>

የኦነጋውያን ቅጥፈት፡ እውን ኦሮሞ ብዙሃን ነው? (መስፍን አረጋ)

የኦነጋውያን ቅጥፈት፡ እውን ኦሮሞ ብዙሃን ነው?

 

ዐብይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ
ሲዋሽ የማያፍር ዓይኑን በጨው አጥቦ፡፡
መሠሪነት ቁሞ ሥጋ ለብሶ ሲሄድ
ዞር ይላል ቢጠሩት ብለው ዐብይ አህመድ፡፡

የኦነጉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ (ዋና ተገዳዳሪውን ደ/ር አምባቸውን በጀርባው ከወጋ በኋላ) ብሔራዊ ሸንጎ ቀርቦ ‹‹ኦሮሞ አላግባብ ስልጣን ይዞ ከሆነ ከኔ ጀምሮ እንጠየቅ›› በማለት በልበ ሙሉነት ተናግሯል፡፡ ይህን ያለው ደግሞ በጉምሩክ፣ በፋይናንስ፣ በአስተዳደር፣ በደህንነትና በመከላከያ ቁልፍ ቦታወች ላይ (ወንበር እንዲያሞቁ ብቻ እዚህም እዚያም ከወዘፋቸው ጥቁት አልኦሮሞወች በስተቀር) ኦሮሞወችን (ለዚያውም ጽንፈኛ ኦሮሞወችን) ብቻ አስቀምጦ ነው፡፡

‹‹ኦሮሞ /የማይገባውን/ ስልጣን አልያዘም›› ማለት ‹‹ኦሮሞ የያዘው የሚገባውን ወይም ደግሞ ከሚገባው ያነሰ ስልጣን ነው›› ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ዐብይ አህመድ በዲፕሎማሲያዊ አነጋገር ለማለት የፈለገው ‹‹ኦሮሞወች የፌደራል ቁልፍ ቦታወችን ከዘጠና በመቶ በላይ፣ የቀሩትን ቦታወች ደግሞ ከሰማንያ በመቶ በላይ መያዛቸው ቢያንሳቸው እንጅ አይበዛባቸውም›› ነው፡፡ ዐብይ ለማስተላለፍ የፈለገው ዋናው መልዕክት ግን የስልጣን ሳይሆን የቁጥር ነው፡፡ ይህ መልዕክት ደግሞ እኛ ኦሮሞወች በከፍተኛ ደረጃ ብዙሃን ስንሆን፣ የቀራችሁት ሁላችሁም ንዑሳን ናችሁ፣ ስለዚህም ወደዳችሁም ጠላችሁም በኛ በብዙሃን ሥር ትተዳደራላችሁ የሚል ነው፡፡

ኦነጋውያን እንደሚሉት እውን ኦሮሞ ብዙሃን ነው? ካማራና ከኦሮሞ በሕዝብ ብዛት ማን ይበልጣል?

 

አማራ ማለት ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ በመሳሰሉ ጥበቶች ራሱን በራሱ ሳያጠብ ጦቢያዊነቱን በማስቀደም በመላ ጦቢያ ላይ ተሰራጭቶ የሚኖር አፍ መፍቻው አማረኛ የሆነ ጦቢያዊ ማለት ነው፡፡ በዚህ ብያኔ መሠረት አማራ በጦቢያ ውስጥ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛውን ኦሮሞን በሚሊዮኖች እንደሚበልጥ ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡ በሌላ አባባል በጦቢያ ውስጥ አማራ በከፍተኛ ደረጃ ብዙሃን (majority) ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ንዑሳኖች (minorities) ናቸው፡፡ ኦሮሞ በጦቢያ ውስጥ ብዙሃን ነው የሚባለው ትርክት (narration) የኦሮሞ ጎጠኞች በመደጋገም ውነት ያስመሰሉት ኦዳ ውሸት ነው፡፡ በምንም ዓይነት ስሌት ኦሮሞ ብዙሃን ሊሆን አይችልም፡፡

