>

"ምናልባት ለዘይትና ሽንኩርት 500ብር  እንጨምርላቹ ይሆናል...!!"ጠ/ሚ ዶ/ ር አብይ አህመድ ቅሬታቸውን ላሰሙ የህክምና ባለሙያዎች የሰጡት ያልተጠበቀ ምላሽ

“ምናልባት ለዘይትና ሽንኩርት 500ብር  እንጨምርላቹ ይሆናል…!!” 
የጠ/ሚሩን ቅሬታቸውን ላሰሙ የህክምና ባለሙያዎች የሰጡት ያልተጠበቀ ምላሽ
 
በዶ/ር አሰፋ ከበደ
 
ትላንት የጠ/ሚሩን ስብሰባ በመካፈሌ ምንም ቅር አይለኝም፡፡ ላለመቅረትም በቂ የሆኑ 3 ዋና ዋና ምክንያቶች አሉኝ፡፡
.
1. የመጨረሻ የመፍትሄ ሰው ስለሆነና ከሱ በላይ የምንጠይቀው አካል ስለሌለ
.
2. ምናልባት እኛ ሐኪሞች ለዘመናት እየኖርንበት ያለውን ዘመናዊ ባርነትን ጠ/ሚሩ ላያቅ ይችላል በሚል ሰበብ እና በተወሰነም ቢሆን ጥያቀቄዎቻችንን በአጭርና በረጅም ግዜ  ይመልስልናል የሚል ትንሽዬ እምነት ስለነበረኝ
.
3. የዛሬዋ ስብሰባ በቀጣዩ ውሳኔዎቻችንን ይጠቅመናል ብዬ  ስላመንኩ …. አዎ የዛሬዋ ስብሰባ በጣም ጠቅማኛለችም ልቤንም ሰብረዋለች, ወደፊትም እንድራመድ አርጋኛለች፡፡
.
ሲጀመር ከስብሰባው ብዙም የጠበኩት ነገር ባይኖርም የሐኪሙን የዘመናት ሮሮ ይሠማል ፣ እንባችንን ያብስልናል ያልነው ጠ/ሚኒስትራችን ይባስ ብሎ በሚዲያ ፊት
.
★ሐኪም ንፅሕናውን አይጠብቅም ፣ ጓውኑን እንኳን በስርዓት አይዝም፡፡
.
★ ስንቶቻችሁ ነው ሰዓት የምታከብሩት?, ሲኒየሩ ሐኪም ስራውን  ሙሉ ለሙሉ ለነርስ  አይደል እንዴ ጥሎ የሚሄደው
★ እናንተ ሐኪሞች አሁን የምላቹን ብቻ ጳፉና ስብሰባችንን እንቋጭ  ያውም በቁጣ
★ብርን አስባችሁ ከመጣችሁ አታስቡት ፡ ኢትዮጽያ በአሁኑ ወቅት ተመንዝሮ የማያልቅ ተስፋ እንጂ ብር የላትም፡ ምናልባት ለዘይትና ሽንኩርት 500ብር  እንጨምርላቹ ይሆናል፡፡
.
★ለሁለት ሰዓት በሆስፒታል ውስጥ ለማይቆይ ሲኒየር ሐኪም 9,000ብር ሲበዛበት ነው፡፡
.
★በሬ እየታረሰበት ስጋውም እየተበላ ቆዳውም  ለጅማት ክር እየዋለ ይሄ ሁሉ ሲደረግበት ምንም ነገር አይናገርም… ሐኪምም እንደዚ በሬ ነዉ መሆን ያለበት
.
★እኛ ከውጭ ትጥቅ አስፈትተን  ወደ ሀገር ቤት አስገብተን ስናበቃ ሕዝቡ አይ እኛ ነን ያስገባናቸው  ብሎ ታሪካችንን እንደተሻማ ሁሉ ሐኪምን በተመለከት ሠሞኑን የሚታየው የለውጡ አካል እንጂ  ኢንተርን ሐኪሞች ናቸው ያነሡት የሚለው የታሪክ ሽሚያ የሆነውን ነግግራችሁን አቁሙ
.
★መኪና መኪና ላላችሁት 1 መኪና እንገዘላችሁና መንዳት በጣም ቀላል ስለሆነ ተራ በተራ ትነዳላችሁ፡፡ ዛሬ አንደኛው በር ላይ ከቆመች ነገ ሌላኛው በር ላይ … በስላቅ  ንግግር
.
★ከተማችንን አዲስ አበባን ለማስዋብ ስንል ባለሃብቶችን ኑ ግቡና አግዙን እያልን ስንት በጀት እያፈሰስን ባለንበት ሰዓት እናንተ ሐኪሞች ብር ብር አትበሉ ሕክምናን ብር ማግኛ አርጋችው አትስሩ ስትመረቁ በገባችሁት ቃል መሠረት አርፋችሁ ስሩ፡፡
.

