>
10:03 am - Wednesday November 30, 2022

ጀነራል ሰዓረ የተገደሉት የት ነው ?  (ዘመድኩን በቀለ)

ጀነራል ሰዓረ የተገደሉት የት ነው ? 
 
     ዘመድኩን በቀለ
★ “ በመኖሪያ ቤቱ ሲሠራ ባህርዳር ለከተማው አረጋግቶ ለህዝቡ አስቦ አረጋግቶ ቤቱ ከመጣ በኋላ ነው የተገደለው። ተዘጋጅቶ ነው የተገደለው ”
የዐይን እማኝ ቤተሰብ
ባህርዳር ወይስ አዲስ አበባ ? ቪድዮው ፍንጭ ይሰጣል። 
•••
የጀነራል ሰዓረን ሞት በተመለከተ ከመንግሥት አፍ እስከአሁን ስንሰማ ከነበረው የተለየ አዳዲስ መረጃዎችን አሁን አሁን እየሰማን ነው። ኢንተርኔቱ ሲከፈት ደግሞ የበለጠ መረጃ ከህዝብ ይጎርፋል ብዬ ተሰፋ እናደርጋለን።
•••
መንግሥት ጀነራል ሰዓረ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው ከጓደኛቸው ጀኔራል ገዛኢ ጋር በመጫወት ላይ በነበሩ ሰዓት በአጃቢያቸው ምክንያት መገደላቸውን ነው የነገረን። እዚህ ላይም ቢሆን ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም። ሃገር ቀውጢ ሆኖ፣ የተባለው መፈንቅለ መንግሥት በባህርዳር እየተካሄደ የሃገሪቱ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም እንዴት ወደ ቤታቸው ሄደው ከጓደኛቸው ጋር የመጫወቻ ጊዜ አገኙ የሚሉ አሉ። ይሄን እንተወውና ሌላ ጥያቄ እናንሳ። ከዚያ በፊት ግን አንድ ሰው ለደሩ ከሰጠው ፍንጭ እነሳና የራሴንም ጥያቄ በማከል ለመጻፍ ልሞክር።
••• ከባህርዳር እንጀምር። 
በባህርዳር ለስብሰባ የተቀመጡት ሰባት የብአዴን አመራሮች መሆናቸውን ራሳቸው ከሞት የተረፍን ነን ያሉ ግለሰቦች በሚድያ ቀርበው ሲናገሩ ታይተዋል። ልብ በሉ ተሰብሳቢዎቹ ሰባት ሰዎች ናቸው። ስብሰባው የተጀመረው ደግሞ በኢትዮጵያውያን የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ነው ብለዋል። ከዚያም ከአንድ ሰዓት በኋላ 11:00  ሰዓት መሆኑ ነው፣ ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና ወታደሮቹ ሊገድሉን መጡ ይላሉ።
•••
እንደእነዚህ ሰዎች አባባል በነበሩበት ቢሮ ውስጥ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረና ሦስት ጓዶቻቸው እንደተመቱ ይናገራሉ፣ ( የተኩስ ልውውጡ ለምን ያህል ሰዓት ቆየ ? ) ሠላሳ ደቂቃ — አርባ ደቂቃ — አንድ ሰዓት — ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አልተናገሩም። ከዚያም እንዲህ ይላሉ ” አንዱ ጓዳችን ስለቆሰለብን ቢሮ ውስጥ የነበረውን መጋረጃ ቀደን ቁስሉን ለመሸፈን ሞከርን ” ይላሉ ፣ ይህ ምንን ያመለክታል፣ በቢሮ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ ወስደዋል ማለት ነው።
•••
የተረፉት ሰዎች ከሞቱት ሰዎች እንዴት እንደተረፉ የሰጡት መረጃ የለም። አንደኛው አቶ እዘዝ ገዳዮቹን አላስገባ ብለው በር ስለያዙ ነው ይላል። ሌላኛው ለመደበቅ ስንሯሯጥ ነው ይላል። [ የሄ በራሱ ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። በተለይ ከጥይት እሩምታ ተረፍን ያሉት ሰዎች በምን ዓይነት ተዓምር እንደተረፉ ወደፊት ኔትወርኩ ሲለቀቅ አብረን ይምናየው ይሆናል ]  የኤፍኤስአሩ ጉዳይም በድጋሚ ይነሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ……
እነዚህ ከሞት የተረፉት ሰዎች አዲስ አበባ ተደዋውለው የፌደራል ፖሊስ እስኪመጣላቸው ( ዐብይን ጨምሮ ማለት ነው ) ምን ያህል ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል መገመት አያቅትም። ከአዲስ አበባ ባህር ዳር ያለው ርቀት 330 ኪ ሜ ነው፣ በፕሌን ከሆነ ፈጣኑ ሰአት አንድ ሰአት ነው፣ እሺ በሄልኮብተር ከሆነ በግምት ከ30 ,እስከ አርባ ደቂቃ ይወስዳል። እንግዲህ ሰዓቱን ማስላት ነው።
