>
5:13 pm - Thursday April 18, 0757

«አፄ አብይ» በኢትዮጵያ በሮች ላይ ነውን? (መስፍን ማሞ ተሰማ)

«አፄ አብይ» በኢትዮጵያ በሮች ላይ ነውን?
Is ‘Emperor Abiy’ at the gates in Ethiopia?
ፀሀፊ፤ DW’s Ludger Schadomsky.

ትርጉም፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

ሠላም ለናንተ ይሁን!

«አዲስ የተስፋ አድማስ» “A new horizon of hope” ይላል ከአንድ ዓመት በፊት ሥልጣን ላይ የወጣው አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦፊሴላዊ የደብዳቤ ራስ ። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተከሰተው ደም መፋሰስ ኢትዮጵያ ወደ ተባበረች ዲሞክራሲያዊት ሀገር የምታደርገውን ጭላንጭል ተስፋ ሰጪ ጉዞ ብርሃኑን ያጠፋው ይሆን? አሁን ባለው ሁኔታ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። የተካሄደውን ደም መፋሰስ አስመልክቶ ግን እስካሁን ድረስ መንግሥት ብቻ ነው «መፈንቅለ መንግሥት» በማለት የሚጠራው። አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ህይወታቸውን ያጡበት የተቀነባበረ ግድያ ኢትዮጵያ ወደ ተረጋጋ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸ,ጋገር መቻሏን ብርቱ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።

 

ውድቀት፤

አንድ ነገር እርግጥ ነው። ለ2012 ዓ/ም (2020) የታቀደው ብሄራዊ ምርጫ ተግባራዊ አይሆንም። እንደውም ብሄራዊው የህዝብ ቆጠራ – ለምርጫው እንደ መሰረት እሚሆነው – ራሱ ተሰርዟል። ይህ ማለት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፅኑ ተስፋ እንዳደረገው በህዝብ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ መሪነቱ ይሁንታን አግኝቶ የተሀዶሶ አጀንዳውን ማስፈፀም አይችልም።

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠንካራ ክንድ (strongman) ደካማ ጎኑ ይህ ብቻ አይደለም። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ በደረሰበት የብሄረሰቦች ግጭት በገዛ ሀገሩ ውስጥ በስደተኞችና በተፈናቃዮች ብዛት በአህጉረ አፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ እንዲይዝ የሆነው በአብይ ዘመን ነው።

ለመሆኑ በዚህ ጥንካሬ በሌለው መሪ ሀገሪቷን ማስተዳደር ይቻላልን?

እነሆ በሀገሪቱ ሥር የሰደደው የብሄረሰብ ትምክህተኝነት አደባባይ በመውጣቱ ምክንያት ለቀዳሚው ጥያቄ ምላሽ ሌላ አይነት ትርጉም አለው። በሀገራዊ እርቅ ቲኬት ሥልጣን ላይ የወጣው ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደሩን በጡንቻ (iron fist) ሊመራ ይችል ይሆናል። የአብይ ታማኞች (loyalists) በክልሎች፤ በወታደራዊ፤ ደህንነትና መረጃ ተቌማት የሀላፊነት ቦታዎችን ወስደዋል። ወጣቱ «ሪፎርመር» ከገራገር (naivete) አመራር ወጥቶ ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ ሲጠይቁት በቆዩት ሀገሪቷ የምትመራበት «ፍኖተ ካርታ» (“road map”) ቀይሯል።

አፄ አብይ?

የዚህ ንድፈ ሀሳብ ደጋፊዎች እንደሚተነብዩት በመጨረሻ ከሙሉ የማይገሰስ ሥልጣን ጋር የመንግሥቱ መሪ (ጠ/ሚር አብይ አህመድ) ፈላጭ ቆራጥ አፄ (absolute monarch) ይሆናል። ይህ አስገራሚ ሊሆን ግን አይችልም። ራሱ አብይ አህመድ ገደብ የለሽ ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣን (extensive presidential powers) የሚለውን ሀሳብ አስቀድሞም አንስቶቷልና።
ለአሁኑ የታሰበው ባለመሆኑ ምሥጋና ይሁንና – ጉዳዩ (አፄነቱ) አሳሳቢ ቢሆንም – ለጊዜው ግን ከሀሳብነት የዘለለ አይደለም። ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞው የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ዘመን አትመለስም ለማለት ግን አይቻልም። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ «አዲስ አድማስ» (“new horizon”) የሪፎርም አጀንዳ ፍሬ እንዲያፈራ ከተፈለገ (ጠ/ሚሩ) በከፍተኛ ቁርጠኝነት ማስተዳዳር ይኖርበታል። ሆኖም አንድ መቶ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ባላባት ሀገር በሁሉም ብሄረሰቦች የተደገፈ ሲሆን ነው የለውጡ እቅድ ፍሬ ሊያመጣ የሚችለው።

********
ሰኔ 2011 ዓ/ም (June 2019)
ሲድኒ አውስትራሊያ
mmtessema@gmail.com

https://www.dw.com/en/opinion-is-emperor-abiy-at-the-gates-in-ethiopia/a-49337334

Filed in: Amharic