>
12:07 am - Thursday December 1, 2022

የላስታ ላሊበላ ህዝብ ቁጣና መልክት!!!  (ጌራወርቅ ዝናቡ)

የላስታ ላሊበላ ህዝብ ቁጣና መልክት!!! 
ጌራወርቅ ዝናቡ
“ብ/ጀ አሳምነው ሕያው ነው”
“ሌላ ጽንፈኛ ኃይል እንጂ አማራ አማራን አይገድልም”
“ብ/ጅ አሳምነው ላማራ ሕዝብ ሕይወቱን የሰጠ ጀግና ነው”
” አማራ በጠላቶቹ ሴራ አይከፋፈልም”
የኢህአዴግ  ድራማ ተመሳሳይ ናት፡፡ ማሰር ወይም መግደል የፈለገው አካል ላይ ልቦለድ ድራማ ይጽፋል፤ ቀጥሎ ደግሞ ዶክሜንታሪ ይሰራል፡፡
ታምራት ላይኔ ላይ ሲመሰክሩ የነበሩት በሙሉ ኢህአዴግ ስክሪፕቱን ሲያስጠናቸው የነበሩ ቃኤላዊ ህሊና የነበራቸው ገጽ ባህርያት ናቸው፡፡ ቀድሞው በነ ጀነራል አሳምነው ጽጌ ላይም ተደርጎ የነበረው “ የመፈንቅለ መንግስት “ ክስ ድራማ እንጂ እውነት እንዳልነበረ ጊዜው ካለፈ በኋላ ራሳቸው ከሳሾቹም ፣ ታሳሪዎቹም ነግረውናል፡፡
ያኔ በመፈንቅለ መንግስቱ ሰበብ ፣ ብዙ ሰዎችን አባረዋል፡፡ አስረዋል፡፡ ገድለዋል፡፡የድራማው ዓላም ይሄ ነበር፡፡
ዛሬም አህአዴግ ያቺኑ የተሰለቸች ድራማ እየደገማት ነው፡፡ ልዩነቱ የድራማው ፕሮዲውሰርና መሪ ቃል  መቀየሩ ነው፡፡ ያኔ ፕሮዲውሰሯ ህወሀት ነበረች፡፡ አሁን ግን የልቦለዱ ደራሲ ባለግዜው ነው፡፡የዘንድሮውን ድራማ ለየት የሚያደርገው “ የሻብያ ተላላኪ “ እና መሰል ክሊሼ ቃላቶች አለመኖራቸው ነው፡፡ሌላው ሁሉም አንድ ነው፡፡
የዶክተር ዐብይ መንግስት ድራማውን ለማሳመን የላካቸው ባለስልጣናት በሙሉ ግን ማስመሰል አቅቷቸው ሲባክኑና ህዝብን ሲያስቁ  ከርመዋል፡፡ አቶ ንጉሱ  ቪኦኤ ላይ ቀርበው “ መፈንቅለ መንግስት ያደረገው ኃይል የአማራ ብዙሃን ጣብያን ተቆጣጥሯል” ሲሉ በሰማንበት ጆሯችን፣ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ደግሞ  በስልክ ደውለው እንደነገሩትና እራሱ ካሜራ ልላክ ብሎ መነጋገራቸውን እና ማንም ጽፈት ቤቱን ለመያዝ እንዳልመጣ ነግሮናል፡፡ሁሉቱ የሚድያ ሰዎች የሰጡት የሚጣረስ መግለጫ ነበር፡
ጀነራሉን አየነው የሚሉትም ሰዎች በተመሳሳይ ሰዓት አንዱ ጽፈት ቤት አየሁት ሲል፣ ሌላጫው ደግሞ ገስታ ሓውስ አየሁት እያሉ ግራ ግብት ያለው ታሪክ ስንሰማ ከርመናል፡፡መስካሪዎቹ የድራማውን ስክሪፕት በደምብ ያጠኑ አይመስሉም፡፡
አዲስ አበባውም ግድያ ዙርያ  ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው አዲስ አበባ ነው የተገደለው ሲሉ፣ ለቅሶ ላይ የነበረ ሌላኛው ከፍተኛ የወታደራዊ ባልስልጣን ደግሞ ከባህር ዳር ሲመለሱ  ሲል ፣ ሌላኛው ደግሞ ኦፕሬሽን እየመሩ ሲል፣ ደግሞ ሌላኛው ጉደኛቸው መጥተው ሻይ ቡና ሲሉ ሲል …. ተገርመናል፡፡ ገዳያቸውም አንዴ ቆሰለ፣ አንዴ ሞተ፣ አንዴ ሃኪም ቤት ነው… ወዘተ መላ ቅጡ የጠፋው መረጃ ሲተላለፍ ነበር፡፡
ውሸት አቅም ስለሌለው አንድ ቦታ ሳይሆን ብዙ ቦታ consistency አጥቶ ራሱን አጋልጧል፡፡ የውሸቱም ዓላማ ይታወቃል፡፡
የተፈበረከችው ውሸት መሸነፏ የገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ቁጣና ርግማን ጀምረዋል፡፡ አይናችሁን ጨፍኑና ይሄን  ሴራ መፈንቅለ መንግስት ብላችሁ ካላመናችሁልኝ “ ከማን ወገን እንደሆናችሁ እለይበታለሁ” ሲሉም አስፈራርተዋል፡፡
ሰው  እኮ እውነትን የሚለካበት የራሱ ሚዛን አለው፡፡በቀቀን አይደለም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሊያውቁት የሚገባው ግን  አንድ ነገር ነው፡፡ ህዝቡም እርሶ ከማን ወገን እንደሆኑ በግልጽ እያየዎ ነው፡፡በአንድ ዓመት ውስጥ በሚዛኑ መዝኖት ክብደቶ ፣ ከቀን ወደ ቀን እየቀለለበት ነው፡፡ ማኔ ቴቄል ፋ
አማካሪዎቻቸው አስቡበት፡፡ ይሄ የሸፍጥ መንገድ ለህወሀትም አልበጃት፡፡
 ግን እኛ ሀገር ከታሪክ መማር የሚፈልግ ሰው የለም፡፡
የላስታ ላሊበላ ህዝብ ቁጣና መልክት!!! 
ቪዲዮውን ለማየት ∨ 
Filed in: Amharic