>

እነ መለስ ዜናዊ የቀበሩትን ፈንጂ  ኦህዴድ/ኦነግ እያፈነዳዳው ነው !!!  (ዘመድኩን በቀለ )

እነ መለስ ዜናዊ የቀበሩትን ፈንጂ  ኦህዴድ/ኦነግ እያፈነዳዳው ነው !!!
ዘመድኩን በቀለ 
ሲዳማዎች ሰውን ገድለው በቤንዚል በማቃጠላቸው  ክልል ተሰጥቷቸዋል ባዮች ናቸው ወላይታዎች።  
አዲስ አባባን ለኦሮሞ ለመስጠት መጀመሪያ ሲዳማን ገንጥሎ አዋሳን ለሲዳማ መስጠት የማመቻመች የሴራ ቦለጢቃ ነው የሚሉም አሉ። 
መጀመሪያ ሲዳማን ክልል ታደርግና ከዚያ በኦኤም ኤንና በኦኤንኤን ላይ የሚለፈፍላቸው ቅማንትና አገው ልክ እንደሲዳማ በአስቸኳይ ከዐማራ ይለዩ ነው ፕላን ቢ…ይቀጥላል!!
 በደቡብ ኢትዮጵያ የወላይታ የዛሬ ውሎ።
•••
ለኢትዮጵያ ባለው ፍቅር ግልገል ነፍጠኛ በመባል ከዐማራ እኩል በአባቶሮቤዎች የሚጠራው ወላይታ ዛሬ ድብልቅልቁን ሲያወጣው ውሏል።
• ስልጤ ቅልቅል የጅማ ኦሮሞዋ ወሮ ሙፈሪያት ካሚል የምትመራው ክልል እነ ጃዋር ባስቀመጡት የብጥብጥና የትርምስ መንገድ ሰተት ብሎ ሳይንገራገጭ ለመሄድ መንገድ ጀምሯል።
•••
ለሲዳማ ሊሰጥ የታሰበውን የክልልነት መብት እኛስ የምንነፈገው ለምንድነው በሚል ምክንያት የወላይታ ህዝብ ዛሬ በክልሉ የሚገኘውን የቀድሞውን የደኢህዴን ባንዲራ አውርዶ በማቃጠል የራሱን የወላይታን ባንዲራ ሲሰቅል ውሏል።
•••
ህወሓትና ጃዋር ሲዳማን መገንጠል የፈለጉት ለአንድ ሁነኛ ምክንያት ነበር። ይኸውም ምክንያት ሲዳማ ሲገነጠል ሌሎቹ እንደ ወላይታ ያሉት ጮጋ ካሉ ወደ ሰሜን ፊታቸውን በማዞር ያ እንደ መብረቅ የሚፈሩትን ዐማራ ለ3 በመክፈል አስር ትናንሽ ለማድረግ እንዲያመቻቸው ነበር። ይኸው ሲዳማ ክልል ሆኖ የለም እንዴ? ለቅማንትም፣ ለአገውም ክልል ይሁኑ እንጂ በማለት ዐማራውን ለማዳካም ነበር እቅዱ። ሲዳማ የጦስ ዶሮ መሆኑ ነው። ነገሩ ግን እንዲህ በቀላሉ እንዳሰቡት የሚሠምርላቸው አይመስልም። ገና ወደ ዐማራ ሳይዞሩ ዛሬ ወላይታ እሳት ለብሶ እሳት መለኮስ ጀምሯል።
• አሁን አዋሳ የጦር አውድማ ትሆናለች። እነ ጉራጌና ዐማራ በግልጽ ከርስታቸው ይነቀላሉ። አዋሳን የገነቡአት ብሔር ብሔረሰቦች የይገባኛል ጥያቄ በግልጽ ያነሳሉ። ፌደራል መንግሥቱ ለአዋሳ የሚመልሰው ምላሽ በቀጥታ ለድሬደዋ፣ ለሐረርና ለአዲስ አበባ ግልጽ የሆነ የባለቤትነት ምላሽ ይሰጣቸዋል።
•••
ደቡብ ሲተራመስ ኦሮሚያ እንዴት እንደምትረጋጋ ወደፊት የሚታይ ይሆናል። እነ አብይ ለማ አስቀድመው በረሃብ በመፈናቀል ያዳከሙትን ደቡብ በቀጣይ ምን አይነት መዓት ሊያወርዱበት እንደተዘጋጁ ዋቃ ብቻ ነው የሚያውቀው።
•••
የኢዜማ አመራሮች በአብዛኛው የደቡብ ሰዎች በመሆናቸው ወደፊት ከማን ጎን እንደሚሰለፉ አብረን የምናየው ይሆናል። የጉራጌ ተወላጁ ዶር ብርሃኑ ነጋ ለኦሮሞ መሪዎቹ አቢቹና ለማ ገሌ መሆኑ እስከመቼ እንደሚዘልቅም አብረን የምናየው ይሆናል።
•••
ነፍሱን አይማረውና መለስ ዜናዊ ቀብሮት የሄደው ኢትዮጵያን የመበታተን ፈንጂ አሁን ጊዜውን ጠብቆ የማደጎ ልጁ ዐቢይ አህመድ ቀለበቱን ፈትቶ ሊያፈነዳው ከጫፍ ደርሷል። ድብልቅልቅ ነገር አለ። ድፍርስ የሚል ነገርም ይታያል። በመጨረሻ ግን አደባላቂው ተደብልቆ፣ አደፍራሹ ተወግዶ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና በጠላቶቿ መቃብር ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራዋን ታውለበልባለች።
•••
ግራኝ አህመድ ጠፍቷል፣ ኢትዮጵያ ግን አለች። ዮዲት ጉዲት ጠፍታለች ኢትዮጵያ ግን አለች። ፋሽስት ኢጣልያ ተዋርዳ ተሸንፋ ተመልሳለች። ኢትዮጵያ ግን አለች። መለስ ዜናዊ አፈር ከመቃብር ገብቷል። ምስጥም በልቶታል። ኢትዮጵያ ግን አለች። ኢትዮጵያ ያለ ጡት ነካሽ የኖረችበት ዘመን የለም። አሁንም ነገም፣ ተነገወዲያም ለዘላለሙ ትኖራለች።
•••
ዐማራ የአሳምነው ጽጌ መገደል የሚገባህ ትንሽ ቆይቶ ነው። ትንሽ ቆይቶ አልኩህ። ደህና እደሩልኝ።
•••
ማስታወሻ | ~ የእኔ የዘመዴን የዛሬውን የጀርመን የፌደራል ፖሊስ ውሎ ነገ እተርክላችኋለሁ። ካሳሾቼንና ክሴንም አጥፍላችኋለሁ።
•••
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት።+4915215070996
ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።
@ZemedkunBekeleZ ደግሞ የቴሌግራም ቻናሌ ነው።
በዚህም ይከታተሉ።
•••
ሻሎም !  ሰላም !
ሐምሌ 8/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic