ መንፈስ ዕርጉምነቱንም ይጨምርላቸዋል።
       ምን አለበት ለዚህች ሽልንግ ለማትሞላ ሥጋዊ ዕድሜአችን መልካም ነገሮችን በማድረግ ቀና የሆኑትን መሪዎች በግልፅነት በማረም እና በመደገፍ በጎ የሆኑ መንፈሳዊ ሥራዎችን ብናደርግ፤ ተንኮልም ይሁን በግልፅ በአደባባይ ብትፈፅሙት፤ልትታረሙ ይቻላል።በዚህም መሠረት እስኪ ያለፍንባቸውን የትግል ጉዞ መመሪያዎች እንመልከት፤ከተመለስንባቸው(አዙሪት)ናቸው።

ቀመር

አንድ ቁስ የግዝፈቱ መጠን  “ ”  ቢሆንና በ”ቨ ጥድፈት፣ የ[ጉብጠት ሬዲየስ| [ጉብጠቱ ሬዲየስ ]] “ ቢሆን፣ የአዙሪት ጉልበቱ መጠን |እንዲህ ይሰላል፡ 

 

ፈ=

ኤሲ=

መቨ  = 

                     ረ

እዚህ ላይ “ኤሲ” አዙሪት ፍጥንጥነት ነው።

የጉልበቱ አቅጣጫ ምንጊዜም ቁሱ ወደሚጓዝበት ክብ ማዕከል ነው። ቁሱ በእውነተኛ ክብ የማይጓዝ ከሆነ፣ ቁሱ ያለበተን ቅጽበታዊ ጎባጣ ከሁሉ በላይ የሚወክል ክብ ወይም ኦሱሌቲንግ ክብ ማዕከል፣ ወደዚያ ያመለክታል።ከላይ አጭር መግለጫ ይዞ ስለአዙሪት የተገለፀው ስለቁስ የተገለፀ ሳይንሳዊ ትንተና ነው ።ከአስቀያሚው የአዙሪት ፈተና፤ይህንኑ ስሌት ነው በቀመርነት በማሕበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ላይ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የምንጠቀምበት

የአዙሪት ጉልበት ምንጮች

በማሕበራዊ  አገልግሎት ትግል ውስጥ ደግሞ የአዙሪት ጉልበት የሚሰጠውና፤ከአዙሪት ጉልበት ምንጮች ቀንደኛው አዙሪት፤

ብታምኑም ባታምኑም  የሕብረተሰቡ ተራ-ወሬ ነው።

ምናልባት “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚለውን የአባት እናቶቻችንን አባባል ካስታወስን ሐቁን ልንጋተው እንችላለን።