♦ ኦሮምያ በሚባለው ልቦለዳዊ ክልል ውስጥ የትላልቆቹ ከተሞች ከተሜወች አብዛኞቹ አልኦሮሞወች (non-oromo) በተለይም ደግሞ አማሮች ናቸው፡፡
♦ባዲሳባ ከከተመው ኦሮሞ ውስጥ አብዛኛው በኦነጋዊ ሹሞች አድሏዊ ትብብር በወያኔና በኦነግ ዘመን የከተመ የቅርብ ሰፋሪ ነው፡፡ እንዲህም ሆኖ ባዲሳባ የሚኖረው ኦሮሞ ጠቅላላ ቁጥር ባንጻራዊ ደረጃ ሲታይ ኢምንት ነው፡፡ በሌላ አባባል አዲሳባ ውስጥ ኦሮሞ አናሳ ወይም ህዳጣን ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ ካዲሳባ ሕዝብ ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ 70% አማራ ነው፡፡ ናዝሬት፣ ደብረዘይት፣ ሐረር፣ ድሬድዋ፣ ጅማ፣ አጋሮ በመሳሰሉት ከተሞችም እንደዚሁ፡፡
♦ ያማራ ቁጥር እንጦሮንጦስ ወርዶ የኦሮሞ ቁጥር ሰማይ የነካው በወያኔ ዘመን ነው፡፡ ወያኔ ደግሞ የሐብትና የንብረት ብቻ ሳይሆን፣ የታሪክ እና የቁጥር ሌባ መሆኑን መናገር አያስፈልግም፡፡ ማጋነን ሲሻ የትግራይ ሕዝብ ይሄን ያህል ነው፣ ሐውዜን ይሄን ያህል ተጨፈጨፈ፣ አይደር ይሄን ያህል አለቀ፣ ከጎንደር ይሄን ያህል ትግሬ ተፈናቀለ እያለ የሚያጋንን፣ ማሳነስ ሲሻ ደግሞ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚገመተውን አዲሳቤ በግማሽ የሚጎመድ፣ ሲዋሽ ዓይኑን የማያሽ፣ በሐሰት ትርክት ተፈጥሮ በሐሰት ለሐሰት የሚኖር ሐሳዊ ድርጅት ነው፡፡
♦ ኦሮምያ የተሰኘው ካማራ፣ ከጉራጌ፣ ከወላይታ፣ ከጉጅ፣ ከሱማሌ ወዘተ. በተነጠቁ መሬቶች አለቅጥ የሰፋው ኢፍትሐዊ ክልል በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ሊሆን ይችላል፣ ለዚያውም ከሆነ፡፡ ይህ ማለት ግን ኦሮሞ በቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ የኦነጋውያን ጥረት ግን እነዚህን እየቅል እውነታወች ማምታታ ነው፡፡ ጥረታቸው ደግሞ በሰፊው ተሳክቶላቸው አብዛኛውን ጦቢያዊ አታለዋል፡፡
♦ ስለዚህም የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) የመጀመርያ ሥራ መሆን ያለበት የኦነጋውያንን የቁጥር ቅጥፈት በመረጃ ሰይፍ መቅጠፍ ነው፡፡ ኦሮምያ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት፣ ኦሮሞ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ አለመሆኑን ደግሞ እንመልከት፡፡
♦ በጎጠኞቹ ወያኔና ኦነግ የሚመራውን ፀራማራ አጀንዳ የሚያራምደውን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ድርጅት (Central Statistical Agency) በማጣቀስ (June 4, 2018) ዊኪፒዲያ (wikipidea) እንዳስቀመጠው፣ በ 2009 ዓ.ም ላይ የአማራ ክልል ሕዝብ በግምት 22 ሚሊዮን ሲሆን፣ የኦሮሞ ክልል ሕዝብ ደግሞ በግምት 35 ሚሊዮን ነው፡፡ ይህ መረጃ ያማራ ክልልን ሕዝብ እጅግ አሳንሶ የኦሮሞ ክልልን ሕዝብ እጅግ ያበዛ የውሸት መረጃ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡ ላሁኑ ግን ውሸቱን እንዳለ እንቀበለው ስሌቶችን እናስላ፡፡
♦በክልሉ የሕዝብ ቁጥር መረጃ መሠረት፣ ካማራ ክልል ሕዝብ ውስጥ 91% አማራ ነው፡፡ ስለዚህም ባማራ ክልል ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ 20 (= 22 × 0.91%) ሚሊዮን አማራ ይናራል ማለት ነው፡፡
♦አዲሳባን ሳይጨምር ካማራ ክልል ውጭ ቢያንስ ቢያንስ 15 ሚሊዮን አማራ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ ላማራ ጥቅም ይቆማል ተብሎ የማይታማው ነአምን ዘለቀ ደግሞ ቁጥሩን በ 12 ሚሊዮን ይገምተዋል፡፡ የማይታመነውን ነዐምንን ላሁኑ እንመነውና ካማራ ክልል ውጭ (አዲሳባን ሳይጨምር) የሚኖረው አማራ 12 ሚሊዮን ነው እንበል፡፡ ስለዚህም አዲሳባን ሳይጨምር በሁሉም ክልሎችና በድሬዳዋ ልዩ ዞን ውስጥ የሚኖረው አማራ 32 (= 20 + 12) ሚሊዮን ገደማ ነው ማለት ነው፡፡
♦ በ 2009 ዓ.ም ላይ የአዲስ አበባ ሕዝብ በግምት 7.2 ሚሊዮን ነው፡፡ ስለዚህ ያዴሳቤ አማራ ቁጥር ቢያንስ ቢያንስ 5 (= 7.2 × 70%) ሚሊዮን ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህም በጦቢያ የሚኖረው አማራ ቁጥር 37 (= 32 + 5) ገደማ ነው ማለት ነው፡፡
