>

ያሳደገን ኢትዮጵያዊው አማራ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ታቦት፣ ሙሽራ፣ ሰንደቅ አላማና አስከሬን  ያከብራል!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ያሳደገን ኢትዮጵያዊው አማራ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ታቦት፣ ሙሽራ፣ ሰንደቅ አላማና አስከሬን  ያከብራል!!!
አቻምየለህ ታምሩ
ኸርማን ኮህን  የዐቢይን መግለጫ ተከትሎ አሳምነውን ሲወነጅለው ወሎዬ ብሎ ሳይሆን  «ለሰባት መቶ ዓመታት  የኖረውን የአማራ የበላይነት ለመመለስ የተነሳ ቀቢጸ ተስፈኛ አማራ»  በሚል ነበር!!
ደብረታቦር ብንወለድ ጋይንት፤ ላሊበላ ብንወለድ ዳንግላ፤ ሐረር ብንወለድ ሸዋ ጠላቶቻችን እየገደሉን ያሉት  አማራ ብለው ነው። የትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ይወለድ፤ የትኛውንም ሃይማኖት ይከተል አማራ አማራ ነው። የሮማን ፕሮችስካ [ኢትዮጵያ የባሩድ በርሚል የሚለውን መጽሐፍ የጻፈው]  ተማሪዎች የሆኑት የአማራ ግንባር ቀደም ጠላቶቹ ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ በጠላትነት የፈረጁት አማራውን በሙሉ ቢሆንም ዋነኛ ጠላታችን ብለው የለዩት ግን ለረጅም ጊዜ የገዛን የሚሉትን የሸዋ አማራ ነበር። አሳምነው ጽጌ የወሎ አማራ  ነው። የነመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት  ኸርማን ኮህን ግን  የዐቢይን መግለጫ ተከትሎ አሳምነውን ሲወነጅለው ወሎዬ ብሎ ሳይሆን  «ለሰባት መቶ ዓመታት  የኖረውን የአማራ የበላይነት ለመመለስ የተነሳ ቀቢጸ ተስፈኛ አማራ»  ብሎ ነበር። ስለዚህ በጠላቶችቻን እይታ አንድ  አማራ የሆነውን የኅልውና አደጋ የተጋረጠበት ሕዝብ እኛ  ተማርን የምንል ሰዎች ያልተጣራ የጠላት ወሬ እያስተጋባን  አናደናግረው።
ያሳደገን ኢትዮጵያዊው አማራ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ታቦት፣ ሙሽራ፣ ሰንደቅ አላማና አስከሬን  ያከብራል። አማራ አንድ ሰው ከሞተ  የጠላትም ቢሆን  አስከሬኑን ያከብራል፤ በሌላው አለም እንደምናየው አማራ እንኳን የራሱን አካል የጠላቱንም አስከሬን አይጎትትም፤ አክብሮ   አፈር  ያለብሰዋል እንጂ። ስለዚህ አማራውን ለመከፋፈል እየሰሩ ያሉትን  ሰዎች ያልተረጋገጠ ወሬ እየለቃቀሙ  «እነገሌ  እንዲህ ካላደረግን ብለው ነበር»  በማለት የሚያራግቡትን ሰዎች ስለ አማራው ባሕል ከማኅረሰቡ ጋር መኖር ባይችሉ እነ ዶናልድ ሌቩን የጻፉትን አንብቡና ስለ አማራ ከመዘባረቃችሁ በፊት በቅድሚያ አማራውን እወቁት  በሏቸው።
Filed in: Amharic