>
5:13 pm - Friday April 19, 5624

ከጀነራል አሳምነው ጽጌ እስከ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ !! (ሀብታሙ አያሌው)

ከጀነራል አሳምነው ጽጌ እስከ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ !!
ሀብታሙ አያሌው
የዛሬ አምስት ዓመት ሐምሌ አንድ ቀን ህወሓት የሃሰት ክስ አቀናብራ  ወደ ምድራዊው ሲዖል ማዕከላዊ አወረደችኝ !!  ዛሬ ደግሞ  ተረኛው ግፈኛ  ኦዴፓ (የተፋቀው ኦነግ) ወንድምና ወዳጄ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ሽብርተኛ ብሎ ዘብጥያ አውርዷል።
እናም እልሃለሁ “የመፈንቅለ መንግስቱ”  ጨዋታ በጊዜ ያልገባህ  የማንንም ትንተና ተውና ኦዴፓ እየሰራ ያለውን ብቻ ተመልከት !!  ‘ጀነራል አሳምነው እና  ኤልያስ ገብሩን ያስተሳሰረ መፈንቅለ መንግስት’  ሲልህ ነገሩ እዛው ጋር አልቋል።  ባህርዳር የህዝቡን ምልክት እነ ዶክተር አምባቸውን የቀጠፈው ግድያ  ሹሩባው ተገምዶ በአዲስ አበባ ጀርባ ላይ ጀነራል ሰዓረን ለምን እንደቀጨ የሚገባህ አሁን ነው።
የሹሩባውን ጫፍ ስትከተል  ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ዝርፍፍ ሲል ብታይ እንዳትደነግጥ ፤  ለውጡ እየፈጠነ ነው ለውጡ እያማረበት ነው።
Filed in: Amharic