♦ ካማራ ክልል ውጭ (አዲሳባን ሳይጨምር) ከሚኖረው 12 ሚሊዮን አማራ ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ ግማሹ (ማለትም 6 ሚሊዮኑ) ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይኖራል እንበል፡፡ ይህ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖረውን አልአማራ (non-Amhara) (ማለትም አሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ.) ጠቅላላ ቁጠር ወደ 29 (= 35 – 6) ሚሊዮን ያወርደዋል፡፡
♦ በተለያዩ ምክኒያቶች ኦሮሞ ከኦሮምያ ክልል ውጭ እምብዛም አይኖርም፡፡ ስለዚህም በኦሮምያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አልአማራ አልኦሮሞወች (non-Amhara non-Oromos) (ማለትም አማራም ኦሮሞም ያልሆኑ ሰወች በተለይም ደግሞ ጉራጌወች፣ ትግሬወች፣ ሱማሌወች፣ ወላይታወች፣ ጌድኦወች ወዘተ.) ቁጥር፣ ከኦሮምያ ክልል ውጭ ከሚኖሩ ኦሮሞወች ቁጥር በጣም እንደሚበልጥ ግልጽ ነው፡፡ ይሁንና የመጀመርያው ቁጥር ከሁለተኛው ቁጥር ጋር እኩል ነው እንበልና፣ ከኦሮምያ ውጭ የሚኖረውን የኦሮሞ ቁጥር እንዲያካክስልን እናድርግ፡፡ በሌላ አባባል በኦሮምያ ውስጥ የሚገኙ ኦሮሞም አማራም ያልሆኑ ጦቢያውያን ቁጥር ከኦሮሚያ ውጭ ከሚኖሩ ኦሮሞወች ቁጥር ጋር እኩል ነው እንበል፡፡ ስለዚህም በድፍን ጦቢያ ውስጥ የሚኖረው የኦሮሞ ቁጥር በዛ ቢባል 29 ሚሊዮን ገደማ ነው ማለት ነው፡፡
♦ በሌላ በኩል ደግሞ በድፍን ጦቢያ ውስጥ የሚኖረው አማራ ቁጥር 37 ሚሊዮን ገደማ እንደሆነ በቁጥር (9) ላይ ተመልክተናል፡፡ በተራ ቁጥር (6) ላይ የተጠቀምነው መረጃ የበለጠ ትክክለኛ ቢሆን ኖሮ ያማራ ቁጥር 40 ሚሊዮኖች ውስጥ ሲሆን፣ የኦሮሞ ቁጥር ደግሞ ከ 25 ሚሊዮን ባልዘለለ ነበር፡፡ ስለዚህም አማራ ኦሮሞን ቢያንስ ቢያንስ በ 8 ሚሊዮን ይበልጠዋል ማለት ነው፡፡
♦ያማራ ቁጥር 37 ሚሊዮን ነው፣ የኦሮሞ ቁጥር 29 ሚሊዮን ነው፣ የትግሬ ቁጥር ደግሞ 6 ሚሊዮን ገደማ ነው፡፡ ስለዚህም ኦሮሞ ብቻውን ይቅርና ኦሮሞና ትግሬ ቢደመሩ እንኳን (29 + 6 = 35) አማራን አያህሉም ማለት ነው፡፡ የዐብይ አህመድ የኦሮሞ ብዙሃንነት እስከዚህ ድረስ ነው፡፡
♦በመሠረቱ አማራ ኦሮሞን በሚሊዮኖች እንደሚበልጥ ለመረዳት ሕዝብ ቆጠራም ሆነ ሌላ ዓይነት ስሌት አያስፈልግም፡፡ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ አርብቶ አደር የማይኖርባቸው፣ አርሶ አደሩ የበሬ ግንባር በሚያህሉ ርስቶች እጅግ ሲበዛ የተጨናነቀባቸው፣ ተራራው፣ ሸለቆው ሳይቀር ሁሉም የሚታረስባቸው ሰፋፊ ክፍለ ሀገሮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባሌ፣ ወለጋ፣ ከፋና፣ ኤሊባቡር ባብዛኛው ጠፍ መሬቶች ናቸው፡፡ በደርግ ጊዜ ሰፋፊ የምንግሥት እርሻወች የተተከሉባቸው፣ በወያኔ ጊዜ ደግሞ ለአበባ እርሻወች የተቸበቸቡት ከነዚህ ጠፍ መሬቶች እየተቆረሱ ነው፡፡ እነዚህ ክፍለ ሀገሮች በቂ ሰው ስሌላቸው አርሶ አደሮቻቸው ቡናቸውን የሚያስለቅሙት፣ ምርቶታቸውን የሚያስሰበስቡት፣ የራሳቸውን ኩርማን መሬት አርሰው ከጨረሱ በኋላ ከወሎና ከጎጃም በሚመጡ በንቀት አጠራር ጎጀ እየተባሉ በሚጠሩ (ኩሊ ለማለት ነው) ጊዜያዊ ሠራተኞች ነው፡፡ ኦሮሞወች በተወሰነ ደረጃ ተጠጋግተው የሚኖሩባቸው ምሥራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋና አሩሲ ሲሆኑ፣ እነሱም ቢሆኑ የሕዝብ ጭፍቀታቸው (population density) (ማለትም የሕዝብ ትፍፍጋቸው) ካማራ ክፍለ ሀገሮች የሕዝብ ጭፍቀት አንጻር ኢምንት ነው፡፡
♦ፀረጦቢያወቹ ወያኔና ኦነግ በዘር መደራጀት ወይም ሞት የሚሉት ወጀቡ ከተነሳ አጥለቅልቆ በሚውጣቸው ጦቢያዊ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙ እጅግ አናሳ ደሴቶች መሆናቸው እጅግ ስለሚያስፈራቸው ነው፡፡
♦በቀጥታና በተዛዋሪ አነጋገሮች እኛ ኦሮሞወች ብዙሃን ነን የሚለው ዐብይ አህመድ፣ በርግጥም የብዙሃን ኦሮሞወች አባል ከሆነ፣ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ከሚለው እስክንድር ነጋ ጋር ጦርነት መግጠም ለምን አስፈለገው?

