ዐማራ ሚዲያ ማዕከል
ዛሬ ወደ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ስንታየው ቸኮልን፣ መርከቡ ሃይሌን፣ ኤልያስ ገብሩንና ጌዴዮን ወንደሠንን ለመጠየቅ የሄዱ ሰዎች እንደገለጹት “ሁሉንም አግኝተናቸው አውርተናል፤ ስለራሳቸው እስር ምንም ሳይመስላቸው እዛ ውስጥ ጨለማ ክፍል የታሠሩ 58 ሠዎች የርሃብ አድማ እደጀመሩና የከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፤ እነሡም እንደሚቀላቀሏቸው ገልጸውልናል” ብለዋል።
የርሃብ አድማ ያደረጉትም መንገድ ላይ እያመጡ የሃሰት ምስክር ስለሚያሰጡባቸው፤ ለረጅም ሠዓታት ምርመራ ስለሚካሄድባቸውና መቋቋም ስላቃታቸው፤ ጉዳያቸው በገለልተኛ ወገን እንዲጣራላቸው ለመጠየቅና ጨለማ ክፍል ቅዝቃዜውን ስላልቻሉትና ከቤተሠብም ጋር ሆነ ከሌላ ጠያቂ ጋር መገናኘት ስላልቻሉ እንደሆነ ገልጸዋል ተብሏል።
ከ58ቱ ውስጥ የአስራት ቴቪ ጋዜጠኛ፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የአብን አባላቶችና የሌላም ፖለቲካ ፓርቲ አባሎቶች እንዳሉ ጨምረው ገልፀውልናል ሲሉ መረጃ አድርሰውናል።
“መንግስት በኛና በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የጀመረውን ንፁሃንን በሠበብ አስባቡ ማሠርና ማሠቃየት የሚያገኘው ትርፍ ካለ ይቀጥልበት፤ ይሄ ግን መቼም አያዛልቀውም፤ በህዝብ ዘንድ ከመጠላትና ውድቀት ከማትረፍ በስተቀር፤ ለማንኛውም እኛ እዚህም ሆነን ትግላችን ይቀጥላል” እንዳሉም ምንጫችን ጠቅሰዋል።