ወዲ ሻምበል
“አንተ የአማራ ተላላኪ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነህ” ለምትሉኝ የህወሓት ደጋፊዎች እና እንዲሁም እውነት ለማወቅ ለሚፈልጉት ወገኖቼ ይህንን መራራ እውነት የኖርኩበት እውነተኛ ታሪክ በፎቶ አስደግፌ ለመንገር እገደዳለሁ እንዲያው ከረጅሙ የህይወት ታሪኬ ውስጥ በጭልፋ ጨልፌ እንደ ማለት ነው።በደርግ ስርዓት ውስጥ በተደረገው የእርስ በእርስ ጦርነት በትግራይ ክፍለ ሃገር ከመደበኛው ሰራዊት ውጪ ፀረ ተሓህት ሆኖ የሚታገለው እራሱ የትግራይ ህዝብ ነበር።
ትሕነግ ዛሬ በእጅ ላሳደጋቸው ልጆችና እንዲሁም በደርግ ዘመን ተወልደው በትህነግ ዘመን ለጎለመሱ የውሸት ታሪክ እያስተማረ አጣሞ ቢያሳድጋቸውም እውነቱን የሚያውቁ አዛውንቶች ደግሞ ጊዜ እስኪያልፍ ያለፋል ብለው ዝምታን ቢመርጡም እኔን የሚመስሉ ግን ለህሊናችን እና ለታሪክ ብለን በእግዚአብሔር ፊትና በሰው ፊት እንመሰክራለን ታላቁ መፅሐፍ ቅዱስ “እውነት አርነት ታወጣለች” ይል የለ።ወቅት የዛሬ አርባ አመት 1970 ነው ቦታ ሰሜናዊ ክፍለ ሃገራችን አካል የሆነችው ትግራይ መቐለ ከተማ ነው አብዛኞቹ ከእኔ በስተቀር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸው የኢትዮጵያ ሰራዊት የዚያድባሬን ወረራ በሚያስደንቅ ጀግንነት ቀልብሶ ፊቱን ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ያዞረበት ጊዜ ነው የትግራይ ወጣቶች የባቶቻቸውን አገር ኢትዮጵያውያን ከወራሪዎች ከገንጣይ አስገንጣይ ለመከላከል ወታደር ሆነው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መስዋዕትነት እየከፈሉ ነው።
የእነዚህ ተማሪዎች ደግሞ ተጨማሪ እንዘምታለን መንግስትን በፍላጎታቸው በመጠየቅ ቀደም ብለው በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀው ከመቐለ ከተማ ከ20 ቀበሌዎች 240 ወንዶች 60 ሴቶች የ6ኛ ነበልባል ክፍለጦር ማሰልጠኛ የነበረው ገርገምበስ የተባለው ካምፕ ሰልጥነው ጀብሐ፣ሻእብያ፣ትህነግ፣ኢህአፓ፣ኢድዩን ለማፋለም እና ህዝባቸውን ለመሰናበት መቐለ እስቴድዬም (ባሎኒ) ትልቅ ወታደራዊ የሰልፍ ትርኢት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና በተገኙበት ሲያሳዩ ዝነኛው የትግራይ ኪነት ቡድን ጀግናው ኪሮስ አለማየሁ ከሴቶች ጀግናዋ ሶፍያ አፅብሐ በሚገርም መረዋ ድምፃቸው ኪሮስ ” ንዘክሮም ናይ ቀደም ወለዲ ሐፂራቶም ዘፅንሕዋ አዲ ናሐልዋ ብውዲ ብግዲ” ሶፍያ “ሎሚ ፅባሕ ዘይእፀፍ ቃል ኪዳና አብዬታዊት ኢትዮጵያ ወይከዓ ሞት ቆሪፅና ተልኢልና” በማለት እስቴድዬሙን በጩሐትና በጭብጨባ በእልልታ አስደመቁት እንዲሑም የኪነቱ በእድሜ ባለፀጋ የነበሩት አቦይ ስዩም እንዲህ ብለው ጎራዴ ይዘው አዜሙ “አያይ ዛጎራዴኻማ አስትያ ደሜ ደምዬ አብ ፀላዕትኻ”
