>

"ቤኒሻንጉልን ኦሮማይዝድ የማድረግ ሴራ!!!"  (ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬ) 

“ቤኒሻንጉልን ኦሮማይዝድ የማድረግ ሴራ!!!”
 ጋዜጠኛ ያለለት ወንድዬ 
አማራ ጠል የሆነዉ የህወሃት መንግስት የበላይነቱን ካጣ በኋላ ተረኛ ነኝ ባዩ የዶ/ር አብይ ድርጅት ኦዴፓ በግብር ስሙ ኦነግ ታላቋን ኦሮሚያ ለመመስረት ብዙ ርቀት ተጉዟል፡፡ ለአብነት በህወሃት የሞግዚት አስተዳደር ስር የነበሩ እንደ ቤኒሻንጉል ፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌና ሃረሪ ክልሎችን በተራዉ ተረክቦ የሞግዚት አስተዳደሩን ቀጥሎበታል፡፡ ጠንቅቄ የማዉቀዉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ እየተሰራ ያለዉን ሴራ የማጋልጥበት ወቅት አሁን ነዉና ተረኛዉ ኦዲፒ ክልሉን ኦሮማይዝድ የማድረግ ሴራዎቹን አንድ በአንድ እናየዋለን፡፡
☞ #ሴራ_አንድ
 የሴኔ 16ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት
*******************************
ሴኔ 16/2010 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ የተቀሰቀሰዉ ግጭት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነዉ፡፡ ኦነጎች የበርታ ማህበረሰብ አባላት የሆኑ 8 ሰዎችን በማገት እና የደረሱበትን ደብዛ በማጥፋት በርታዎች ቂም እንዲይዙ ተደረገ፡፡ ኦነግ ወይም ኦዲፒ ይን ሲያደርግ በደንብ አስቦበትና ለሁለት ዓላማ ነዉ፡፡አንድም የአሶሳ ከተማን ከትግራይ ተወላጆች ወይም ከህወሃት ሰዎች ነፃ ማድረግ ሲሆን ሁለትም የቤጉህዴፓን አስተዳደር ማፍረስ ነበር፡፡ አንደኛዉ ተሳክቷል፡፡በክልል ደረጃ ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸዉን የትግራይ ተወላጆች ነፃ ለማድረግ የተሸረበዉ ሴራ ተሳክቷል፡፡ ቤጉህዴፓን ለማፍረስ የተደረገዉ ተደጋጋሚ ጥረት ግን ሳይሳካ በመቅረቱ ወደ ድርድር ተገብቷል፡፡ ድርድሩም ከኦዲፒ ጋር ተባብሮ መስራት ነዉ፡፡ በዚህ የፖለቲካ ሴራ ዉስጥ የሰኔ 16ቱ የአሶሳ ግጭት የ21 ሰዎች ህይወት ቀጥፎ አልፏል፡፡ ኦዲፒ ወይም ኦነግ ይህን ሴራ ነጥብ አስመዝግቦበታል፡፡ የኦዲፒ ወይም ኦነግ የወረራ ሴራ በዚህ አላበቃም፡፡
☞ #ሴራ_ሁለት
የመስከረም 16ቱ የካማሺ ዞን የጉሙዝ አመራሮች ግድያ
**********************************
የቤኒሻንጉልና የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጋራ የፀጥታ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዉ መስከረም 16/2011 ዓ.ም ወደ ካማሽ ሲጓዙ የነበሩ የካማሽ ዞን የጉሙዝ አመራሮች ላይ የኦነግ ሰራዊት ጥቃት ይፈፅምባቸዋል፡፡ በጥቃቱም 4 አመራሮች ወዲያዉ ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ጥቃቱ ሆን ተብሎ የታቀደበት ነዉ፡፡ ምክንያቱም የጉሙዝ አመራሮችን የያዙ መኪኖች ሹፌሮቻቸዉ ኦሮሞዎች በመሆናቸዉ ሳይነኩ ቀርተዋል፡፡ መኪኖቹ ግን በእሳት እንዲጋዩ ተደርጓል፡፡ በሞቱት አመራሮች የተቆጡት የካማሽ ጉሙዞች በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ ምንም በማያዉቀዉ የኦሮሞ ህዝብ ላይ መዓት ወረደበት፡፡ በካማሽ ዞን አምስቱም ወረዳ ላይ የሚኖረዉ አማራዉም የመስዋዕት በግ ሆነ፡፡ ለቁጥር የሚያታክት ህዝብ አለቀ፡፡ በርካቶች ተፈናቀሉ፡፡ የኦሮሞ ወጣቶችም ከፍተኛ የሆነ የመጠቃት ዕልህ ዉስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል፡፡ የኦሮሞ ወጣቶች የመጠቃት የእልህ ስሜትን ኦዲፒ ወይም ኦነግ ብሄርተኛ እንዲሆኑ አጋጣሚዉን ተጠቀመበትና የቄሮ አደረጃጀቱን በምዕራብ ወለጋ ላይ ገነባ፡፡ ለተከታታይ 6 ወራት ያህል ቀጠናዉ ታመሰ፡፡ ከካማሽ ዞን አማራዉ በዚህ መልኩ እንዲፀዳ ተደረገ፡፡ ከካማሽ ዞን ሁሉም አከባቢዎች የተፈናቀሉትን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች ላይ የድህነት ኑሮን የሚገፉ በርካታ ኦሮሞዎች እስከ ግንቦት 10/2011 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ እንዲመለሱ ወይም መደበኛ እና አዲስ ኑሮ እንዲጀምሩ ተደረጓል፡፡ በዚህም ከአማራዉ ነፃ የተደረገዉ የካማሽ ዞን በአሁኑ ሰዓት ኦሮማይዝድ ተደርጓል፡፡ የኦዲፒ ወይም የኦነግ ሴራ አሁንም ቀጥሏል፡፡
