>

በዜግነት ፖለቲካ 7 ፓርቲዎች የሚያደርጉት የውህደት ዝግጅት ስራ ተጠናቀቀ 

በዜግነት ፖለቲካ 7 ፓርቲዎች የሚያደርጉት የውህደት ዝግጅት ስራ ተጠናቀቀ 
አልዓዛር ተረፈ
የዜግነት ፖለቲካና ማህበራዊ ፍትህን መሰረት አድርጎ በቅርብ የሚመሰረተው አዲስ ፓርቲ በባለፉት ስምንት ወራት ሲያደርገው የነበረውን ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡
የሚመሰረተው አዲስ ፓርቲም ቀደም ሲል የነበሩ ሰባት ፓርቲዎችን በማዋሀድ የሚፈጠር እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ፓርቲዎቹም ሰማያዊ፣ ግንቦት 7፣ መኢዴፓ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ ኢዴፓ፣ የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ እና የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ናቸው ተብሏል፡፡
የአዲስ ፓርቲ ዝግጅቱም ከዚህ በፊት የነበረውን የፓርቲዎችን መዋቅር ለማክሰም እንዲሁም በተለያዮ ጉዳዮች መግባባት እንዲደረስበት ለማድረግ የተካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ፓርቲው በባለፉት ስምንት ወራት ሲያደርግ የነበረውን የውህደት ስራ አጠናቆ በመጪው ሐሙስና አርብ የፓርቲ መስራች ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡
በጉባዔውም 1 ሺህ 700 ከየወረዳው የተወጣጡ ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ፓርቲው የዜግነት ፖለቲካ በአሁኑ ሰዓት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል፡፡
Filed in: Amharic