♦ላንድ ክልል ስንል ሕገመንግሥት አንቀይርም በማለት ካማራ ክልል ሕዝብ በስተቀር ሌሎች ጦቢያውያን ሕገመንግሥቱን (ርዕሰ ሕጉን) ይደግፉታል የሚለውን መልዕክቱን ለማስተላለፍ የፈለገው ዐብይ አህመድ፣ በርግጥም አብዛኞቹ ጦቢያውያን ሕገመንግሥቱን የሚደግፉት ከሆነ፣ ሕገመንግስቱን ለውሳኔ ሕዝብ (referendum) ማቅረብ ምን አስፈራው?

♦ የነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄወች የሁሉም መልሶቻቸው የሚገኙት ካንድና ካንድ ሐቅ ብቻ ነው፡፡ ይህ ኦነጋውያንን የሚያንቅ ሐቅ ደግሞ በጠላትነት የፈረጁት አማራ ኦሮሞን በብዙ ሚሊዮኖች የሚበልጥ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሐቅ የሚያንቀው ደግሞ ኦነጋውያንን ብቻ ሳይሆን ያጼ ምኒሊክን የጥቁር አንበሶች ጥቁር ብሔርተኝነት (black nationalism of black lions) የማልኮልም ኤክስን (Malcom X) የጥቁር አፍሪቃውያን ጥቁር ብሔርተኝነትን በሚመለከቱበት ዓይን የሚመለከቱትን፣ የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ዘረኛ ሐሳብ የሚያቀነቅኑትን ኸርማን ኮኸንን (Herman Cohen) የመሳሰሉትን ፀራማራወች ነው፡፡

