>

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደው እስርና አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል (ኢትዪ 360)

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደው እስርና አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል
ኢትዪ 360 
 በኢትዮጵያ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለምርመራ ትፈለጋላችሁ በሚል የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።
ለኢትዮ 360 ከየአካባቢው የደረሱት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ለጥያቄ በሚል የሚያዙ ዜጎችን ቁጥር በውል ማወቅ አልተቻለም።
በቢሾፍቱ የጠንክር ሆቴል ባለቤት፡የጎልድ ማርክ ሆቴል ባለቤት፡የቶሚ ሆቴልና የሌሎች ሆቴል ባለቤቶች ይሄ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በደህንነት ሃይሎች ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል ከተወሰዱበት አለመመለሳቸው ታዉቋል።
በሐዋሳ የኢትዮጵያ ባንዲራን፡እጃችሁ ላይ አደጋችኋል በሚል ሰበብ ወደ ምርመራ የተወሰዱ ሰዎችም ዛሬ እንዲለቋቸው ድርድር ላይ መሆናቸው ነው መረጃዎቹ የሚያመለክቱት።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ለአለም አቀፉ የዜና አውታር ሮይተርስ በአመራሩና በአባላቱ ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት እስር ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ዛሬ በቁጥጥ ስር መዋላቸው ታውቋል።
በአስራት ሚዲያ ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ወከባ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰምቷል።
የአማራ ክልል አሁንም በመከላከያ ቁጥጥር ስር ናት።ይህ ደግሞ ውጥረቱ  እንዲባባስና በሰበብ አስባቡ የሚታሰሩና የሚግርደሉ ሰዎች ቁጥር እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል ይላሉ የኢትዮ 360 ምንጮች።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በፖሊስ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የባላደራው ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ስንታየሁ ቸኮልና ሌሎች አባላት ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውን ነው የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ባልደራስ ጸሃፊ አቶ ኤልያስ ገብሩ ለኢትዮ 360 የገለጸው።
የታሳሪዎቹ ቤተሰቦችም እስረኞቹን አግኝቶ ለማነጋገር በሚደረገው ጥረት ምርምራ ላይ ናቸው የሚለው ምክንያት ፈተና እንደሆነባቸው ተናግሯል።
አንድ ሰው ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ሲውል የህግ አማካሪዬን ሳላናግር ቃሌን አልሰጥም የማለት መብት ቢኖረውም አባላቶቻችን ግን ይሄ መብታቸው እንዲገፈፍ ተደርጓል ነው ያለው።-ጠበቆቻቸው አግኝተው ሊያነጋግሯቸው ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን በመግለጽ።
የባላደራው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ስንታየሁ ቸኮል ቤት ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲበረበር መደረጉንም ነው የተናገረው።
ይሄ አካሄድ ደግሞ ትላንት ሕወሃት ኢሕአዴግ ሲያደርግ የነበረውንና ህገ ወጥ የሆነውን የፍትህ ስርአት ያስቀጠለ ነው ይላል።
በአጠቃላይ እየታዩ ያሉት የአፈናና የማዋከብ ተግባራት የለውጥ ሃይል ነው የሚባለውን አካል ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል ሲሉ መረጃውን ከተለያዩ አካባቢዎች ለኢትዮ 360 ያደረሱት ምንጮች ገልጸዋል።
*እስካሁን የታሰሩ የአማራ ወጣቶች የታወቁት ከ300 አልፏል!!!
ታደለ ጥበቡ
በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት   ያልታወቁ ወጣቶች ስላሉ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ እንደሚል ይገመታል። እስካሁን ከታሰሩት መካከል፦
 
1. ክርስቲያን ታደለ.
2.በሪሁን አዳነ፣
3.አስጠራው ከበደ.
4.ጀነራል ተፈራ
5.ኮሎኔል አለበል
6.ስንታየሁ ቸኮል
7.ጌታቸው አባቸው
8.ሲሳይ አልታሰብ ይገኙበታል።
*በጠቅላላ
1. በአዲስ አበባ 13
2.በሱሉልታ 42፣ 
3.ፉሪ ላይ 30፣
4. ጅማ 8፣
5. ናዝሬት 8፣ 
6.አሰላ 26፣ 
7.ፍቼ 11፣
8.ለገጣፎ 56፣ 
9.ምስራቅ ወለጋ 53 
10.ሰበታ 13 
11.በባህርዳር 173
12.በጎንደር 27  ሰዎች ታስረዋል።
*ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ በየወረዳው፣ባልታወቀ ቦታ የታሰሩ አሉ።ይኼ የጅምላ አፈሳ ሆነ ተብሎ የአማራን ስነ-ልቦና ለመስለብ የሚደረግ ተንኮል ነው።የትግራይ ቴሌቪዥን፣ዋልታ ቴሌቪዥን፣የውጭ ሀገራ ዲፕሎማቶች፣ኢሳትና ሌሎች የሚነዙትን ወሬ መንግሥት ሳያስቆም በየመንገዱ ወጣቶች አፍሶ ማሰር መፍትሄ ሊሆን አይችልም።
*ወጣቶች፥አክቲቪስቶች ወቅቱ ጥንቃቄ፥ብስለትና ጥበብ የሚጠይቅ ከስሜት በጸዳ መልኩ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር የገጠመንን ፈተና ልናልፈው ይገባል።በዚህ ወቅት በጎራ ተከፋፍሎ መነታረክ ለአማራ ሕዝብ ፋይዳ የለውም።እንዳየነው በየአቅጣጫው ሁሉም ጣቱን ወደ አማራ ቀስሯል።ይሄን ፕሮፖጋንዳ የምንመክተው አንድና አንድ ስንሆን ብቻ ነው።
በድጋሜ ለሞቱት ነፍስ ይማር!!
Filed in: Amharic