☞ #ሴራ_ሶስት
የሚያዚያ 17ቱ የመተከል ዞን ግጭት
***********************************
ሚያዚያ 17/2011 ዓ.ም መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ቆታ መገንጠያ ላይ በጫኚና አዉራጆች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በአንድ የጉሙዝ ብሄር ተወላጅ ላይ የፌደራል ፖሊስ አባል በወሰደዉ እርምጃ መልኩን ቀይሮ አማራዉ ብቻ ተነጥሎ በጉሙዝ ብሄረሰቦች በቀስትና በጥይት እንዲያልቅ ተደርጓል፡፡ ይህ ግጭት ስፖንሰር በተደረጉ የጉሙዝና አንዳንድ  የሽናሻ አመራሮች ፊት አዉራሪነት የተፈጸመ ነዉ፡፡ በዚህ ግጭት ከአይን እማኞች ባረጋገጥኩት መረጃ መሰረት እስከ 4 መቶ የሚደርሱ የአማራ ብሄር ተወላጆች በቀስት ተመተዉ በካራ ታርደዉ በጫካ ቀርተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩት ከቀያቸዉ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡ ችግሩ አሁንም ድረስ አልተፈታም ፡፡
*******
የODP Grand goal 
የኦዲፒ ወይም የኦነግ ማስፈፀሚያ ስልታዊ ተቋማት 
****************************
#1ኛ. የኦሮሚፋ ቋንቋ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ እንዲሰጡ ማድረግ ነው። ይህ አሶሳ ከተማ እና ባምባሲ ወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ ተደርጓል።
#2ኛ. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች የጋራ ፕሮጄክት ፅ/ቤት ከፍተዉ እየተንቀሳቀሱ ነዉ፡፡ የጋራ ፕሮጄክት ፅ/ቤቱ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስም የተከፈተ ቢሆንም የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከግማሽ ቢሊዬን ብር በላይ በጀት በመመደብ ሁለት የመንገድ ፕሮጄክቶችን እየሰራ ነዉ፡፡ አንደኛዉ ከአርጆ ጉደቱ እስከ በሎጅጋንፎይ (ሶጌ) 395 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመንገድ ፕሮጄክት፣ ሁለተኛዉ ከሃሮ ሊሙ (ኦሮሚያ) እስከ ያሶ (ካማሽ) 230 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የመንገድ ፕሮጄክት ነዉ፡፡ ይህ ፕሮጄክት ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ታስቦ የተሰራ ሳይሆን ቤኒሻንጉልን የመጠቅለል ስትራቴጂ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ኦሮሚያ ዉስጥ በርካታ ኦሮሞዎች ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖሩ ይታወቃልና፡፡
#3ኛ. በኦዲፒ ወይም በኦነግ ስፖንሰር አድራጊነት የመተከል አስመላሽ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥያቄያቸዉን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
#4ኛ. የአገዉ ብሄራዊ ሸንጎና የምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ፓርቲ (እዉቅና ያላገኘ) ፓርቲዎች በኦዲፒ ወይም በኦነግ ስፖንሰር ተደርገዉ አገዉና አማራ ከመተከል እንዲወጣ በማድረግ የአዊ ዞን እና መተከልን ደምረዉ  ክልል የማድረግ ሴራ እየተሰራ ስለመሆኑ፣
#5ኛ. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳን ወደ ኦሮሚያ መጠቅለልና ኦሮሚያ ከሰሜን እና ደቡብ ሱዳን ጋር ሚያዋስናትን ቀጠና መመስረት፣
#6ኛ. የማንነት ክስረት (Identity crisis) ወይም እኛ ከሌላዉ እንለያለን የሚሉ (special identity) ያላቸዉን ፅንፈኞች በማደራጀት ክልሉን ከአማራ ነፃ በማድረግ ከ5 ሚሊዮን በላይ ኦሮሞዎችን የማስፈር ዕቅድ ተነድፎ በተጨባጭ እየተሰራበት ይገኛል፡፡
ልብ ያለው ልብ ይበል ሰዎቹ ብዙ እርቀት ሄደዋል።
Filed in: Amharic