>

የዶ/ር አብይ አባት አህመድ አሊ አረፉ!!! (ሞሀ ሞሰን ሞሀመድ)

የዶ/ር አብይ አባት አህመድ አሊ አረፉ!!!
ሞሀ ሞሰን ሞሀመድ
ከጅማ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በደረሰኝ መረጃ የጠ/ሚር አብይ አህመድ አባት አቶ አህመድ አሊ በICU (ከፍተኛ ክትትል የሚደረግበት ክፍል) ለአንድ ሳምንት ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ሰባት ሰአት ገደማ አርፈዋል። ከዚህ ቀደም የህክምና ክትትል ሲያረጉ የነበረው አዲስ አበባ በሚገኘው የኮርያ ሆስፒታል ሲሆን “ሀገሬ ሄጄ እዛ መታከም እፈልጋለሁ” ብለው ወደ ጅማ ያቀኑት በቅርቡ ነበር ተብሏል። አቶ አህመድ 91 አመታቸው ነበር።
—-
 * አህመድ አሊ ያልተዘመረላቸዉ የሐገር ዋርካ
የአባ ደብስ አባ ፊጣ ልጅ፤ የጠቅላይ ሚኒስትራችን የዶክተር ዐብይ አሕመድ አባት – አህመድ አሊ ወይም በክብር ስማቸው አባ ፊጣ። በአካባቢያቸው እጅግ የተከበሩ ሽማግሌ ሽማግሌ ናቸው። ክብሩ ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን፣ መረቱ ጥልቅ! ነገር ግን ብዙም የማናውቀው የሐገር ውለታም ጭምር ነው።
ተወልደዉ ላደጉባት በሻሻ የነበራቸዉ የባለቤትነት ስሜት በእጅጉ የሚደነቅ ነዉ፡፡ አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከሀይለስላሴ ጋር በአከባቢዉ ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡ …
በበሻሻ ለተሰሩ በርካታ መሰረተ ልማቶችም የገዛ መሬታቸዉን አሳልፈዉ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ክሊኒክ፣ የስልክ አገልግሎት የሚሰጠዉን ስልክ ቤት፣ ትምህርት ቤት እና ሌሎችም አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች እንዲሰሩ፣ ውድ የሆነዉን  የቡና ተክል መሬታቸውን ያለማቅማማት አሳልፈዉ ሰጥተዋል፡፡
እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ የተረጋጉትና ብዙ የማያወሩት አባ ፊጣ፣ ለሐገር የዋሉትን ትልቅ ውለታ ቀለል አድርገው ነው የሚያወሩት:-
“ያኔ ከተማዋ ምንም ሰዉ አልነበረባትም፡፡ ሳር መሬት ብቻ ነበር፡፡ … ከተማዋ ብዙም ሳትደራጅ ጣሊያን መጥቶ አንዴ አፈራረሳት፡፡ ጣሊያን ካፈራረሳት በኋላ፣ የኃ/ስላሴ መንግሥት ሲመለስ እሷም ዳግም አገገመች፡፡
በዚህ ሁኔታ ነው  እንግዲህ በወቅቱ ትምህርት ቤት ስላልነበር፣ ልጆች ትምህርት አጡ፡፡ ቀደም ሲል ት/ቤት እዚህ አከባቢ አልነበረም፤ ስለዚህ ት/ት ቤት ይቋቋም ሲባል፣ እሺ ደስ ይለኛል፤ ይቋቋም ብዬ፣ የኔም ልጆች የአከባቢዉ ህብረተሰብም ይማሩበት ዘንድ የራሴን መሬት ሰጠሁ፡፡ ስለዚህ ለት/ቤት የራሴን ቤት በመስጠት፣ ዘማቾች ሲመጡ በር እና መስኮት በመግዛት፣ ተጨማሪ ቤት ሠርተን ልጆች እንዲማሩ አድርገናል፡፡ …

በተጨማሪም ለመስጂድ መስሪያ፤ ለስልክ ቤት እና ለክሊኒክ መስሪያ የሚሆን መሬት ሰጥቻለሁ፡፡ መንገድም በወቅቱ ስላልነበር ለከተማይቱ መንገድ መስሪያ ቦታ ሰጥተቼ መንገድ ተሠርቶላታል፡፡”

ከሰውዬው መፅሀፍ የተወሰደ መረጃ 
Filed in: Amharic