>
4:25 pm - Sunday December 5, 2021

የትግል ጓዶቼን ባሰብኩ ጊዜ! [ኣቶ ኣስራት ኣብርሃ - ኣንድነት ፓርቲ]

Habtamu Ayalew Andinet

ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ የማውቃቸው አንድነትን ከመቀላቀሌ ቀደም ብሎ ነው። የመድረክ ስራ አስፈፃሚ ሆኘ በምስራበት ወቅት የባለራዕይ ወጣቶች ሀያ ሁለት አከባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል አድርጎት በነበረው ስብሰባ ለመገኘት በሄድኩ ጊዜ ነበር ሀብታሙን ለመጀምሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት። የባለራዕይ ወጣቶች እንዲያ ተሰባስበው ስለሀገገር ጉዳይ ሲመክሩ ስመለከት ተስፋ ነበር የታየኝና ስሜቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር። አዲሱ ትውልድ በራሱ ጉዳይ ራሱን ችሎ ሲመክር በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ያየሁበት ቀን በመሆኑ ነው ደስታዬ እጥፍ ድርብ ያደረገው። ከስልሳው ትውልድ ተፅዕኖ የተላቀቀ ፍፅም አዲስ የሆነ አስተተሳስብ ያለው፤ በአከባቢያዊነት ወይም በቋንቋ ሳይሆን በሀሳብ በኢትዮጵያዊነት የተሰባሰበ፤ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው የየሚል አዲስ ትውልድና አደረጃጀት መሪ ሆኖ ሳገኘው ለሀብታሙና ለአባላቱ አድናቆቴን የምገልፅበት ቋንቋም ሆነ አቅም አልነበረኝም። ንግግር እንንዳደርግ ስጋበዝ “ይሄ ተቋም የወደፊት የሀገራችን መሪዎች የሚፈጠሩበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ነበር ያልኩት፤ በኋላ የተወሰኑ በአንድነት ሳገኛቸው ደስ ብሎኛል።

ሀብታሙ በተለያዩ ጊዜያት ንግግር ሲያደርግ ተመልክቸዋለሁ አንደበተ ርቱዕ የሆነ የፖለቲካ ሰው ነው፤ በተለይ በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ በቴሌብዥን ቀርቦ ያደረገው ክርክር ብዙ ሰው የሚያስታውሰው ይመስለኛል። የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠይቅ ወደ ዝዋይ በሄድን ጊዜ አንድ ወጣት በቴሌብዥን አይቼሀለሁ ሲለው ስምቻለሁ።
ሀብታሙ ባለትዳርና የልጅ አባትም ነው። ልጁ ማታ ማታ “ሀብታሙ ይመጣል ተይ በሩን አትዝጊው!” እያለች እናቷን እንደምታስቸግር ሰማሁ፣ የልጅ ነገር ልጅ ያለው ነውና የሚያውቀው እንደልጅ አባት ሆነህ ስታይው ያማል!
ዳንኤል ሽበሺ እጅግ የሚገርም ሰው ነው። ዓረና ወደ አንድነት እንዲመጣ ብጣም ይፈልግ ነበርና በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ ጋር በተደጋጋሚ ተነጋግረናል፤ከእኔ የአቶ ገብሩ አስራት ስልክ ውስዶ ተቀጣጥረው አነጋግሮታል፤ አንድነትን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ፓርቲ የማድረጉ ሂደት ጥንክረው ሲሰሩ ከነበሩ የአንድነት ሰዎች ዳንኤል አንዱ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ አንድነትን በሁለት እግሩ እንዲቆም ብዙ ፅህፈት ቤቶችና አባላት እንዲኖሩት ጊዜው፣ ገንዘቡንና ጉልበቱን ሳይሰስት የሰዋ ምርጥ የአንድነት ልጅ ነው ዳንኤል ሸሺበሺ! በበዚህ ላይ የቁጫ ህዝብ እንደህዝብ እንዲታወቅቅ ያደረገ፤ የቁጫ ህዝብ ታጋይና የሰብኣዊ መብት ተማጓች ነው።
ዳንኤል ሺበሺ ለእኔ የትግል አጋሬ ብቻ አይደለም፤ አንድ ሰፈር ስለነበር ጓደኛዬም ነው። አንዳንድ ጊዜ አየር ጤና በሚገኘው ሳሚ ካፌ እየተናኘን ሻይ ቡና እንል ነበር። ከታሰረ በኋላ ሳሚ ካፌ ጭር ብሎብኛል፤ እናም ወደዚያ አልሄድም፤ ጥሩ ስሜትም አይሰማኝም።
የዳንኤል ቤተሰቦች እሱን ለመጠየቅ ወደ ማዕከላዊ በሄዱ ጊዜ “እንዴት ነው መገናኘት አይቻልም ወይ?” ብለው ጠባቂዎቹ ቢጠይቋቸው፤ ፌስቡክ እንዲጠቀሙ ስለተፈቀደላቸው በፌስቡክ ተከታተሉ እንዳሏቸው ሰማሁ፤ እውነት ፌስቡክ በማዕከላዊ መጠቀም የሚቻል ቢሆን ኖሮ እኔ ራሴ እሰሩኝ ብዬ እሄድ ነበር። ምክንያቱም ውጭ ገንዘብ እየከፈልኩ ነው ኢንተርኔት የምጠቀመው። እስሩ እንደሆነ አሁንስ መቼ ነፃ ሆንኩ! በሰፊው ስርቤት አይደለ ያለሁት!
እንግዲህ እስሩ እየቀጠለ ነው፤ አንንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮነን፣ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፤ በቀለ ገርባ፣ ውብሸት ታዬ፤ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፤ ዞን ዘጠኝ፤ አብርሀ ደስታ፣ ሀብታሙ አያሌው፤ የሽዋስ ሌሎችም በርካታ ዜጎች በሽብርተኝነት ስም በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ፤ እንግዲህ ሽብርተኛ ማለት እኔ እንደሚገባኝ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ወይም ቦንብ ያፈነዳ እንደሆነ ነው! ኢህአዴግ ሽብርተኛ የሚለው ግን የእርሱን ስርዓት በሰላማዊም ሆነ በማነኛውም መንገድ የሚቃወሙት ነው! በዚህ ጉዳይ ላይ እርሱ እንደ መንግስት እኛ እንደ ዜጋ እኮ መግባባት አልቻልንም። በመሆኑም እስርን ራሱ እንደ አንድ የሰላማዊ ትግል ስልት እንወስደው ዘንድ ነው የምንገደደው!

