>

የምንስማማው አሐዱን ፈትታችሁ ጃዋርን ስታስሩ ነው!  (ስዩም ተሾመ)

የምንስማማው አሐዱን ፈትታችሁ ጃዋርን ስታስሩ ነው! 
ስዩም ተሾመ
* ዓይን ያወጣ ጎጠኝነት? ዘረኝነት? አድሏዊነት?
* እባጭ አምባገነንነት? ጨቋኝነት? አፋኝነት? ወይስ 
* አጉል እብሪት? ትዕቢት? ማን-አለብኝነት? ቅብጠት? 
—-
አንድ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣን ጋዜጠኛ ሊያስር የሚችለው መቼ ነው? ጋዜጠኛው በክልሉ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀስ ከተገኘ ሊታሰር ይችላል፡፡ ነገር ግን ባለፈው አንድ አመት ኦሮሚያ ውስጥ ወጣቶች ዱላና ገጀራ ይዘው እንዲወጡ በመቀስቀስ ረገድ ሁሉም ጋዜጠኞች አንድ ላይ ቢደመሩ ጃዋርን አይስተካከሉም፡፡ እንደ አለሙ ስሜ ባሉ የክልሉ ባለስልጣናት ላይ የሃይል እርምጃ እንዲወሰድ በመቀስቀስ የሞት ፍርድ ሲፈርድ የነበረው አያቶላህ ጃዋር ነው፡፡ የኦዴፓ ሆነ የክልሉ መስተዳደር ሃላፊዎች ያሳለፏቸውን ውሳኔዎች በመፃረር ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ በመቀስቀስ ከሆነ እንደ ጃዋርና OMN የተሳካለት የለም፡፡ በህዝቦች መካከል ቂምና መቃቃርን በመስበክ ረገድ ከደቡብ ሲዳማ እስከ ሰሜን ጎንደር የአመቱ ተሸላሚ ሚዲያ የጃዋር OMN ነው!!! በፈለገው ሰዓትና ቦታ የሚያቀረሸው ጃዋር ነው!!! የአሕዱ ራዲዮና ጋዜጠኞች ጥፋት ምንድን ነው? የጃዋርና ጃዋር አለመሆናቸው አይደለምን?? ለእነ ጃዋር ሲሆን እንደ ህዋ ሰፍቶ የተለጠጠው ትዕግስት እና ልበ-ሰፊነት ለአሕዱ ሲሆን  እንደ መርፌ ቀዳዳ የጠበበበት ምክንያት ምንድነው?
በአጠቃላይ እንደ ጃዋር ያለ ሰው እንደፈለገው በሚያዛርጥበት ሀገር የአሕዱ ራዲዮ ጋዜጠኞች መታሰር ለብዙዎቻችን ከልክ ያለፈ፤ ጎጠኝነት፥ ዘረኝነት እና አድሏዊነት ነው!!! በአሕዱዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ከልክ ያለፈ እባጭ አምባገነንነት፥ ጨቋኝነት እና አፈና ነው!!! ሌላው ሀገር እያተራመሰ “አለሁ ባይ” ባለግዜ የሌላቸውን ጋዜጠኞችን ማሰር፥ ማንገላታትና ማስፈራራት ለብዙዎቻችን በአጉል እብሪት የተሞላ ትዕቢት፥ ማን-አለብኝነትና ቅብጠት ነው!! አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በተናገረ ቁጥር ሀገር የሚበጠብጠው፣ እንደ ሰሞኑ ዝም ሲል ደግሞ ሰላም የሚወርደው፤ በሀገርና ህዝብ ላይ ቁማር እየተጫወተ ገንዘብ የሚያተርፈው ጃዋር የሀገር ሰላምና ደህንነት አደጋ ነው፡፡ ለእሱ ከጥፍር እስከ ፀጉሩ እንክብካቤ እየተደረገለት የአሕዱ ጋዜጠኞችን ማሰር በሁላችንም ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው፡፡ የአሕዱ ጋዜጠኞች ያጠፉት ብቸኛ ነገር ቢኖር እውነትና ትክክል ብለው ያመኑበትን ነገር በግልፅ መናገራቸው ነው!!! በግልፅ ሆነ በድብቅ ውሸት እየተናገረ ጥላቻና ቂም ሲሰብክ የሚውለው ጃዋር፣ ሁከትና ብጥብጥ የገቢ እና ዝናው ምንጭ የሆነ ሰውዬ ቆሞ እየሄደ ሌሎች ጋዜጠኞችን ማሰር የመጨረሻው #ቀይ_መስመር ነው፡፡ እንዲህ ከተጀመረ ደግሞ ከእኔ ጋር የምንስማማው አሕዱዎችን ፈትታችሁ ጃዋርን ስታስሩ ነው!!!
በመሰረቱ ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም ! 
ክፉው የምርጫ 97 ሳይመጣ በፊት እጅግ አሳዳጅ የነበረው ወያኔ እንኳን ጋዜጠኞችን ፓሊስ ጣቢያ እንዲመጡ በመጥሪያ ይጠራ ነበር። (እስርና እንግልቱ ከወራት የፍርድ ቤት ምልልስ በኃላ የማይቀር ቢሆንም)
አሁን በተያዘው ለውጥ ትልቁ ቁምነገር ምን ያህል ጋዜጠኞች ታሰሩ የሚለው ጉዳይ አይደለም። የአንድ ጋዜጠኛ እስር እንኳን ሀሳብን በነጻነት መብት ላይ የተቃጣ ጥቃት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። ይህ ብቻ ሳይሆን የዛሬው የኢትዮጵያ ፓሊስ የተቦካውና የተጋገረው በአፋኙ የወያኔ ስርአት መሆኑን አንዘነጋውም። እናም የቆዬ ልማዶች እንዳልጠፉ እንዲያውም ፓሊስ ራሱ ተሃድሶ (systemic reform ) ማድረግ እንዳልጀመረ እናውቃለን። ክላሹን አንግቶ የጋዜጠኛ ቢሮ ለአፈና የሚመጣ ፓሊስ ራሱ ጸረ ለውጥ ከመባል የተሻለ ስያሜ አይኖረውም።
ጋዜጠኞች ፍቱ ፣ ጸሀፍትን ማዋከብ ይቁም !  ፓሊስ ህግ ከማስከበሩ በፊት ህግን ይወቅ !
የታሰሩት ጋዜጠኞች በዋስ ተፈተዋል::
– የታሰሩት የአሀዱ ሬድዮ ጋዟጠኞች በዋስ ተለቀዋል::ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ከ6ወር በፊት በነበረ ኬዝ ስቱድዮ ድረስ የታጠቁ ሰዎች ሄደው አርብ አመሻሽ ላይ ያሰሩት ሲሆን ሌላኛው ጋዜጠኛ የታሰረው ጥበቡን ሊጠይቅ በመሄዱ መሆኑ ይታወቃል:: ሁለቱም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ዛሬ በዋስ ተፈተዋል::
Filed in: Amharic