>

"ሲዳማም ሆነ ወላይታ ከአማራ ጎን መቆም እና መደራጀት  አለባቸው!!!"  (አቶ መኮንን ዶያሞ)

“ሲዳማም ሆነ ወላይታ ከአማራ ጎን መቆም እና መደራጀት  አለባቸው!!!” 
አቶ መኮንን ዶያሞ – (ከአስራት ቲቪ ጋር  ካደረጉት ቃለመጠይቅ)
 “ዶ/ር አብይ ከመጣ መከራ፣ መፈናቀል እና ሞት ነው የመጣው። ያገኘውን ስልጣን ለዲሞክራሲ ሽግግር በማረግ ፋንታ ዞር ብሎ ወደ ጎሳው ሄዶ የኦሮሞ የበላይነትን ለማንገስ እየሞከረ ነው። ኦነግን አዲስ አበባ ጋብዞ ህዝቡን አሳረደ። ባንክ አዘረፈ።  ዶ/ር አብይ መንግስት ምን እንደሆን እንኳ የሚዋቅ አይመስለኝም። በ17ኛው ክ/ዘመን የቀረ ሞዴል ይዞ እኔ አሻግራችኃለሁ ይላል። እሱ ሊያሻግረን አይችልም።
•••ኢጄቶ የኦሮሞ ፅንፈኛ ሀይሎች እጅ ነው። ኢጄቶ ቃሉም ኦሮምኛ እንጅ ሲዳምኛ አይደለም። የሲዳማ ህዝብ ክልል መሆን ከፈለገ የማንንም እርዳታ አይፈልግም። ራሱን ችሎ መሆን ይችላል። ኦሮሚያ የምትባል ሀገር እፈጥራለሁ የሚለው በጅዋር የሚመራው የኦነግ ክንፍ ነው እየበጠበጠ ያለው። ነጮቹ በየትኛውም መንገድ ኦሮሚያ የሚባል ሃገር ለመፍጠር መሞከር ፈጽሞ የማይቻል እና የሞኞች ቅዠትነው ይላሉ።ግን የሚሆን መስሏቸው በውጭ ካሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ገንዘብ እየተቀበሉ እየሰሩ ነው። ኦነግ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሳሪያ ነው።
 ይርጋ ጨፌን እኮ ጨፌ ኦሮሚያ ብለው የምኞት ካርታቸው ላይ አካተዋል። ጉራጌን በገንዘብ እየደለሉ ነው። በመሐል ላይ ወላይታ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። ማወቅ ያለባቸው ግን ሲዳማን ኦሮሞ እንደፈለገ የሚጠመዝዘው ህዝብ አለመሆኑን ነው። እንዲያውም በትክክል ቢሰራ ኦሮሚያ እንኳን ሃገር ክልልም መሆን አልነበረባትም። ምክንያቱም ኦሮሞ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ማይኖሪቲ ነው። ነቀምት ብትሄድ፣ናዝሬት ብትሄድ፣ወሎ ብትሄድ፣ ሸዋ እና አሩሲ ብትሄድ ኦሮሞ የትም ቦታ ማይኖሪቲ ነው። ከአማራ ክልል ውጭ የሚኖረው አማራ ብቻውን በቁጥር ከኦሮሞ ይበልጣል።
ኢትዮጵያን ለማዳን አማራን ማዳን አለብን። አማራ ሀገሩን ከጠላት ተከላክሎ የኖረ ህዝብ ነው። መፍትሄው ለአዲስ ህገ መንግስት ሪፈረንደም ማካሄድ ነው። የአማራው መደራጀት ለኛ ትልቅ ተስፋ ነው። አማራ ተመታ ማለት የኢትዮጵያ አከርካሪ ተመታ ማለት ነው። አማራ ከተመታ ሌሎቻችን ብዙ አቅም አይኖረንም።ስለዚህ ሌላውም ከአማራው ጋር መደራጀት ይኖርበታል። አማራ ቤተሰባችን ነው። ትህትና ያስተማረን እና በኢትዮጵያ ሁሉ ከተማ የገነባ ህዝብ ነው።•••”

 

 

Filed in: Amharic