•••
እንግዲህ ጀነራል ሰዓረ የተገደሉት ከባህር ዳሩ ክስተት ከሰዓታት በኋላ እንደሆነ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለVOAም ሆነ ለሚድያዎች ያደረጉትን ኢንተርቪው መመልከት ይቻላል።  እንዲያውም ደግሞ አንዳንድ የመንግስት ሚዲያዎች ሲናገሩ ጀነራሉ የተገደሉት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት እንደሆነ በግልጹ መግለጫ ሰጥተዋል።
•••
እሺ ። እንግዲህ ጠሚዶኮ ዐብይ ጀነራሉ እንደተገደሉ በሚድያ ቀርቦ የተናገረው ከምሽቱ 12:30 አካባቢ ነው።  which means ሰውየው ሳይገደሉ ዐብይ እንደሚሞቱ ያውቅ ነበር። ወይም ጀነራሉ የተገደሉት አዲስ አበባ ሳይሆን ባህር ዳር ነው የሚል መላምት እንዲፈጠር ያደርገዋል ማለት ነው። በዚህ ላይ ገዳይ የተባለው ጠባቂ በጠሚዶኮ ቢሮ መግለጫ በቁጥጥር ስር መዋሉ ከተነገረ በኋላ፤ በፖሊስ ኮሚሽነሩ ደግሞ ራሱን ማጥፋቱ ከተነገረ በኋላ ጫጫታ ሲበዛና እንዴት ይሆናል የሚል ጥያቄ ሲነሳ አይ ሞቷል ያልነው በስህተት ነው ገዳዩ ተመትቶ ሆስፒታል ነው ያለው የሚል መግለጫ ለመስጠት ተገደዋል። ይሄ ገዳይ እንዳያርግና ጉድ እንዳይሠራቸው፣ ወይም እንደ ኮንዶሚንየሞቹ፣ እንደ መርከብና አውሮፕላኖቹ እንዳይሰውርና አጃኢብ እንዳየሰኘን ያሰጋል።
•••
ምንአልባት ዐቢይ ጀነራሉን ወደ ባሕርዳር እንሂድ ብሎ ይዟቸው ሄዶ እዚያ ደርሰው አፍርስ አታፍርስ እያሉ ሲጨቃጨቁ በተፈጠረ ግጭት ጀነራሉ ተገድለው አስከሬናቸው ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ይሆን ወይ? ጥያቄ ነው እንግዲህ። ይህ እንዲህ ከሆነና ጀነራል ሰዓረ ባህርዳር ከተገደሉ ጡረተኛውስ ሟች ጄነራል የት ነው የተገደሉት?
•••
ጀነራሉ ባህርዳር እንደነበሩ ግን ይሄ ቪድዮ ጮክ ብሎ ይናገራል። ለምን ሄዱ፤ ማን ገደላቸው የሚለውን ግን ጊዜና ኔትወርክ ሲለቀቅ አብረን የምናየው ይሆናል።
•••
በቪድዮው ላይ የሚታየው የሟች ቤተሰብ የሆነው ሰው ደግሞ እንዲህ ነው የሚለው። “ በመኖሪያ ቤቱ ሲሠራ ባህርዳር ለከተማው አረጋግቶ ለህዝቡ አስቦ አረጋግቶ ቤቱ ከመጣ በኋላ ነው የተገደለው። ተዘጋጅቶ ነው የተገደለው ” ሲል ይታያል። እንዴት ነው ማረጋጋት ማለት። መቼ ሄዶ መቼ ነው የመጣው። ባህርዳር እኮ ፒያሳ አይደለም። አብይ 12 ሰዓት መግለጫ ሲሰጥ ጄነራሉ እኮ አልሞቱም ማለት ነው። እንደዚያ ዓይነት ተኩስ ውስጥ የዋለ ሰውስ በምን ፍጥነት ወደ አዲስ አበባ መጣ? የሟቾች አስከሬን መች ተነሳና። ሟቾች እኮ የ50 ሚልየን ህዝብ መሪዎች እኮ ናቸው። እንዴት ነው ነገሩን አቅልለው ዐብይን ባህርዳር ጥለው እሳቸው ሻይ ለመጠጣት ወደ ቤታቸው የሚመጡት?
•••
ጀነራል ሰዓረ ላይ የትግራዩ የደርግ ወታደር ልጅ ዳንኤል ብርሃነ በፌስ ቡክ ገጹ እንደዛተባቸው አይተናል። የራያ ተወላጅ ስለሆኑ እንደ ከሃዲም የሚቆጥሯቸው ብዙ የትግራይ አክቲቪስቶች እንዳሉም ሰምተናል። ህውሓት ራሷም እንደከሃዲ እንደቆጠረቻቸውም ተመልክተናል። በዛሬው የአስከሬን አሸኛኘት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙትና ምስክርነት የሰጡት ጀኔራል ጓደኛቸው ጀነራሉ ለዐቢይ መንግሥት በማገልገላቸው እንደ ከሃዲ መቆጠራቸውን በግልጽ ሲናገሩ ተደምጧል። ይህን ሲናገሩም የቴሌቭዥን ካሜራው በጄነራል ሳሞራ የኑስ ላይ አተኩሮ ሲቁነጠነጡ ያሳይ ነበር።
ሻሎም !  ሰላም !
ሰኔ 18/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic