>

 "ፍ/ቤት ነፃ ቢላቸውም ዛሬም በእስር ላይ ያሉት 53 የልዩ ኃይል አባላት ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው!!! (ቅዱስ መሀሉ)

 “ፍ/ቤት ነፃ ቢላቸውም ዛሬም በእስር ላይ ያሉት 53 የልዩ ኃይል አባላት ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው!!!
ቅዱስ መሀሉ
 
ትግራይ ላይ መንግስት ጦር እንዲያዘምት ሃሳብ የሰጡት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለአማራ ክልልስ ምን አስበው ይሆን? 
ከ12 ቀናት በፊት የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው 53 የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እስካሁን ከቤተሰቦቻቸው አለመገናኘታቸው ታውቋል። የፖሊስ አባላቱ የፍርድ ቤት ውሳኔውን ተከትሎ ከእስር ከመፈታት ይልቅ ባህር ዳር አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ታፍነው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ከቦታው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው 53 የልዩ ኃይል አባላቱ ቅያሬ ልብስ እና ህክምና እንዳያገኙና “በህግ ያልታወቀ ቦታ” እንዲቀመጡ መደረጋቸው ተገልፆል። የልዩ ኃይል አባላቱ “ፍ/ቤት ነፃ ያለን ሰዎች ሆነን ሳለ ያለአግባብ ታፍነን የተያዝንበት ሁኔታ ለደህንነታችን አስጊ ስለሆነ ህዝብ እና ህጋዊ አካል ይህን ይወቅልን” ብለዋል።
እናም ትግራይ ላይ መንግስት ጦር እንዲያዘምት ሃሳብ የሰጡት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለአማራ ክልልስ ምን አስበው ይሆን? ላንድ የፍትህ ተቋም ህግ ማስከበር መቼም በብሄር የተለያየ መስፈርት ሊኖረው አይችልም። በኦሮሞ ክልል ሰው ዘቅዝቀው ሰቅለው ሲቃጠል ቆመው ሲሳለቁ የነበሩት ፖሊሶች እና ወታደሮች ዛሬ አማራውን እያሳደዱ ነው። በሲዳማ ንጹሃንን ያሳረዱት የቄሮ መሪዎች አጠገብሽ ሆነው ምን አደረገሽ? አፍንጫሽ ስር ካሉት ወንጀለኞች ጀምሪ፤ፍትህ ክልል እና ድንበር አያቆመውም።
Filed in: Amharic