♦ በትልቅ ውሻ ላይ የሚቧርቀው ትንሽ ውሻ ነው፡፡ የሚቧርቀው ደግሞ ስለሚፈራ አስቀድሞ ለማስፈራራት ነው፡፡ የፈሪ ብትር ደግሞ ሆድ የሚቀትር ሰቅጣጭ ብትር ነው፡፡

♦ጃዋር ሙሐመድ በነፍጥ ዘመን በሜንጫ ለማስፈራራት የሚሞክረው፣ ሽብር የሚለቀው ግድያው ሳይሆን አገዳደሉ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው፡፡

♦ዐብይ አህመድ እነ ዐምባቸውን ባሰቃቂ መንገድ የጨፈጨፈው በዚያውም ባማራ ላይ ሽብር በመንዛት ባንድ ዲንጋ ሁለት ወፍ ለመግደል ነው፡፡

♦መንግሥታችን ተነካ ብለው ከቡራዩና ከሰበታ እየመጡባችሁ ነው ሲለን ያፍ ወለምታ ነው ብለን ብናልፍለት፣ ባንድ ጀንበር መቶ ሺወች ይታረዳሉ በማለት ያፍ ወለምታ እንዳልሆነ በትክክል አረጋገጠልን፡፡ ከሀገር መሪ ቀርቶ ከግለሰብ አፍ ሊወጣ የማይገባውን መታረድ የሚለውን ዘግናኝ ቃል የተጠቀመው ደግሞ ሆን ብሎ ነው፡፡ ቃሉ የተወረወረው ላማሮችና ላማሮች ብቻ ነው፡፡