መፍትሄ

 • መጀመሪያ የትግል አዙሪት ውስጥ የሚመልሰንን በሚገባ እንረዳ ይህም “ጦርነት”ብቻ ነው፤ምን ዓይነት ጦርነት ኤኬ ፎርቲ ሰቭን ጠብመንጃዎችን አሊያም ልዩ ልዩ ስናይፐሮች  እንዳይመስሉን፤በቴክኒዎሎጂ የሚታገዙ የወሬ ማሰራጫ መሳሪያዎች ናቸው፤እንደገናም የሚመልሰን ደግሞ በጉልበተኛነት መተማመን ነው።እናም  የፍቅር አስፈላጊነት እንዳለ ሆኖ፤ ሰውንም በሰውነቱ መቀበል የመጀመሪያችን «የሰብዓዊነት» እርከን አድርገን፣የዳኝነቱንና  የኅላፊነቱን  ሥልጣን ግን ለሕዝብ አስረክበን የተሻለ ሃሳብ እንዲያሸንፍ ሙሉ ፈቃዳችንን እንስጠው።
 •     ይኼንን  ጊዜም   የሃምሳ ዓመታቱን ቁስል አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በይቅርታ እንዳጠፋነውና፤ከጦርነት አዙሪቶች ወጥተን በተገቢው መንገድ  ከአዙሪቷ  ስንገላገል ደግሞ፣አምስት ዓመታት ባልሞላን ጊዜ ውስጥ ታምር የሆኑ ውጤቶችን ከአትሌት ውጤቶች በላይ ለአለም እናሳያለን።የስሌታችንም መጠሪያ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ “መ+ደ+መ+ር”እንዳሉት (ስለተባለ ብቻ ሳይሆን ስለማምንበት፤)ቀላል  ቀመር ነው፣ብዬ   ነው  በዓለም ላይ  እንዲታይ፤የምስማማበት።
 •        በነገራችን ላይ እነዚህ የኢሕአድግ አባላት ናቸው  ከተባሉት መካከል፤መ+ደ+መ+ር+ን እንደማይደግፉና አብዮታዊ ዲሞክራሲን ብቻ እንደሚያራምዱ፤በመግለጫቸው በአደባባይ የነገሩን መብታቸው ቢሆንም፣እኛ መሃከል ገብተው ሊያጋድሉን አንፈቅድላቸውም።
 • በፓርቲ ስብሰባቸውም መጨረሻ ላይ በአይዲዎሎጂ ልዩነት ሕውሃት መለየቱን ይፋ አድርጓል።እስከዛሬ ወደ መ+ደ+መ+ር ሥልጠናም ከተራ አባላት ጀምሮ እንዲገቡ አልታዘዙም።እናም በድብቅ  በሦስተኛው እጆቻቸው ሕዝቡን እያጋደሉ እንደሆነ ሕዝብ ያወቀው ገሃድ ነው።ለምንስ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ “እ+ን+ደ+መ+ር” እያለ ሕዝቡን እንደሚጨቀጭቀው እነዚህን የሥጋ ትሎች ቆራጥና  ሕጋዊ ርምጃ አይወስድባቸውም?በጣም የሚያሳዝነው በየከተማው ምን እየተደረገ እንደሆነ የማያውቁ ብቻ ሳይሆኑ በእነርሱ ላይ ስለሚደረገው ግድያ ለሃያ ሰባት ዓመታት ሲዋሻቸው የነበረ  መሆኑ ነው።ካድሬው ዛሬ ዛሬማ ብሶበት የመሳሪያ ደላላ ሆኖ  እንዲጋደል ያስታጥቀዋል። እንግዲህ በምንፈፅማቸው ነገሮች እያንዳንዳችን የግልና የጋራ ኃላፊነት እንዳለብን ተገንዝበን እኛ  አልተነካንም ብለን ችግሩ እስኪደርስብን ድረስ አንጠብቅ።
 • ስ+ን+ደ+መ+ር   =   [ነብሰ-ገዳዮች+ይቅርታቸው+{በሚነበብ+በግንባር}]-[ኢሃድግ-ሕውሃት]x{O}
 •                          =   በነብሰ-ገዳዮች ለተገደሉት እና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን የደም-ካሳ ይገባቸዋል፤
 •              ስለዚህ  =   ምን ስሌት ያስፈልጋል ለዚህ ውስብስብ የማህበራዊ ቀውስ፣
 •           ግልፀኝነት =  ለ+መ+ደ+መ+ር መንገዱ ነው፤
 •                  ፍቅር=  ግን ሁሉን ይበልጣልና
 •             ከአዙሪት =  በመውጣት፣
 •                ነፃነትን =  ለማግኘት
 •                 ዛሬም  =  በሕግ እንደመር።
 • ማጠቃለያዬ      የትግላችን መዳረሻ፣ከአዙሪት በመውጣት፣ነፃነትን ለማምጣት አይደለምን? ዶ/ር ዐቢይ አህመድም የምር  በእሥስቶቹና በአጭበርባሪዎቹ መሐል ሆነውም   አዙሪቱ  ገብቷቸዋል።

ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘላለም ትኑር!!!

Filed in: Amharic