>
5:18 pm - Wednesday June 16, 6247

የደቡብ አፍሪካው ኤምባሲ የሚያስመሰግን ተግባር እየፈጸመ ነው!!! (ህብር ራድዮ)

የደቡብ አፍሪካው ኤምባሲ የሚያስመሰግን ተግባር እየፈጸመ ነው!!!
ህብር ራድዮ
በደቡብ አፍሪካ ዜጎቻችን ከዕለት ዕለት ዘራፊዎች እስከ ተደራጁ የመንግስት እርምጃዎች የጥቃት ሰለባ ይሆናሉ።ሰሞኑን ፖሊስ በከፈተው ዘመቻ በርካታ ዜጎቻችን ለእስር ተዳርገዋል፣የንብረት ዘረፋ ደርሶባቸዋል ።ከዘራፊዎች መካከል ጥቂት ፖሊሶች ጭምር ተገኝተው በራሱ በፖሊስ ተቁዋሙ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በስፍራው ያለው ኤምባሲ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ሰምተናል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) በጆሃንስበርግ ሴንትራል ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው በውጭ አገር ስደተኞች ውብ የጸጥታ አስከባሪዎች መካከል ሰሞኑን በተፈጠረ አሰሳ እና ተከትሎ በመጣ ግጭት በጣቢያው ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከኢትዮጵያውያኑ የማህበረሰብ ወኪሎች እና የአፍሪካውያን ስደተኞች ፎረም አመራር አባላት ጋር በመሆን ከአገሪቱ የአገርብውስጥ ጉዳይ ባለሥልጣናት እና የፖሊስ ሀላፊዎች ጋር ተነጋግረዋል።ንግግሩ እስረኞች በቆይታቸው መብታቸው የሚጠበቅበት እና ከእስር ቤት ቶሎ የሚፈቱበት ሁኔታ ተነጋግረዋል።
 በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ አፍሪካ መንግስት የስራ ኃላፊዎች በእስር ላይ የሚገኙትን ዜጎች እስከ ዛሬ ማምሻውን ድረስ አጠቃለው እንደሚለቁ ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሩ ከኃላፊዎቹ ጋር ያደረጉትን ውይይት ካጠናቀቁ በኋላ ከፖሊስ ጣቢያው ውጪ ሲጠብናቸው  ለነበሩ የታሳሪ ቤተሰቦች እና ጉዋደኞች  ውይይቱን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ ደስ የተሰኙት እና ተስፋ ያደረጉ የታሳሪዎቹ ጉዳይ የሚመለከታቸው በሙሉ ኤምባሲው እና አምባሳደሩን አመስግነው ክትትሉ እንዳይቁዋረጥ ጠይቀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ከህወሓት በተለየ በውጭ የሚገኙ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያውያን ሁሉ ወኪል እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ይህ መሰሉ ተግባር ያስመሰግናል።ይህን የምንለው ከነበርንበት ሁኔታ ተነስተን እንጂ የአንድ አገር ኤምባሲ እና ቆንስላ ከአምይ ሥራዎቹ አንደኛው ተግባር ይህ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር በቅርቡ የጀመረው የእስር እርምጃና የእስረኛ አያያዝ ላይ ቤተሰቦች እንዳይጠይቁ፣በጨለማ ቤት የታሰሩ ጭምር መኖራቸውን ሊያምን ባይፋልግም እውነት ነው።ይህን የማያዋጣ የአፈና ድርጊትም እንዲያቆም ሳናጣራ አናስርም ያለውን ቃል ጭምር እንዲጠብቅ እግረ መንገዳችንን እንጠይቃለን
ተከታዩ ፎቶ አምባሳደሩ ከደቡብ አፍሪካ የሚመለከታቸው ባለ ሥልጣናት ጋር ተነጋግረው ሲወጡ ለሚጠብቁዋቸው ወገኖቻችን ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
Filed in: Amharic