♦ኦነግ በሻቢያና በወያኔ አንቀልባ ያደገ፣ አሁን በቅርቡ ደግሞ ባማራ ትካሻ ስልጣን የጨበጠ፣ በታሪኩ አንድም ቀን ሆነኛ ውጊያ አድርጎ የማያውቅ፣ በራሱ መቆም የማይችል መዥገር (parasite) ሲሆን፣ አመራሮቹ ደግሞ ቢወቅጡት ገለባ መሆናቸውን በደንብ ስለሚያውቁ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ /የሚያልባቸው/ ፈሪወች ናቸው፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠር ጭራቃዊ ልዩ ጦር በኦሮምያ ክልል ውስጥ አሰልጥነው፣ በሰው በላው ብርሃኑ ጁላ የሚመራውን ፀራማራ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው፣ ጀነራል አሳምነው ጽጌ ጥቂት ሺ ሚሊሻወችን ማሰልጠኑ አንበጨበጫቸው፡፡ በቸጉዌራ (che guevara) ጥብቆወች (t-shirt) እየተጀነኑ፣ ያጼ ቴድሮስን ጥብቆ ሲያዩ ቀዘኑ፡፡ የቀዘኑት ደግሞ ከፈረሱ አፍ (from the horse’s mouth) እንደሰማነው የጥቁር አንበሶች ጥቁር ብሔርተኝነት ስጋት ስላደረባቸው ነው፡፡

♦ ዕባብ ያየ በልጥ በረየ፡፡ የወያኔ ዕባብ ደደቢት ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ አማራውን እዚህም እዚያም እየነከሰ ክፉኛ ቢጎዳውም በልጥ እንዲበረይ ስላደረገው ግን በእጅጉ ጠቅሞታል፡፡ ወያኔ 27 ዓመት ባማራ ላይ ለመጨማለቅ ያገኘውን እድል ኦነግ አያገኘውም፡፡ ዘመነ ዐብይ በወራት እንጅ ባመታት አይቆጠርም፡፡
♦ ከሰኔ 15 ጀምሮ እየፈጸመው ባለው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ አስርና እንግልት ለጊዜውም ቢሆን ወታደራዊ የበላይነት የጨበጠው ዐብይ አህመድ፣ ወታደራዊ የበላይነቱን ወደ ፖለቲካዊ የበለይነት ለመቀየር በጃዋር ሜንጫ አፍ እንደራደር ማለት ጀምሯል፡፡ ድርድር የሚለው ቃል ካንደበቱ ወጥቶ የማያውቅ ግለሰብ የድርድር ሰባኪ ሆኗል፡፡ በመግደል የኃይል ሚዛንን ለውጦ፣ መገዳደል ለውጥ አያመጣም ይለናል፡፡ እሱ የኦሮሙማን ጅብ እየጋለበ፣ ጥቁር ብሔርተኞችን ጥቁር አንበሳ አትጋልቡ ይላል፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ በጭካኔ እንጅ በውጊያ የማይታወቀው ኦነግ ባማራው መነሳሳት ክፉኛ መርበትበቱን ነው፡፡ በጭፍጨፋ ያገኘው ወታደራዊ ድል ጊዜያዊ ድል ስለሆነ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ፖለቲካዊ ድል ተቀይሮ ቋሚነትን ካልያዘ በስተቀር መና እንደሚቀር አሳምሮ ያውቃል፡፡

♦ከኦነጋውያን ጋር የመደራደር ዕድል ሰኔ 15፣ 2011 ዓ.ም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አክትሟል፡፡ አዴፓ ውስጥ የተሰገሰጉ ኦነጋውያን ባማራ ስም እንደራደራለን ካሉ ደግሞ፣ ድርድሩን መቸም እንደማይቀበለውና ተደራዳሪወቹን ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ያማራ ሕዝብ ካሁኑ ግልጽ ማድረግ አለበት፡፡ በተለይም ደግሞ በባሕርዳሩ ጭፍጫፋ የሚጠረጠሩት ደመቀ መኮንን፣ ዮሐንስ ቧያለውና ንጉሱ ጥላሁን እጃቸው እንዲቆረጥ ካፈለጉ በስተቀር በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ላይ እጃቸውን ማስገባት የለባቸውም፡፡ ይህ ወሳኝ ጉዳይ የሚመለከተው በእውነተኛ ነጻ ምርጫ የተመረጡ፣ አማራ የሆኑ፣ ያማራ አመራሮችን ብቻና ብቻ ነው፡፡

♦አራዳው ዐብይ አህመድ ሲያሰኘው ፓስተር፣ ሲያሰኘው ወታደር፣ ሲያሰኘው መምሕር እየሆነ (ይልቁንም ደግሞ የሆነ እየመሰለ) በማታለል ጦቢያን የሚገድልበትን ኦነጋዊ ጥይት ራሳችን ጦቢያውያን እንድንገዛለት አድርጎናል፡፡ የእስካሁኑ ማታለል ኀፍረቱ ለራሱ ሲሆን፡ ካሁን በኋላ ቢያታልለን ግን ኀፍረቱ የኛ የራሳችን ነው (Cheat me once – shame on you. Cheat me twice – shame on me). ያልሆኑትን ነን በማለት አለቅጥ የተነፋፉት ኦነጋውያን ማንነትና ምንነታቸውን (በተለይም ደግሞ አናሳነታቸውን) በትክክል ተረድተው፣ በተራ ቁጥር (12) በተጠቀሰው እውነታ መሠረት በልካቸው የሚሰፋላቸውን ልብስ እስከሚለብሱ ድረስ፣ የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) ፀረኦነግ ትግል ባስፈላጊወቹ ዘዴወች (by any means necessary) እየተቀጣጠለ መቀጠል አለበት፡፡

♦አታላዩ አብይ አህመድ አማራውን ከትግሉ ለማዘናጋት የተለያዩ የማታለያ ዘዴወችን ሊጠቀም ይችላል፣ ይጠቀማልም፡፡ ከነዚህ የማታለያ ዘዴወች ውስጥ አንዱ የይስሙላ ሹመቶችን መስጠት ነው፡፡ ጀኔራል አደም ሙሐመድ ምንም የማይተክር ወንበር አሟቂ ነው፡፡ ሕግ አስከባሪውና ሕግ አስፈጻሚው ሙሉ በሙሉ ኦነጋዊ በሆነበት ሁኔታ፣ የዳንኤል በቀለ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር መሆን ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ አማራን ፊት ለፊት የተጋፈጠው ጥያቄ የመኖር ወይም ያለመኖር ጥያቄ ሲሆን፣ ትግሉም የሞት ሽረት ትግል ነው፡፡ ስለዚህም የትንሽ መዘናጋት ዳፋው ግዙፍ ነው፡፡

♦ ዐብይ አህመድ ጦቢያዊነትን ሽቅብ የሚያነሳው ሊፈጠፍጠው እንደሆነ ሁሉ፣ አማራውን የሚጠቅሙ የሚመስሉ ድርጊቶችን የሚያደርገው ደግሞ አማራውን ለመጉዳት ነው፡፡ እነ ደ/ር አምባቸውና ጀነራል አሳምነው በዐብይ አህመድ የተበሉት፣ መሠሪነቱን አውቀው ጉድጓድ ባለመማሳቸው ነው፡፡ ስለዚህም ይህ መሠሪ ግለሰብ ማናቸውንም በጎ የሚመስል ድርጊት ሲያደርግ፣ በዚህ ድርጊት አማካኝነት ሊያሳካ ያሰበውን እኩይ ኦነጋዊ ዓላማ አውቆ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንጅ መቸም ቢሆን መሞገስ የለበትም፡፡ በተለይም ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ይህን በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል የሚሉ አስተያየት ሰጭወችና ተንታኞች ስሕተታቸውን ሊያርሙ ይገባል፡፡ መታየት ያለበት ትልቁ ስዕል እንጅ ዝርዝሩ አይደለም፡፡ ቤትህን አፍርሶ እክሽናው የሚያስጠጋህ የሚያስብብህ እንጅ የሚያስብልህ አይደለም፡፡

