>

ገራፊዬ ተንታኝ ሆኖ አገኘሁት!!!  ኤርሚያስ ቶኩማ

ገራፊዬ ተንታኝ ሆኖ አገኘሁት!!!
 ኤርሚያስ ቶኩማ
 
ከትንተና ይቅርታ ይቅደም!!!
2002 ሰኔ ወር ላይ ነው፤ ተመርቄ እንደወጣሁ መምህር ከመሆኔ በፊት መምህራን በሙሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲ መሰልጠን አለባቸው በሚል በሀገሪቱ እንገኝ የነበርን መምህራን በሙሉ ስልጠናውን መውሰድ ጀምረን ነበር። በወቅቱ ስልጠናውን ይሰጡ ከነበሩት አንዱ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ይሰራ የነበረው አቶ ታዬ ቦጋለ ነበረ።
አቶ ታዬ ስልጠናው ላይ በወቅቱ ይናገር የነበረው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ፍቱን ስርዓት እንደሆነና በዚህ አይዲዮሎጂ መጓዝ ካልቻልን የምንሊክ ልጆች ኢትዮጵያን የራሳቸው በማድረግ የብሄረሰቦቸን ማንነት በመጨፍለቅ በአሃዳዊያን የበላይነት የሚገነባ ኢኮኖሚ እንደሚመሰርቱ ይተነትን ነበር።
በወቅቱ እኔና ጓደኛዬ Degu Chane ደጉ ጫኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ቅዠት እንደሆነ አማራም ባልሰራው በደል ስሙ አላግባብ መነሳት እንዳሌለበትና ትላልቅ ድርጅቶች ወደግል የማይዞሩት የመንግስት ባለስልጣናት ከተቋማቱ ገቢ ላይ በሰፊው ስለሚዘርፉ መሆኑን ስሜታዊ ሆነን ተናገርን።
ከስብሰባው በዃላ ምን ሆነ?
የዛሬው ተንታኝ አቶ ታዬ ቦጋለ ሁለት አማራዎች ስልጠናውን ለመረበሽ እየሞከሩ ነው በማለት የእኔንና የጎጃም ደብረወርቁን ልጅ ደጉ ጫኔን ስልጠናውን አቋርጠን ለሁለት ቀናት ገርጂ ታክሲ ተራ አካባቢ እንድንታሰር ተደርጎ ከየምናስተምርበት የትምህርት ተቋም እንድንለቅ ተደረገ። ሁለት አማራዎች ያለው ብሄራችንን ለይቶ ሳይሆን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚቃወም በሙሉ አማራ ነው ብሎ ስለደመደመ ነበር።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬ አቶ ታዬ ለህዝብ አሳቢ ለታሪክ ተቆርቋሪ ተደርጎ በየመድረኩ ስለሀገር ፍቅር ትንታኔ እየሰጠ ነው። ታዬ ቦጋለን ቦሌ ያስተማረ መምህር በሙሉ ማንነቱን ጠንቅቆ ያውቀዋል። ሰው ይለወጣል፤ እርሱ በግፍ ያሰቃያቸው ግን እኔና ጓደኛዬን ጨምሮ ብዙዎች አሉና ከትንተና ይቅርታን እናስቀድም!!!
Filed in: Amharic