>
6:04 am - Wednesday December 7, 2022

የኦዲፒ ህዝብ ላይ ፍርሃት መልቀቅ እና የስነልቦና ተሸናፊነት እንዲያዳብር የማድረግ አካሄድ!!!  (ሚኪ አምሀራ)

የኦዲፒ ህዝብ ላይ ፍርሃት መልቀቅ እና የስነልቦና ተሸናፊነት እንዲያዳብር የማድረግ አካሄድ!!!

ሚኪ አምሀራ
ስለ ጠ/ምኒስትሩና ፓርቲያቸው
በኦህዴድ ላይ እየሄድንበት ያለዉ አካሃድ አደገኛ ነዉ፡፡ ለኦህዴድ ሁሉ ሰጋጅ፤ ሁሉም ነገር ኦህዴድ ብቻ ባለዉ መንገድ እንደሚሄድ አድርጎ መሳል ይህ ፍርክርክ ድርጅት የሌለዉን ስነልቦና እና ኮንፊደነስ ማጎናጸፍ  መስሎ እየተሰማኝ ነዉ፡፡ በፊት ትህነግን አግዝፈን በመሳላችን ህዝቡን ለፍርሃት ዳርገነዉ ትህነግንም ልቡ እንዲያብጥ እና ተፈሪነቱን በማስፋት አፍኖ እንዲገዛ አድርገነዋል፡፡ ኦህዴድ ኮንስፓየር አያደርግም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ኦህዴድን የምንተችበት መንገድ ልክ እሱን የሚያጀግን እና በራሱ ክልል ዉስጥ እንኳን አጣብቂኝ ዉስጥ በሆነበት ሰአት ሌጅትሜት፤ የተረጋጋ እና ሀገረን በሚገባ ገቨርን እያደረ እንደሆነ አይነት ስነልቦና መገንባት ማቆም አለብን፡፡ ቀስ በቀስ የራሳችን ህዝብ ላይ ፍርሃት እንድንለቅ እና የስነልቦና ተሸናፊነት እንዲያዳብር ማድረግ የለብንም፡፡ በተለየም ከአማራ ክልል ዉጭ ያለዉ አማራ ሳይፈራ እንዳይደራጅ እና መብቱን እንዳይጠይቅ ይሄን ወለጋ እንኳን መሄድ ማይችል፤ በ leadershop crisis የተመታ እና ሀገሪቱንም ቁልቁል ይዞ እየተመዝገዘገ ያለ ቡድን እና የግለሰቦች ጥርቅም ማጀገን እና የሁሉን ነገር አድራጊ ፈጣሪ አድርጎ ማቅረብ ትክክል አይደለም፡፡ ኦህዴድ መመዘን እና መገምገም የሚገባዉ በትክክለኛ አቋሙ ነዉ፡፡ ይሄም ጠ/ሚዉ የራሱን ድርጅት እንኳን አንድ አድርጎ መምራት ተስኖታል፡፡ ኦህዴድ እንደ ድርጅት ብዝሃነትን የማይቀበል በኦሮሚያ ዉስጥ ሌሎች ብሄሮችን ማየት የማይፈልግ፤ አንድን ከተማ ተነስቶ የኔ ነዉ የሚል፤ ግማሹን የኦሮሚያ ክፍል የማያስተዳድር እና በወለጋ ሙሉ ለሙሉ መዋቅሩ የፈረሰ ድርጅት በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ ገደል አፋፍ ላይ እንድትቆም ያደረገ ነዉ፡፡ ይህ ድርጅት በራሱ በኦሮሚያ ክልል ዉስጥ እንኳን አጣብቂኝ ዉስጥ የገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም እዚህ ስትራቴጅክ ባልሆነ ፕሮፖጋንዳ ልናጀግነዉ እና ከገባባት አጣብቂኝ ዉስጥ ልናወጣዉ አይገባም፡፡
ስለ ክልል ፕሬዝዳንት ምርጫው
አቶ የክልሉ ፕሬዝደንት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምርጫዉ ብዙዎቻችን ያላሰብነዉ እንደሆነ ከታየዉ ሪአክሽን መገመት ይቻላል፡፡ ነገር ግን አቶ ተመስገንን ለመመዘን በእኔ በኩል ሁለት ነገር እስከማይ እጠብቃለዉ፡፡ አንደኛ በክልሉ ምክርቤት የሚያደርገዉ ንግግር እና በተለያዩ የአማራ አጀንዳወች ላይ በሚይዘዉ አቋም በተለይም በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያለዉ አተያይ፤ ከተፎካካሪ ድርጅት ለምሳሌ ከአብን ጋር ሊኖረዉ ስለሚችል የስራ ግንኙነት እና የአማራ ህዝብ ነጻነት እና ዲሞክራሲ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ስለሚገኙ አማራዎች መብት እና ጥቅም ይዞት ስለሚመጣዉ ተጨባጭ እና ተግባራዊ ስለሚሆን እቅድ መስማት እፈልጋለዉ፡፡ ሁለተኛ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ዉስጥ የሚወስዳቸዉ የተለያዩ እርምጃወች ከማንኛዉም አካል ነጻ ሁኖ እንደሚዎስዳቸዉ እና ለአማራ ህዝብ በጠቀመ መንገድ እንደሆነ የማየት እና የመገምገም ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ ከአብይ ጋር ስለሚቀራረብ የሚባለዉ ያን ያህል ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ከአብይ ጋር የማይቀራረብ የአዴፓ አባል ቢኖር ምናልባትም የወረዳዎች እና ዞን አካባቢ ያሉት ነዉ ሚሆኑት እነሱም የአብይ ደጋፊ ናቸዉ፡፡ ከዛም በላይ የአማራ ህዝብ እጅግ ብዙ ጉዳይ እየጠበቀ ሁሉንም ነገር ከአብይ ተቀብየ እሰራለዉ ካለ ረዥም እድሜ ስለመይኖረዉ ለስልጣኑ እና ለራሱ ሌጋሲ ሲል የሚያደርገዉ አይመስለኝም፡፡
በመሆኑም ገና ከመምጣቱ ከህዝብ ከምንነጥለዉ ይልቅ የሚከተሉትን አጀንዳወች እንሰጠዋለን እነሱን የሚመልስበት መንገድ አይተን ከዛ በኋላ ግልጽ አቋም መያዝ እንችላለን፡፡
1. የክልሉን የጸጥታ አመራሮች በፍጥነት በመፍታት ወደ ነበሩበት ስራ እንዲመለሱ፡፡ ከእነሱ በላይ በዉስጣቸዉ የሚጠረጠሩ ሰዎችን ጓደኞቻቸዉ ስለሆኑ አላሰሩም፡፡ እኒህ የጸጥታ ሃላፊዎች ግን ደጋፊ ስለሌላቸዉ ታስረዋል፡፡ የመጀመሪያዉ ስራ እነሱን መፍታት፡፡በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የታሰሩ የአብን ደጋፊዎች በፍጥነት እንዲፈቱ እና ይህ አካሄድ መቼም እንደማይደገም ማረጋገጫ መቅረብ አለበት፡፡
2. ህገመንግስቱን በምክር ቤት ዉይይት ተደርጎበት ከሌሎች አካላት ጋር እንዴት ድርድር እንደሚጀመር አቅጣጫ ማስቀመጥ፡፡ የአማራ ህዝብ በተጨባጭ መቀየር አለበት የሚለዉን ነገር ከህዝብ ጋር ዉይይት በማስጀመር ዋና አጀንዳ እንዲሆን ከወዲሁ መስራት፡፡
3. በሌላ ክልል የሚኖሩ አማራዎች ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብታቸዉ የሚከበርበት ግልጽ ፍኖ ካርታ አዘጋጅቶ ለዉይይት ማቅረብ
4. የራያ እና የወልቃይት ጉዳይን በመንግስት ደረጃ በፍጥነት መፍትሄ እንዲሰጠዉ ተግበራዊ እንቅስቃሴ መጀመር
5. አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም ምናምን የሚባል ነገር ተቀባይነት እንደሌለዉ እና እራሷን የቻለች የሀገሪቱ ህዝቦች መኖሪያ መሆኑኗን፡፡ ነገር ግን 2/3ኛዉ የአዲስ አበባ ህዝብ አማራ በመሆኑ የስልጣን ተዋረድ እና ዉክልና ይሄን መሰረት ያደረገ እንዲሆን፡፡
6. በአማራ ክልል ዉስጥ ዶ/ር አምባቸዉ እየዘረጋዉ የነበረዉን ፍጹም ዲሞክራሲ ማለትም የዜጎችን የመናገር፤ የመጻፍ፤ እና የመደራጀት አካሄድ በበለጠ ማስፋፋት፡፡
7. የክልሉን የጸጥታ ሃይል ህዝቡን ከጥቃት ሊታደግ በሚችል አቋም እና ቅርጽ እንዲገነባ ማድረግ፡፡