♦ ሌላው የዐብይ ማታለያ ‹‹የጥላቻ ንግግር የሕግ ተጠያቂነት›› የሚለው ማስፈራሪያው ነው፡፡ ወያኔና ኦነግ ለዚህ የበቁት መረን የለቀቀ መሠረት አልባ ጥላቻ በመንዛት ብቻና ብቻ ነው፡፡ የአኖሌ ሐውልት የተሠራው እነ ዐብይ አህመድ ባሰባሰቡት ገንዘብ ነው፡፡ ጃዋርን ጃዋር ያስባለው ስድ የሜንጫ ቋንቋው ነው፡፡ ወያኔና ኦነግ ባማራ ጥላቻ የቀሰቀሱት ተደራጅቶ የታጠቀ አያሌ ጀሌ ስላላቸው፣ ተጨማሪ ቅስቀሳ አያስፈልጋቸውም፡፡ ትልቁ ስጋታቸው በጦቢያዊነቱ ተማምኖ የተኛው፣ በቁጥርም በሌላም ብዙ የሚበልጣቸው አማራ ከጦቢያዊነቱ ጋር በማይቃረነው ባማራነቱ ተቀስቅሶ፣ አማራ በመታደግ ጦቢያዊነትን ለመታደግ እንዳይንቀሳቀስ ነው፡፡

♦ፀራማራው ዐብይ አህመድ ‹‹ጥላቻ ነዥወች በሕግ ይጠየቁ›› የሚለው ጥላቻን በመጥላት ሳይሆን ላማራ ባለው ጥላቻ ነው፡፡ ዓላማው አማራን የሚቀሰቅሱ ድምጾችን ሙሉ በሙሉ ማፈን ስለሆነ፣ ሚዛናዊ ነኝ ብሎ ለማታለል ጥቂት የኦሮሙማ ቀስቃሾችን ጭዳ ሊያደርግ (ሊገብር) ይችላል፡፡ ማናቸውም አምባገነን እየወደቀ መሆኑ የሚያስታውቀው መረጃ ማፈን ሲጀምር ነው፡፡ የቤንመረብ (intenet) መዘጋት፣ የስልክ መቋረጥ፣ የማሕበራዊ ሚዲያ መወገዝ፣ የባላደራ መታፈን፣ የአብን መታደን የሚጠቁሙት የዐብይ አህመድ አገዛዝ አንድ እግሩ መቃብር ውስጥ እንደገባ ነው፡፡

♦ያደቆነ ሰይጣ ሳያቀስስ አይለቅም፡፡ በወያኔ የስለላ ድርጅት ውስጥ ቁልፍ ቦታ ላይ ተቀምጦ የወያኔን ተቃዋሚወች ሲያፍንና /ሲያድን/ የኖረው ዐብይ አህመድ፣ የኦነግን ተቃዋሚወች በውስጥም በውጭም ሊያፍንና ሊያድን ተነሳስቷል፡፡ የውስጡን አፈናና አደና አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ በሆነበት የኦነግ ፍርድ አማካኝነት እያሳካ ቢሆንም፣ የውጩን (በተለይም ደግሞ የምዕራቡን) ግን ለማሳካት የሚችለው ያማራ ቀስቃሾችን በባዶ ማስፈራርያ ማስፈራራት ከቻለ ብቻ ነው፡፡

♦ጥላቻን የሚነዙ በትክክለኛ ፍርድ ቤት ይጠየቁ ቢባል የመጀመርያው ተጣያቂ የራሱ የዐብይ ኦነግ እንደሆነ ስለሚያውቅ፣ ዐብይ አህመድ ይህን ርዕስ የሚያነሳው አልኩ ለማለትና ያማራ ወትዋቾችን (activists) ለማስፈራራት ብቻና ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ያማራን ሕዝብ ባመርቂ ሁኔታ እየቀሰቀሳችሁ ያላችሁ ያማራ ቀስቃሾች፣ የኦነጋውያንን ባዶ ጉራ ከቁብ ሳትቆጥሩ ቅስቀሳችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉበት አደራ እላለሁ፡፡ አደራ የምላችሁ ደግሞ በብርሃኑ ጁላ የሚመራው አረመኔው የኦነግ ጦር በዚች ባሁኗ ቅጽበት ያለ ርኅራኄ በሚጨፈጨፋቸው ወገኖቻችሁ ስም ነው፡፡

ጸሃፊውን  ለማግኘት mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic