>

ግንቦት ፳ -  ሪፑብሊክ ለመመስረት ጫካ የወረዱ ፋሽስቶች ኢትዮጵያን   የወረሩበትና አፓርታይድን ሕጋዊ ያደረጉበት ርጉም ቀን ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

ግንቦት ፳ –  ሪፑብሊክ ለመመስረት ጫካ የወረዱ ፋሽስቶች ኢትዮጵያን   የወረሩበትና አፓርታይድን ሕጋዊ ያደረጉበት ርጉም ቀን ነው!
አቻምየለህ ታምሩ
ግንቦት ፳ የኢትዮጵያ ሻለቆችና የበታች መኮንኖች የመሰረቱት የጭካኔ አገዛዝ ተወግዶ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ጫካ የወረዱት  ፋሽስት ወያኔዎችና ናዚ ኦነጎች   የመሰረቱት የአፓርታይድ አገዛዝ የተተካበት ቀን እንጂ የኢትዮጵያ «የድል ቀን» አይደለም! ሆኖም ግን  የወያኔውን ዲቃላ ዐብይ አሕመድን ጨምሮ የአገዛዙ ባላደራዎቹ ሁሉ ግንቦት ፳ን ልክ እንደ የካቲት ፳፫ የዓድዋ ድል በዓል «የድል በዓል» አድርገው  እንኳን አደረሳችሁ እያሉ በማክበር ላይ  ይገኛሉ።
ግንቦት ፳ ለኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ውስጥ የአገዛዝ ለውጥ [Regime Change] የመጣበት ቀን እንጂ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ የውጭ ወራሪ የተሸነፈበት የድል ቀን ወይንም [Victory Day] አይደለም። ግንቦት ፳ «ብሶት» ወለደኝ ለሚሉት ፋሽስት  ወያኔና ናዚ ኦነግም ቢሆን ኢትዮጵያን እየገዘገዙ እስካሉ ድረስ ደርግ የሚባል የኢትዮጵያ ሻለቆችና የበታች መኮንኖችን አገዛዝ ተክተው  ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ የመሰረቱት  አረመኔያዊ የአፓርታድይ አገዛዝ የተከለበት ቀን እንጂ እንደ ፋሽስት ጥሊያን አይነት ባዕዳና የጋራ ጠላታችንን ያሸነፈበት ዕለት አይደለም።
ስለዚህ  በመንግሥትነት ለተሰየመውም ለዐቢይ አሕመድና ለጄሌዎቹ ለብአዴኖችም  ሆነ ለኢትዮጵያውያን የድል በዓላት የሚሆኑት እንደ የካቲት ፳፫ [ጀግኖች አያቶቻችን ጥሊያንን ዓድዋ ላይ ድባቅ የመቱበት ዕለት] እና ሚያዚያ ፳፯ [ኢትዮጵያውያን አርበኞች የፋሽሰቱን የሙሶሎኒ ወራሪ ኃይል አቧራ አስገስተው ካገራችን ጠራርገው ያስወጡበት ዕለት] ወዘተ… አይነት ልዩ ቀናት ናቸው እንጂ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው ደርግ ሄዶ ከነትንሽነቱ የደርግ የጭካኔ ታናሽ ወንድም የሆነ ወያኔ የሚባል ጨካኝ የትግራይ ማፍያ ቡድን የኢትዮጵያን መንበረ መንግሥት የተቆናጠጠበት ቀን አይደለም።
 የወያኔ ዲቃላው ዐቢይ አሕመድም  ግንቦት ፳ን የድል በዓል አድርጎ የመቁጠሩ አባዜ የመጣው ወያኔ የመንፈስ አባቱና ሱሪ ያስታጠቀው ሻዕብያ የሚያደርገውን ሁሉ እንደወረደ ሲኮርጅ የኖረውን መኮረጁ ነው።  ሻዕብያ አስመራን የተቆጣጠረበትን ቀን የድል በዓል ብሎ ሲያከብር ስላየ ዐቢይም  ወያኔ አዲስ አበባ የገባበትን ግንቦት ፳ን የድል በዓል አድርጎ እንደ ወረደ ከሻዕብያ ኮረጀ። ወያኔ ከሻብያ አላንስም በሚል የመንፈስ ጥገኝነቱ ምክንያት ሻዕብያ ያደረገውን ሁሉ እየኮረጀ ሻዕብያ ከኢትዮጵያ አንጻር የፈጸማቸውን ሁሉ በመቅዳት ኢትዮጵያን የኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እያዋረደ ነው።
ሻዕብያ ኢትዮጵያን ወራሪና ቅኝ ገዢ ብሎ ነፍጥ አንስቶ ስለታገለና የታገለለትንም ዓላማ ስላሳካ፤ በተግባርም አሁን ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ኃይል ስላልሆነ፤ ግንቦት ፳ን የድል በዓል አድርጎ ሊያከብር የተገባ ነው። ዐቢይና ወያኔ ግን እንደ ሻዕብያ ሁሉ ከኢትዮጵያ ተለይተው የኦሮሚያ ሪፑብሊክና  የትግራይ ሪፑብሊክን እስካልመሰረቱና ኢትዮጵያን እስኪያንገሸግሻት እየገዙ  እስካለ ድረስ ግንቦት ፳ን በኛ ገንዘብ የድል በዓል አድርገው ሊያውጁና ሊያከብሩ አይችልም።
ለተቀረነው ኢትዮጵያውያን ግንቦት ፳ ማለት፡ የድልም የስርዓት ለውጥም የመጣበት ዕለት ሳይሆን ደርግ የሚባል ሻለቆችና የበታች መኮንኖች የተሰየሙበት የጭካኔ አገዛዝ ተወግዶ በጭካኔያቸው  ክብረወሰን የተቀዳጁት  ፋሽስት ወያኔዎችና ሁሉ ኬኛ የሚሉ  ሁሉ ብርቁ  ናዚ ኦነጋውያን  የተተከሉበት የመከራ ቀን ነው።
Filed in: Amharic