>

ቃሌ ይመዝገብልኝ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ቃሌ ይመዝገብልኝ!!!
ዘመድኩን በቀለ
በእነ ዶክተር አምባቸው ግድያ ዐቢይ አህመድን እጠረጥረዋለሁ!!!
★  አምባቸውን ከአፈር ቀላቅሎ ነው ወይራ በመቃብሩ ላይ ወይራ ተክሎ ነው እንዲህ በነፃነት የሚፏልለው!!!
•••
እንደ ዋዛ የማይታለፈው የዐቢይና የዶር አምባቸው ሙግት። 
★ አስታውሳለሁ ፦ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጋበዙበት አንድ ስብሰባ ላይ ስለ ሕገ መንግሥቱ የማሻሻያ ነጥብ አንስቶ ንግግር ያደረገው የዐብኑ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ ነበር። “ይሄ ሕገ መንግሥት ሲረቀቅ ጀምሮ የዐማራ ሕዝብ ያልተሳተፈበት ሕገ መንግሥት ነው። እናም እኛ ዐማሮች ይሄ ሕገ መንግሥት እንዲቀየር እንፈልጋለን። ለዚህም በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን” በማለት ነበር ሃሳቡን ያቀረበው።
•••
ይህን የዐብኑን ሰው ሃሳብ መነሻ በማድረግም በወቅቱ በስብሰባው ላይ ተገኝተው የነበሩት ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ “ለአንድ ክልል ተብሎ ሕገ መንግሥት አይሻሻልም” በማለት ቆፍጠን ያለ መልስ መስጠታቸውንም አስታውሳለሁ። እዚህች ጋር የጠሚዶኮን “ ለአንድ ክልል ተብሎ ሕገ መንግሥት አይሻሻልም” የሚለውን ኃይለ ቃል ያዙልኝና ተከተሉኝ።
•••
ከዚህ ንግግር በኋላ በሕገ መንግሥቱ መሻሻል ዙሪያ ጠንከር ያለ የዐቢይን “ ለአንድ ክልል ተብሎ ሕገ መንግሥት አይሻሻልም ” ድንፋታ የሚያስተነፍስ የተቃውሞ ንግግር ያደረጉት ሟቹ የዐማራ ክልል ፕሬዘዳንት የነበሩት ዶር አምባቸው መኮንንን ነበሩ። ዶር አምባቸው የ50 ሚሊየን ዐማራ መሪ እንደሆነ ያዙልኝ። ዶር አምባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እንዳልሆነ ያዙልኝ። ዶር አምባቸው የመለሰ ዜናዊን ንግግር እንደ በቀቀን ይዘው ያስተጋቡ እንደነበሩት እንደ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ህላዊ ዮሴፍ ወዘተ የቀድሞዎቹ የዐማራ ክልል መሪዎች እንደ ነጉሡ አጎንብሱ እንዳልነበረ ያዙልኝ። በቀጥታ የዐቢይን ቃል ጠቅሶ ነው ዐቢይን የተቃወመው።
★ “ ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሁ አትቆረጠምም” የምትባለዋን ይትበሃል እዚህ ጋ ብንጠቅሰው ምን ይለናል። ምንም፤ ምንም አይለንም።
እስቲ የዶክተር አምባቸውንና የዐቢይ አህመድን ሙግት እንመልከት።
“ ሌላው የወሰንና የሕገ መንግሥት ማሻሻያን በተመለከተ ነው። ሕገ መንግሥቱ መሻሻል አለበት የሚለውን አቋም መጀመሪያ ከደደኑ ውስጥ ሲወጣ አዴፓ የመጀሪያ አቋም የያዘው አዴፓ ነው። የመሻሻል አለበት። ይሄ አንቀጽ ይሄ አንቀጽ መሻሻል የለበትም የምንለው የለንም። ሕዝብ የፈለገው በሙሉ ይሻሻል ነው የእኛ አቋም። ስለዚህ ህገ መንግሥትን የማሻል ጉዳዮች ዋናው ቋጠሮአችንና ፈተናችን የሚሆነው ሌላው እንዲቀበለው ማድረጉ ነው። “ ለአንድ ክልል ብለን ሕገ መንግሥት አናሻሽልም የሚለው ትክክል አይደለም። ትክክል አይደለም። አገር ምስረታ ነው።አንድ ስለተባለ ብቻ አንድ አይደለም። ሰፊ ህዝብ ነው። እንደገና ደግሞ የአንድ ክልል ጥያቄ ብቻም አይደለም። ሌሎቹም የሚያምኑበትና የሚቀበሉት ማሻሻያ ሃሳብ አለ። ስለዚህ ሕገ መንግሥቱ ላይ መሻሻል አለበት የሚል አቋም ነው ያለን በእኛ በኩል።
•••
የትኛው አንቀጽ ነው የሚሻሻለው? ሕዝብ የሚፈልገው አንቀጽ ነው የሚሻሻለው።  በሚፈልገው መንገድ። የእኛ አቋም ሕዝባችን የሚይዘው አቋም ነው የሚሆነው። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ያየነው ፍዳና መከራ ስለነበረ ከሕገ መንግሥቱም ጋር ስለሚያያዝ የመጀመሪያ ብሬክ አድርገን ሰብረን የወጣነው እኛ መሆናችንን እንድታውቁ”  በማለት ነበር ዶር አምባቸው የዐቢይን ድንፋታ እርቃኑን አውጥተው ጉዳዩን አፍርጠው በገሃድ ያወጡት።
••••
እዚህ ጋር ሌላ ነጥብ ስበን እናምጣ። በዚህ በዶክተር አምባቸው ንግግር የሚናደደው ማነው? የሚከፋው ማነው? ጀነራል አሳምነው ጽጌ ወይስ ዐብን?  ደብረጽዮን?፣ ወይስ ጃዋር? ህወሓት ይህን የዶክተር አምባቸውን ንግግር እንዴት ነው የምታየው? ስውሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አያቶላ ሃጂ ጃዋር መሀመድስ እንዴት ነው የሚመለከተው? አስበነዋል ግን?