★ለልብ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት  የሠጣት ምላሽ

በጣም ልቤን የነካው ንግግር ነበር የልብ ቀዶ ሕክምና እስፔሻሊት የሆነችዋ ሴት ዶ/ር ተማፅኖ ያለበት ንግግር  ነበር የተናገረችው፡፡ ለ10 ዓመት ያለ ደሞዝ ያገለገለች  Passionate  የሚለው ቃል ለሷ የማይመጥናት  ርሁርህ ሐኪም፡፡ እባካችሁ አትግፉን (don push us) ሀገራችንን ማገልገል እንፈልጋለን ስትል ጠ/ሚሩም እኔም የ ICT ባለሙያ ወደ ውጪ መውጣት አቅቶኝ አይደለም ሀገሬን ላገልግል ብዬ ነው ብሏት አሁንም የባርነት ህይወቷን እንድትቀጥል እንዲሁም የሕክምና ሙያ ከምንም እንደማይበልጥ በቀላሉ ነግሯት አለፈ፡፡
.
አባቴ ከሞተ 5ዓመቱ ነው ፣ ከሱ ሞት በኀላ ዛሬ ለመጀመሪያ ግዜ በዚች እስፔሻሊት ንግግር  እንባ ተናንቆኝ አለቀስኩ፡፡ I hate my profession.
.
★አሁንም ሌላኛዋ anethesia resident የወለድኩትን ልጄን እንኳን ጡት ሣላጠባ እያለች ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ፣ ማይኩን ሊቀሟት ሲሞክሩ እምቢዮ ላልቅስ ይውጣልኝ  ተዉኝ እያለች ስታለቅስ ጠ/ሚሩ ያንቺ የግል ጉዳይ ስለሆነ ጉዳይሽን ሰሞኑን ከ ዶ/ር አሚር ጋር ጨርሺ ብሎ በአንድ ቃል አለፋት፡፡ ፠ የሁለቱን ሴቶች እንባ ትላንት የነበረ ሰው ማንም ለደቂቃ አይረሳም።
.
★እኛ ነጭ ሸሚዝ በ black ribbon አስረን የገባን ሐኪሞች እጅ ብናወጣም እድል ስላልተሰጠን አላስችል ብሎት ማይኩን በግድ ቀምቶ ለተናገረው ለጀግናው ዶ/ር በጋሻው (Senior surgeon @ Arba minch general hospital) የተሠጠው ምላሽ ልክ እንደ anesthesiaዋ resident ነበር፡፡
.
★እንዳጋጣሚ ሆኖ አባቴ ሰሞኑን ለሕክምና አዲስ አበባ መጥቶ ነበር እና ዛሬ ከሐኪሞች ጋር ስብሰባ እንዳለኝ ስነግረው በደንብ መርቃቸው ለነሱ ሚገባቸው ትልቅ ምርቃት ነው አለኝ አባቴ።
.
★ ለምንድነው ሚኒስትሮች ለጉንፋን እንኳን ውጨ ሀገር ሄደው የሚታከሙት ሲባል, ኢትዮጵያ ውስጥ ሕክምናም ሐኪምም ስለሌለ እና ለsecurity ሲባል ነው፡፡
.
★ ሰሞኑን ሐኪሞች ስላኮረፋችሁ ለኩርፊያችሁ የሚሆን ምሳ ብሉና ቤተ-መንግስቱን ጎብኝታችሁ ወደ ስራ ሂዱ
…..
ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ተብለናል ፣ መሪያችን ባደባባይ ባሪያ መሆናችንን በድጋሚ ሲያበስረን እጅጉኑ አመመኝ፡፡ ትላንት ሙያዬን ከልቤ የጠላውበት ቀን ነበር፡፡ ምንም እንኳን ፖለቲከኞችን ማመን ቢከብድም ሰውየውን እስከ ትላንትናዋ ቀን ድረስ ትንሽዬ እምነትና አድናቆት ነበረኝ ፣ አሁን ላይ ግን ክፉኛ ጠላሁት፡፡
.
He is a smart politician but I never expected that he will defend for this infected and corrupted health system for his political consumption only. But he did it!
.
በጣም የገረመኝ አንድ ጥያቄ እንኳን አለመመለሱ ሣያንሠው ቀኑን ሙሉ ሲሳለቅብን መዋሉ ነው፡፡ የተለመደውን የሽንግልና ቃል እንኳን ሳይለን እና በስርዓት treat ሳያረገን የባሠውኑ አሸማቆ መለሰን፡፡
.
ውድ የኢትዮጵያ ሐኪሞች በሙሉ እስከ አሁን የመጣንበትን መንገድ በትልቁ  ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ በትክክል step by step ተጉዘን ጠ/ሚሩ ጋ መድረሳችን ተገቢ ነበር ፤ እደግመዋለው አዎ ተገቢ ነበር። እንኳንም ተሠበሠብን እንኳንም ሠማን፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ለሁሉም ነገር በቃን ልንል ይገባናል፡፡ ስለሙያችን ጥልቀት ምናውቀው እኛና እኛ ብቻ ስለሆንን ማንም እየተነሳ በጭፍን የፈለገውን  ስላለን ብዙም አንናደድም፡፡
.
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ሐኪሞች እና በሙያው ስም የተመሠረታችሁ ማህበራት በሙሉ ስለሕክምናው ምንም እውቀት ሳይኖራቸው በመፈትፈት የብዙሃኑን ወጣት ሐኪሞች ተስፋ ያጨለሙትን አካላት/ሠዎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ በቃ ልንል ይገባል፡፡  እናስቁማቸው።
.
ክቡር ጠ/ሚ የኢትዮጵያ ሐኪሞች ጥያቄ ምንም ፖለቲካዊ ይዘት የሌለው ሊኖረውም የማይችል ለዘመናት መልስ ያጡ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ እርሶ ትላንትና እንዳየኖት ከሆነ አስቀድመውኑ pre-occupied ሆነው እንዲሁም ለተጮከነው ሐኪም የሚሰማ ጆሮ እንጂ ልብ ይዘው እንዳልመጡ በግልፅ አይተናል፡፡ ክቡር ጠ/ሚ አሁንም ቢሆን ግዜው ሳይረፍድ እራሶትን ከሀሰተኛውና ከሙሠኛው ጤ/ጥ/ሚ ነፃ አውጥተው ጆሮትንና ልቦትን ለሐኪሙ ቢሰጡ እላለው፡፡
.
Break The Silence And Liberate The Health System
Dr. Assefa kebede
ሚያዝያ 26/08/2011ዓ.ም
Filed in: Amharic