>

ከ109 ዓመት በፊት የታተመ የመጀመሪያው  የአፍሪካ  ልቦለድ ደራሲ ፕ/ር  አፈወርቅ  ገ/ኢየሱስ  (በየሺሃሳብ  አበራ)

ከ109 ዓመት በፊት የታተመ የመጀመሪያው  የአፍሪካ  ልቦለድ ደራሲ ፕ/ር  አፈወርቅ  ገ/ኢየሱስ 
በየሺሃሳብ  አበራ
አፍሪካ በ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከባሪያ  ንግድ  እስከ ቅኝ ግዛት  ወረራ ድረስ  የአውሮፓውያን  ተስፋፊዎች  መፈንጫ  ሆና ቆይታለች፡፡
በዚህም  የተነሳ  አፍሪካ  በአብዛኛው የራሷ ባህል፣ስነጽሁፍ  እና  ቋንቋ  እንዳኖራት ተጽዕኖ አሳርፎባታል ፡፡ስዋህሊኛ  እና  አማርኛ በቅደም  ተከተል በተናጋሪ ብዛት  የአፍሪካ  ቀዳሚ  ቋንቋዎች  ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ  የምስራቅ አፍሪካው  ስዋህሊኛ ቋንቋ  በእንግሊዝኛ ፣ፈረንሳይኛ  እና  በአረብኛ  ቋንቋዎች ስለተዋጠ  የራሱን  ስነጽሁፍ ና ባህል ማሳደግ አልቻለም፡፡
አማርኛ ግን  የቅኝ  ግዛት  ሰለባ  ስላልሆነ  የራሱን  ከግዕዝ  ፊደላት ጨምሮ  የራሱን  ስነ ልሳናዊና  ስነጽሁፋዊ  ይዘት አበልፅጓል፡፡
የፕሮፊሰር  አፈወርቅ  ገብረ ኢየሱስ ጦቢያ  ልቦለድ መጽሃፍ  ከዛሬ 109 ዓመት በፊት በ1900 ዓ›ም. በሮም  ሲታተም  የመጀመሪያው  የአፍሪካ  ልቦለድ ሆኗል ፡፡
የአፍሪካ ነባር  የልቦለድ  ስነጽሁፍ  ዘውግ ጀማሪው ፕሮፊሰር አፈወርቅ  ገብረኢየሱስ  እንደሆኑ ምሁራን ይስማማሉ፡፡
ፕሮፊሰር  አፈወርቅ  ገብረኢየሱስ  በጣሊያን  ሀገር  የአማርኛ  ቋንቋ  መምህር ከመሆናቸውም  በላይ  በአማርኛ ፣በግዕዝ  እንዲሁም በአፍሪካ  ቋንቋዎች  ጥናት  የመጀመሪያው  ፕሮፊሰር  ናቸው፡፡
ከባህር ዳር  ምዕራባዊ  አቅጣጫ  ጣና ሀይቅን ተጎራብታ በምትገኘው ከቡና እና ፍራፍሬ መንደሯ ዘጌ  በ1860 ዓ ም የተወለዱት ነጋድራስ  አፈወርቅ ገብረኢየሱስ  በአፄ  ምኒልክ  ተመርጠው  በሮም ከተማ  ቋንቋ  አጥንተዋል፡፡
አማርኛ፣ግዕዝ፣ጣሊያንኛ  እና  ፈረንሳይኛን አቀላጥፈው የሚናገሩት  አፈወርቅ  በምኒልክ  ቤተመንግስት  በአስተርጓሚነት  እና  በሰዓሊነት  አገልግለዋል፡፡የውጫሌን  ውል አንቀፅ 17 ጣሊያንኛውን  ክፍል የአማርኛ ትርጓሜ  ለእነ እቴጌ ጣይቱ በማስረዳታቸው የጣሊያን  ሴራ ተደርሶበት ለአድዋ  ጦርነት ምክንያት ሆኗል፡፡
የእቴጌ  ጣይቱ ዘመድ የሆኑት ፕሮፌሰር አፈወርቅ  ገብረኢየሱስ የነጋድራስነት ማዕረግም  ነበራቸው  ፡፡ፕሮፊሰር አፈወርቅ   የአፄ ምኒልክን  የመንግስት  ምስረታ ታሪክ በአካል ተገኝተው ከትበዋል፡፡
 የቤተክርስቲያን  ሰዓሊም  የነበሩት  ፕሮፌሰር  አፈወርቅ  ጣሊያናዊ  ሚስት  አላቸው መባሉ እና  እምነታቸውን  ወደ ካቶሊክ መቀየራቸውን  እቴጌ ጣይቱ  በመስማታቸው  ቤተመንግሥት  እንዳይደርሱ  ተወስኖባቸዋል ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ፕሮፌሰሩ ቤተክርስቲያን  እንዳይገቡ እቴጌ  ጣይቱ  ዕገዳ  አድርገውባቸው ነበር፡፡
በኋላም የገቢዎችና  ጉምሩክ  ሀላፊ  የነበሩት  ነጋድራስ ወደ ጣሊያን ሮም ኮበለሉ፡፡በስደት እያሉም  የአፍሪካን  ቋንቋዎች  በስፋት አጥንተዋል ፤አስተምረዋል፡፡
በታሪክ እና  ባህል፣በስነጽሁፍ  እና  ስነ ስዕል  የሀገር  ባለውለታ  የሆኑት ነጋድራስ አፈወርቅ  በ 1933 ዓ .ም. ከጣሊያን ዳግም  ሽንፈት በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ፡፡
መስከረም 15 ቀን 1939 ዓ ም  በ 79 ዓመታቸው  ከዚህ  ዓለም  በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረኢየሱስ በአማርኛ  የስነጽሁፍ  ታሪክ  ውስጥ የመጀመሪያው  የአማርኛ  ልቦለድ  ደራሲ  ብቻም  ሳይሆኑ  በአፍሪካም  የመጀመሪያው  የልቦለድ  ደራሲም ያደርጋቸዋል፡፡
Filed in: Amharic