>
5:13 pm - Tuesday April 20, 8455

የብዙዎችን ተስፋ ያጨለመው የሳውዲ ውሳኔ (አሸናፊ በሪሁን)

የብዙዎችን ተስፋ ያጨለመው የሳውዲ ውሳኔ

(አሸናፊ በሪሁን ከSeefar)

ሳዕዳ አህመድ የ 19 ዓመት ወጣት ነች፡፡ በትምህርትዋ ከ10 ክፍል በላይ ብዙም መግፋት ያልቻለችው ሣዕዳ ቤተሰቦችዋን አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በመሸጥ በምታገኛት ገቢ ትደግፋለች፡፡ የምታገኛት ትርፍ ብዙም ህይዎትዋን የማይለውጥ መሆኑ ከተረዳች ወዲህ ከንግድ የሰበሰበቻትን ጥቂት ጥሪት ሰብስባ እንደሌሎች ጎደኞችዋ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ ሂደቱን ከጀመረች ወራትን ተቆጥረዋል፡፡ ከደቡብ ወሎ ርዕሰ መዲና ደሴ በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐይቅ ከተማ ያደገችው ሳዕዳ ፊት ታዲያ ሁሌም ፈገግታ አይለየውም፡፡ ከሰሞኑ የሰማችው ዜና ግን የሳዕዳን ፊት አስከፊ ፀዳል አልብሶታል፡፡ ሳዕዳ ከወራት በፊት ነበር ሳውዲአረቢያ ለመሄድ ፕሮሰስ የጀመረችው፡፡ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥም ወደ ሳውዲ በህጋዊ መንገድ ለመሄድ የሚያስፈልጎትን በቤት ሰራተኝነት የስራ የስራ መስክ ስልጠና ወስዳ ውየብቃት ማረጋገጫ ያገኘች ሲሆን ፣ የቅድመ ጉዞ ስልጠና ወስዳ ው ሰርተፊኬትበመያዝ ቪዛዋን በእጆ አስገብታለች፡፡ ዕቅድዋም ከቤተሰብዎችዋ ጋር ጥቂት የስንብት ጊዜያን በማሳለፍ ወደ ሳውዲ አረቢያ ማቅናት ነበር፡፡ ከሰሞኑ የሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገሯ ለስራ ለሚገቡ ኢትዮጵያውያን የሰጠችውን ቪዛ መሰረዟን እና ሰራተኞችን መቅጠር ለጊዜው ማቆምዋን ማስታወቅዋን ተከትሎም የሣዕዳ ህልም እና እና ተስፋ በድንገት ጨልሞል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ የስራና ሰራተኞች ሚኒስቴር ቪዛው የተሰረዘው ከኢትዮጵያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በስራ ቅጥር ላይ ስምምነት ባለመደረሱ ነው ብሎል። በዚህም ምክንያት ባለፉት ጊዜያት ሳዑዲ አረቢያ መድረስ ያለባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች መቅረታቸው ታውቋል።ሳዑዲ አረቢያ በቅጥር ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ሰፊ ልዩነት መኖሩን ከመግለጽ ባሻገር ዝርዝር መረጃ ለመስጠጥ ፈቃደኛ አይደለችም።ልዩነቱ ግን ጥልቅና ሰፊ መሆኑን የስራና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል። የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያ በኩል ለዜጎቿ የጤንነት ምርመራ ማዕከል ለመመስረት ፍቃደኛ አይደለችም ሲል ስምምነቱ እንዳይደረስ ካደረጉ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያኑን ቪዛ ከሰረዘች በኋላ ሀገሯ ገብተው መስራት ከፈቀደችላቸው 19 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያን ማስወጣቷን ተዘግቧል፡ የቤት ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ እንዲልኩ በሳዑዲ መንግሥት ፈቃድ ያገኙት አገራትም ፊሊፒንስ፣ ኒጀር፣ ህንድ፣ ፓኪስታን ባንግላዴሽ፣ ሲሪላንካ፣ ቬትናም፣ ኡጋንዳ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ሌሎች አገሮች መሆናቸውንም ታውቋል፡፡

በቅርቡም ነበር ሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ ስምምነት ውል ፈጽመውና በፓርላማዎቻቸው አፅድቀው ስራ ለመጀመር የተስማሙት፡፡ ሳውዲ አረቢያ በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በመቀበል ቀዳሚዋ አገር ነች፡፡ በስምምነቱ መሰራት ከሳውዲ አረቢያ መንግሰት ለሰራተኞች በወር እስከ 1000 የሳውዲ ሪያል ለመክፈልም ስምምነት ላይ ተደርሷ ነበር ፡፡ በቅርቡም በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በህጋዊ ሰራተኛ እና አሰሪ ኤጀንሲዎች በኩል ለመውሰድ የተለያዩ ቅጥሮችን በማከናወን ላይ ነበርች፡፡ በድንገት በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረው አለመስማማትም ስደተኞች ህገወጥ መንገድን ተከትለው ወደ አረብ አገራት እንዲሰደዱ እና እንዲፈልሱ የበለጠ የሚያበረታታ ነው፡፡ ሣዕዳ እና መስሎችዋም ሳውዲ ለመሄድ ህጋዊውን መንገድ ተከትለው ብዙ ደክመዋል ብዙም ወጭ አውጥተዋል፡፡ የሁለቱ አገራት ስምምነት መፍራስም ነገ ያልፍልናል በሚል ወደ አረብ አገራት በመሄድ የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ህይዎት ለመቀየር ተስፋ ያደረጉትን የብዙዎችን ህልም የሚያጨልም ይመስላል፡፡
ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ስምምነቱን ለማደስ እና አዲስ ስምምነት ላይ ለመድረስ የተቻላቸውን ጥረት ቢያደርጉ መልካም ነው እንላለን ፡፡

Filed in: Amharic