8. አዲስ አበባ ላይ እና አማራ ክልል ላይ ብቁ የሆኑ፤ የተማሩ እና ህዝቡን በሃቀኝነት ሊያገለግሉ በሚችሉ ሰወች ቢሮክራሲዉን እና የአስፈጻሚ አካላትን ማዋቀር፡፡
9. ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለዉጥ እና ኢኮኖሚያዊ አቢዮት በማካሄድ ህዝቡን ከድህነት ማዉጣት ይሄንም ግልጽ በሆነ የፖሊሲ ማሻሻያ፤ የገንዘብ አቅርቦት፤ የኢንደስትሪ እና ኢንቨስትምንት ማስፋፋትን ትልም በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባት፡፡
10. የአማራን ህዝብ በዉሸት ትርክቶች ሲከሱት የኖሩትን ብሎም አዴፓ ሰሞኑን ህወሃት ጸረ አማራ ድርጅት ነዉ ያለበትን አካሄድ በማጤን ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር የሚኖዉን ግንኙነት የማቋረጥ ወይም ይሄን የዉሸት ትርክታቸዉን በሚገባ የመጋፈጥ ስትራቴጅ መንደፍ እና አሁንም የሚታዩትን ጸረ አማራ እንቅስቃሴ የማክሰም ስራ፡፡
11. በይሉኝታ ያልተሸበበ እና የአማራ ህዝብ አጀንዳ ፊት ለፊት ወጥቶ እንዲሁም ልጆቹ በማንኛዉም ቦታ የመሪነት ሚና እንዲረከቡ ጠንክሮ መስራት፡፡
12. የሀገሪቱ ኢኮኖሚን ምንጭ የሆኑትን እንደ ቴሌ፤ አየር መንገድ፤ ባንክ፤ እና ሌሎች ተቋሞች በሚገባ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚኖርብተን ስትራቴጅ መቅረጽ፡፡
13. ባህርዳር ላይ የተደረገዉን ግድያ በፍጥነት በገለልተኛ እና ሙያዉ ባላቸዉ ቡድን ምርመራ በማድረግ ጥቃቱን ያቀናበረዉን በግልጽ ለይቶ ማዉጣት እና ተገቢዉን ቅጣት መስጠት፡፡
14. በሀገሪቱ የስልጣን እርከን የሚንሰቴር ቁጥርን ሳይሆን የትኛዉ ወሳኝ ስልጣን ነዉ በሚል ለይቶ በማስቀመጥ በእነዛ ቦታዎች ላይ ተገቢዉን ድርሻ በመዉድ ጠንካራ እና የተማሩ ሰወችን ማስቀመጥ፡፡
15. ባጠቀላይ የአማራን ህዝብ ጎጥ ሳይለዩ በአንድነት መንፈስ መምራት ይጠይቃል፡፡
በእነዚህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ በትቂት ቀናቶች ወይም ወራቶች በሚያሳየዉ አቋም ተመስረተን መገምገም ይገባናል፡፡
ከዛ ዉጭ ግን አሁን ካለብን ችግር በተጨማሪ ሌላ negative energy ወደ አማራ ፖለቲካ radiate ማድረግ እራሳችን ከማድቀቅ ዉጭ የሚያመጣዉ ለዉጥ እንደሌለ ይታየኛል፡፡ ከዛ ዉጭ በሌላ ተጽእኖ መስራት እና አለመስራቱን እኮ 1 ወር ሳይቆይ እናየዋለን፡፡ ምንም አያስቸኩለንም፡፡ በስሜት መፏለሉ አይጠቅምም፡፡ በተለይ ደግሞ ዶ/ር አምባቸዉ እንደመጣ እንደዛ ባልተገዛ ስሜት ላይ ታች ስትረግጡ የነበራችሁ ቢያንስ አሁን እስኪ ዝም ብለን እንየዉ ትላላችሁ የሚል ግምት ነበረኝ፡፡ ጉዳያችሁ ግን ሌላ ነዉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ኢኮኖሚስትን፤ የፖሊሲ ሰዉን፤ አካዳሚሽያንን፤ ፖለቲካኛን እና ብሄረተኛን ፕሬዝደንት መተካት ቀላል እንዳልሆነ ያየን ይመስለኛል፡፡
መወቀስ ካለባቸዉ ህዝብ ምሩ ተብለዉ ሲጠየቁ በራሳቸዉ ኮምፎርት ዞን ለመኖር ሲሉ አይ አንፈልግም ያሉ ሰወች ናቸዉ፡፡ እነዚህ ሰወች ለአማራ ህዝብ ያላቸዉ ኮሚትመንትም ጥያቄ ዉስጥ ገብቷል፡፡
Filed in: Amharic