>

ሲአይኤ ስለ መንግስቱ ሃይለማሪያምና አቢዮቱ! (ቅዱስ ማህሉ)

ሲአይኤ ስለ መንግስቱ ሃይለማሪያምና አቢዮቱ!
ቅዱስ ማህሉ
 
የሲአይኤን የ1967ዓ/ም (እኤአ1975)ሪፖርት ስለመንግስቱ ሃይለማሪያም እና ስለ አቢዮቱ ያሰፈረው አብይ አህመድ እና የቄሮ አብዮት እስካሁን የሄደበትን መንገድ በከፊል ያሳያል።  አብይ አህመድ እንደ መንግስቱ የሚቀናቀኑትን ሰዎች እየገደለ እና ካጠገቡ እያጠፋ ነው። አብይ አህመድም እንደያኔው  በትግራይ እና በአማራ ህዝብ መሃል ጦርነት ለመለኮስ በተለያየ አቅጣጫ እየሞከረ ነው።  እስላምና ክርስቲያኑን ለመከፋፈል ያኔ እንደተሞከረው ሁሉ አሁንም በግልጥ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በፖለቲካ ውስጥ በተጠና መንገድ እያስገባ መደስኮሩ ወደዚያ ልዩነት የሚያደርሰን መንገድ ጅማሮ ነው። ሲአይኤ አቢዮቱን የጋላ አቢዮት ይለዋል። ዛሬ የቄሮ አቢዮት ነው ብለውናል። እስኪ ይህን ሪፖርት እያነበቡ ዛሬ እየሆነ ያለውን ይመልከቱበት። በሲአይኤ ጥሁፍ ውስጥ ጋላ እና ጋሎች እንጅ አንድም ቦታ ላይ ኦሮሞ አይልም። እኔ ጋላ እና ጋሎች  የሚለውን ኦሮሞ እያልኩ ጽፌዋለሁ።)
*****
የሲአይኤ የ1967 ሪፖርት ገጽ 8 ላይ የወጣው እንዲህ ይላል። የአጤው ስርዓት መወገድ የኦሮሞዎችን ሁናቴ አሻሽሏል። አብዛኛው የወታደራዊው ቡድን አባላት ኦሮሞዎች ናቸው። መንግስቱ ሃይለማሪያም ራሱ ኦሮሞ ነው። ይህ የፖለቲካ የበላይነት በአይምሯቸው ያለውን የጎሳ ብሄርተኛነት ያጠናክረዋል። በወታደራዊው ቡድን ውስጥ ኦሮሞዎች ከፍተኛ የመንግስት ስልጣኖችን እና የሲቪክ ቦታወች ተቆጣጥረዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ኦሮሞዎች ከመሬት አዋጁ ተጠቅመዋል።
ብዙ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች አቢዮቱን የኦሮሞ አቢዮት እንደሆን ማስተዋል ጀመሩ። ወታደራዊው ቡድን ብዙ የታጠቁ ጨሰኛ ኤርትራን እንዲዋጉ ሲልክ አማራዎች ይህ የኦሮሞን የፖለቲካ ግብ ለማሳካት ካልሆነ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም ይሉ ነበር። ምክንያቱም የታጠቁ አማራዎችን ኤርትራ የሚልከው በዚያ የሚገኙ ብዙ ትግሬ አማጺያንን በማጥቃት የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ለማዋጋት እንደሆን ይረዱ ስለነበር ነው። በእላሞች እና በክርስቲያኖች መሃከልም ልዩነት ለመፍጠር ይሞከር ነበር። ምክንያቱም የአማራው ታጣቂ አብዛኛው ክርስቲያን ሲሆን የኤርትራ አማጺያን ደግሞ አብዛኞቹ እስላሞች ነበሩና ነው። ይህንም ዘመቻ ለማገዝ በሚዲያ በሚደግፏቸው አረቦች ላይ እና በአማጺያኑ ላይ ጸረ እስልምና ዘመቻ ይደረግ ነበር። ይህን በክርስቲያኑ ስነልቦና ላይ በሚያሳድረው ተጽእኖ ምክንያት ወታደሩ እንደ እፎይታ ጊዜ ይቆጥረዋል። አማራ እና ኦሮሞ(ጋላ) በምንም ዓይነት የፖለቲካ ፕሮግራም እና አይዲዮሎጅ አንድ ሆነው አያውቁም። ኦሮሞዎች በራሳቸው በተለያየ ጎሳ ተከፋፍለው በተለያየ ቦታ ተሰራጭተው የሚኖሩ ናቸው።  በደቡብ ያሉት ኦሮሞዎች ማዕከላዊ መንግስቱ ላይ በሚያደርጉት አመጽ በሶማሊያ ይደገፋሉ።
Filed in: Amharic