ደኢህዴን ከፍተኛ የሲዳማ እና ሀድያ ባለስልጣናትን አገደ!!! (DW)

ደኢህዴን ከፍተኛ የሲዳማ እና ሀድያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን አገደ!!!
 .DW amharic ሸዋንግዛው ወጋየሁ
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሀድያ ዞን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከኃላፊነት ማገዱን አስታወቀ።
ደኢህዴን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ዞን አመራሮች የታገዱት ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማና እና በሲዳማ ዞን የገጠር አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የራሳቸው ሚና ነበራቸው በሚል ነው። የሃድያ ዞን አመራሮች በዞኑ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ የማገድ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።
ድርጅቱ ከስልጣን አግጃቸዋለሁ ያላቸውን የሲዳማና የሀድያ ዞን ባለስልጣናት ”የፊት አመራሮች ” ከማለት ውጪ ቁጥራቸውንም ሆነ ማንነታቸውን አልጠቀሰም። በደቡብ ክልል በከፋ እና በወላይታ ዞኖች የተስተዋሉት ተመሳሳይ ድርጊቶችም የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ናቸው ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ጠቁሟል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.