አብርሃ ደስታን ባሰብኩ ጊዜ!
Abrha Destaበ2003 ዓ.ም. አጋማሽ በአንዱ ዕለት መቀሌ በሚገኘው የዓረና ዋና ፅህፈት ፀሀፊዬ በአጋጣሚ ስላልነበረች ብቻዬ ቁጭ ብያለሁ። ከሰዓት ነበር፤ በዚህ ጊዜ አንድ ሰው መጣ፤ ስሙንና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሰራ ነገረኝ። በማስከተልም አባል ለመሆን እንደመጣ አስረዳኝ፤ እኔም የፓርቲውን ህገ ደንብና ፕሮግራም በመሰጠት በመጀመርያ እነዚህን አንብብና ከዚያ የአባልነት ፎርም ትሞላለህ አልኩት። ቀድሞ አግኝቷቸው ኖሮ አይቸዋለሁ አለኝ። እንግዲያውም በጣም ጥሩ ብዬ የአባልነት ፎርም ሰጥቼው ሞላ። ያ ሰው አብርሃ ደስታ ነበር። ከዚያ በኋላ በተመደበበት መሰረታዊ ድርጅት ውስጥ በንቃት ከመሳተፉም በላይ ለአባላት ስልጠና በመስጠት በእኩል ጥሩ አስተዋፅኦ ማድረግ ጀምሮ ነበር። ከዚያ በኋላ እኔ ወደ አዲስ አበባ በመምጣቴ በየጊዜው መገናኘታችን ቢቀርም አዲስ አበባ ሲመጣ አንድ ሁለት ጊዜ አግኝቼዋለሁ፤ ሁልጊዜ ስንገናኝ ባደረግናቸው ውይይቶች ጥሩ ተግባቢና ሀሳብ ለመቀበል የማያዳግትው ሰው ሆኖ ነው ያገኘሁት። በነገራችን ላይ ብዙ ሰው የአረና አባል መሆኑ ያወቀው በአረና ሶስተኛ ጉባኤ አመራር ሆኖ በተመረጠ ጊዜ ነበር።
በነበረው ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የትግራይ ህዝብ፤ በተለይ ደግሞ ምንም የሚዲያ እድል የሌላቸው የክልሉ ገበሬዎች ድምፅ ሆኖ አገልግለዋል፤ በስርዓቱ እስኪታሰር ድረስ። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነን በትናንትናው ዕለት ሕድሮም የሚባል የአረና አባል ከወቅሮ አፅቢ ደውሎ እየደረሰባቸው ስላለው ሰቆቃ ነገረኝ፤ ሌሊት የአረና አባላት ሲደበደቡና ሲጨሁ በድምፅ የተቀዳውን አሰማኝና “አብርሃ ነበር ድምፃችን፤ እሱ ታሰረብን” ሲለኝ እንባ ነው የተናነቀኝ። አሁን ጥያቄው ስርዓቱ አብርሃን በማሰር የህዝቡን የፍትህና የነጻነት ጥያቄ ዝም ማሰኘት ይችላል ወይስ አይችልም የሚለው ነው። በማህበራዊው ሚዲያ ብዙ አዳዲስ ወጣቶች እያየሁ ነው፤ ስለዚህ ትግሉ ተጠናክሯል ማለት ነው ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል!

 

Filed in: Amharic