•••
በዚህ ላይ የዐማራ ሕዝብ ብሔረተኝነት እንቁላሉን ሰብሮ ወጥቷል። በዚያ ላይ የዐማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚኒሻው በሚገባ ሥልጠና እየወሰደ ነው። እናም ጉዳዩ “ ሕገ መንግሥቱ አይቀየርም በሚሉት በእነ ዐቢይ፣ ደብረ ጽዮንና በእነ ጃዋር በኩል ሊኖር የሚችለውን መናበብ እዚህ ጋር ማምጣት ብቻ ነው። ልብ በሉልኝ እየሞገታቸው ያለው አቶ አየለ ጫሚሶ አይደለም። ሞጓቹ ዶር አምባቸው መኮንን ነው። ስለዚህ “ ይህቺ ባቄላ ያደረች እንደሁ አትቆረጠምም ” የሚለው ይትበሃል ቢታወስ ምንም ክፋት የለውም።
•••
እዚህ ጋር ነው ከባድ የፖለቲካ ሴራ መጎንጎን የሚጀመረው።  አምባቸውን ለማስወገድ የጦስ ዶሮ ያስፈልግ ነበር። እናም የጦስ ዶሮ ተፈልጎ ተገኘ። ጀነራል አሳምነው ጽጌም የጦስ ዶሮ እንዲሆን ተፈረደበት። እዘዝ ዋሴ፣ አምባቸውና ምግባሩ ከጀነራል አሳምነው ጽጌ የተለየ አቋም የላቸውም። እዘዝ ዋሴ በልዩ ኃይሉ ምረቃ ጊዜ የተናገረው ንግግር እንዳስገደለው ፊልሙን ፈልጋችሁ እዩት። 7 ሆነው ተሰብስበው ገዳይ የተባለው እስኳድ እነ ላቀ አያሌውን ትቶ እነ አምባቸው መኮንንን የሚገድለው ምን ስላደረጉ ነው? ግድያው የተጠናና ህልም አጨናጋፊ ግድያ ነው ባይ ነኝ።
••• የአዞ እምባ ቦለጢቃ ተጀመረ። 
ከዚያ “እንዴት ሰው አምባቸው መኮነን ይገድላል? አምባቸው መኮንን እንኳን ልትገድለው ልትቆጣው የሚያሳሳ ሰው ነው። አምባቸው መኮንን ለዐማራ ህዝብ የከፈለውን ታሪክ ያወጠዋል፡፡ ይህንን ፍልቅልቅ የገደለ ጭንቅላት ራሽናል መሆን አይችልም” … … …ብሎ እነዚያን በቀደመው የፓርላማ ዘመን ማጨብጨብን ከእንቅልፍ ጋር ደርበው እንደ እከ ለሽ በማለት የሚታወቁትን፤ አሁን ደግሞ በዘመነ ዐቢይ አጨብጫቢነትን በሆነው ባልሆነው በየሄዱበት በመነፋረቅ ፓርላማ ውስጥ ጭምር ነጠላ ዘቅዝቀው ደረት እየደለቁ ፓርላማውን ለቅሶ ቤት በማስመሰል እንባ ሲራጩ እንዲውሉ ይደረግልኛል። የአዞ እምባ አለ ሌኒን። በዚህ በኩል ሚሊዮኖች በሸወዱም እኔ እንደ አንድ ዜጋ የአምባቸው ገዳይ ወይም ለአምባቸው መገደል እንደ ዋነኛ ተጠርጣሪ የምቆጥረው ጠቅላይ ሚንስትሬ ነው። አከተመ።
•••
ለዚህ ነው ዶር አምባቸው፣ ዋነኛ ተገዳዳሪው። ዘቅዞ የያዘው ሰው ከተወገደለት በኋላ በትናንትናው የፓርላማ ንግግሩ ላይ በነፃነት እየፏለለ ያለ ከልካይ  “ሕገ መንግሥቱ አይወክለኝም የሚል አካል ለምርጫ መዘጋጀት የለበትም የሀሳብ ነፃነት መብት ጥያቄንም መጠየቅ አይችልም” እያለ ሲደሰኩር የነበረው። አምባቸውን ከአፈር ቀላቅሎ ነው ወይራ በመቃብሩ ላይ ወይራ ተክሎ ነው እንዲህ በነፃነት የሚፏልለው። ከዚህ በኋላ ተገዳዳሪ የለኝም ማለት ይመስላል። እናም ዐቢይ አህመድን እጠረጥረዋለሁ።
