>
11:13 am - Wednesday December 7, 2022

የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ድምፅ ???? (ጴጥሮስ አሸናፊ)

የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ድምፅ ????
                ጴጥሮስ አሸናፊ
የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጄኔራል አሳምነው ከጋዜጠኛ ጋር ያደረጉት የስልክ ድምፅ ልውውጥ ነው በሚል አሰምቶናል። ምንም የድምፅ ቅጂው ከግዲያው 6 ቀናት በኋላና ብዙ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ አስተያየቶች ከተሰነዘሩ በኋላ የተለቀቀ ቢሆንም ገዢው ፓርቲ እንደ አንድ ማስረጃ ይጠቅመኛል ባለበት ወቅት መልቀቁ መብቱ የተጠበቀ ነው።
•••
የመረጃ ትንሽ የለውና የቀረበው የድምፅ ማስረጃ በባለሙያዎች ሳይመረመርም በዚህ ደረጃ ለገበያ ማዋሉ ብዙም አያስኬድም። የዋሆችንና ካድሬዎችን ከመሸንገል ውጪ።
•••
እነ ትራንዚስተር ገና ስራ ሳይጀምሩ በዘመነ ቫኪዩም ቲዩብ ዘመንም የድምፅ ቴክኖሎጂ ጣራ ላይ የደረሰ ነው። እንኳን በዲጂታል ዘመን በአናሎጉም ዘመን ትንፋሻችን ሳይቀር ተለይቶ ይታወቅ ነበር።
•••
ለማንኛውም በቲቪ የቀረበውን ድምፅ በመስማት ብቻ አዎ ጄኔራሉ በወቅቱ ያስተላለፈው ነው ለምትሉ የዋሃት አትቸኩሉ።
•••
በዚህ ዘመን የተሰማውን የድምፅ ፍሰት ለመመርመር  3 ድግሪ አይጠይቅም። ይህን ፅሁፍ የምታነቡ በተለይ ማትላብ የመጠቀም ልምዱ ያላችሁ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ደረጃም ያላችሁ ተማሪዎች አጠገባችሁ ባለው ኦሲሎስኮፕ የተለቀቀውን ድምፅ ፍሪኩዌንሲ( ርግብግቢት)፣ አምፕሊቲዩድና የሞገድ ርዝመት (wave length) በማየት ማረጋገጥ ስትችሉ፤ የሙዚቃ ባለሙያዎች ደግሞ የድምፁን ሬንጅ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በመከተል በቀላሉ ቴነር ወይም ባሪቶን ወይም ቤዝ መሆኑን በቀላሉ ማወቅ ብቻ ሳይሆን የሴት ሶፕራኖ፣ ሜዞ ሲፕራኖ ወይም ኮንትራልቶም አለመሆኑን መለየቱን ለእናንተ እተወዋለሁ።
•••
በአጭሩ በቲቪ የተለቀቀው ድምፅ የጄኔራል አሳምነው ሲሆን፤ ድምፆቹ ግን ጄኔራሉ በተለያዩ ወቅቶች የተናገሯቸውን በመሰብሰብ በከፍታና ዝቅታ ርግብግቢት ማጣሪያ (High pass and low pass filter) ሪዞኔት የተደረጉ ድምፆች ስብስብ ነው።  ይህም ቢሆን  ምልልሶቹ በተመሳሳይ የሞገድ ርዝመት( Wave length) ላይ የማይገኙ ሲሆን የአምፕሊቲዩድ ልዩነትም አላቸው።  በተለይ በተለይ “ካሜራ እንላክ ” የሚለውና  “ወደ ገስት ሃውስ ላኩ” የሚሉት ድምፆች ላምዳቸው ( Lambda )ትልቅና የተለየ ነው። የጄኔራሉ የተፈጥሮ ድምፅ የሚመደበው ጮህ ብሎ በጥራት የሚሰማ( Orotund) ወይም (Raucous)  ወይም (Ringing) ከሚባሉት ውስጥ ነው።
•••
ግን ድምፆቹን አሰባስቦ ፊልተር ያደረጋቸው ኢንጂነር 90/100 ይገባዋል! ጎበዝ ነው!  10% የተቀነሰበት ምናልባትም ከመሳሪያ እጥረት እንጂ የአቀናባሪው ኢንጂነር ችሎታ በማነሱ አይደለም።
•••
ግን መንግስት ለምን ራሱን ላላስፈላጊ ጭቅጭቅ የሚከተው ነገር ውስጥ ይገባል? አሁን የዚህ ሁሉ ግዲያ አርቃቂና ፈፃሚ ጄኔራል አሳምነው ነው ቢባልስ ለክልሉ ችግር መፍትሄ ተገኘ ማለት ነው? ክልሉ ውስጥ አለመግባባት እንዳለ ሲነገር የቆዬ ነው ።ያንን ችግር ወደፊት እንዴት እንፍታውና ክልሉ ወደሰላም ይመለስ የሚለው ላይ መስራት ወይስ ያልተጠና ውንጀላ በቴሌቪዥን መልቀቅ?
•••
ጄኔራሉም ቢሆን አንድን የጣቢያው ጋዜጠኛ በስልክ በማግኘት ብቻ የፈለኩት መልዕክት ይደርሳል ብለው ያስባሉ ማለት ከባድ ነው።  ጋዜጠኛው የእሳቸው ተባባሪ ካልሆነ በስተቀር በሃይል ያልተቆጣጠሩትን ሚዲያ በስልክ ይሞክራሉ ማለት አስቸጋሪ ነው። ደግሞው “በክልሉ አመራር ላይ ርምጃ ተወስዷልና” በፌዴራል ደረጃ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደርጓልን ማን አዛመዳቸው፣?
•••
ያሁኑ መንግስት ሆይ ፕሮፓጋንዳ የቀደመውንም መንግስት አልጠቀመ። ይልቅስ ዜጎችን እኩል የምታዩበት የፖለቲካ መስመር ያዙና እንደግፋችሁ።
       ለሞቱት ነፍስ ይማር !!
Filed in: Amharic