•••
ይሄ የእኔ እይታ ነው። ይሄ የእኔ አመለካከት ነው። ይሄ የእኔ ምልከታ ነው። የእናንተ ደግሞ ሌላ ምልከታ ነው። እኔ ገዳይ ዐቢይ ነው የሚል ጥርጣሬ ነው ያለኝ። እናንተ ደግሞ ዐቢይ አይደለም ባይ ናችሁ። ሁለታችንም መብታችን ነው። እናንተ እንደ እኔ የማሰብ ግዴታ እንደሌለባችሁ ሁሉ እኔም እንደ እናንተ የማሰብ ግዴታ የለብኝም። አዲዮስ።
•••
በተረፈ የዐቢይ እርግማን እኔን አይመለከትም። እኔ ሞጋች ነኝ። እኔ ሃሳብ አቅራቢ ነኝ። እንጂ እኔ ልክ እንደ የአርበኞች ግንቦት ሰባቱ አቶ ነአምን ዘለቀ ግደሉ፣ ፍለጡ፣ ቁረጡ አልልም። ዐቢይ መልካም ሲሠራ ለማመስገን ቅሽሽ አይለኝም። ገለቶሚ እለዋለሁ። ሲያጠፋ ደግሞ እቃወመዋለሁ። ይኸው ነው።
•••
የዐብይ እግዚአብሔርና የእኔ እግዚአብሔርም አንድ አይደሉም። የአቢይ ክርስቶስና የእኔ ክርስቶስም አንድ አይደሉም። የእኔ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተጸንሶ በድንግልና የተወለደ፣ ከዘላለማዊ ድንግል ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በተዋሕዶ የተወለደ። ሞቶ የተነሣ። ዳግም በክብር ለፍርድ የሚመጣ ፈራጅ አምላክ ነው የማመልከው።
★ የእኔ ፈራጅ ኢየሱስና የእነ ዐቢይን አማላጅ ኢየሱስ ሁለቱም አይተዋወቁም። በጭራሽ አይተዋወቁም። እኔና ዐቢይን አንድ የሚያደርገን ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ነው። በዚህም እንለያያለን። እኔ ዘር የለኝም። እሱ የዘር ፓርቲ ሊቀመንበር ነው። እንዲያም ሆኖ ጨፍኑ ላሞኛችሁ ባይ እልም ያለ የአጋሮ አራዳ ነው። እሱ በኦሮሞ ስም ለኦሮሞ እየታገለ በኢትዮጵያ ስም ሲምል የሚውል ሃሳዊ ነው። እስቲ ወንድ ከሆነ የዘር ፖለቲካን በዐዋጅ ያቁም። ኦህዴድን አፍርሶ ኢትዮጵያዊ ስም ይስጠው። እንዲህ ቢያደርግ ሚልዮኖች ቆመን እናጨበጭብለታለን። ሚልዮን ኦነጎች ግን በአንድ ቀን ከዙፋኑ ላይ አሽቀንጥረው ይጥሉታል። እናም የመሪዬ እርግማኑ እኔ ዘመዴን አይመለከተኝም። አከተመ ።
•••
በእነ ዶክተር አምባቸው ሞት ግን ለእኔ ዐቢይ አህመድ አንዱ ተጠርጣሪ ነው። ተጠርጣሪ ሁሉ ግን ወንጀለኛ እንዳይደለ ግን ይሰመርበት። ምርመራ ከተጀመረ ግን ከዐቢይ መጀመር አለበት።
•••
የግድያው ቀን ከሱዳን ካርቱ በቀጥታ ባህርዳር ምን ልትሠራ ሄድክ?  ብሎ መርማሪው ምርመራውን ከአቢቹ ይጀምረው።
•••
ሻሎም !   ሰላም !  
ሰኔ 25/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic