>
7:39 am - Wednesday December 7, 2022

የግብጽ እና የኦሮሚያ ፍቅር!! (ዘመድኩን በቀለ)

የግብጽ እና የኦሮሚያ ፍቅር!!
ዘመድኩን በቀለ
ስለሁለት ፍቅረኛሞች ግብጽ እና ኦሮሚያ በመጠኑ ስንወያይ እንውላለን። የፈርኦኗ ግብጽ የ3 ሺ ዘመኗንና የዕድሜ ባለፀጋዋን ሀገር ኢትዮጵያን ማፍቀር የጀመሩት ገና ጥንት ነበር። ጥንት በሙሴ ዘመን ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ እንኳ ለሚስትነት የመረጠው ኢትዮጵያዊቷን ነበር። ግብጽ ተቀምጦ አይሁዳዊትም ግብጻዊትም አላማሩትም። ቀልቡንም አልገዙትም። ከምር ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶችም ሆኑ ራሷ ኢትዮጵያ እኮ ሲጀመር በተፈጥሮ ራሱ ውቦች ናቸው። ያለ ሜካፕም ተመራጭ ናቸው። አሁን አሁን ዱቄት ውስጥ የገባች አይጥ የመሰሉ ሴቶች የቻይናን ፌር እየተለሰኑ መሳቂያ መሳለቂያ አድርገው አሳቀቁን እንጂ የእኛ ሴቶች ያለ ቅባት ራሱ እኮ ውብ ናቸው። በተለይ ውብ ሴቶች በሠርጋቸው ቀን ለምን አይጥ መስለው መታየት እንደሚፈልጉ እስከአሁን አልተገለጸልኝም። ሰው እንዴት በሰርጉ ቀን ጭራቅ መስሎ ታዳሚውን ሲያስፈራራ ይውላል? ሆሆይ ጉድ እኮ ነው።  በዚህ ጉዳይ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። አሁን የግብጽ በኢትዮጵያ የዐይን ፍቅር መውደቅን እንመልከት።
•••
ግብጽ መጀመሪያ እናት ኢትዮጵያችንን ነበር ለማግባት ፍላጎት የነበራት። ለውቅያኖስና ለባህር ቅርብ መሆኗ፣ ለእስራኤልም ቅርብ መሆኗ፣ ወደ አረቢያ ምድር መሻገሪያ ድልድይ መሆኗ ካልሆነ በቀር እዚህ ግባ የማይባል ሀብት ያላት ግብጽ ሀብታሟን ኢትዮጵያን አግብታ ሀብታም ሆኗ መኖር አማራት፣ ግብጽ የምትጠጣው ውኃ እንኳ አይደለም በቤቷ በሰፈሯ በሀገሯ የላትም። ውኃውንም የምትልክላት ይኽቺው ባለፀጋዋ ኢትዮጵያ ናት። ውኃ ብቻ አይደለም አፈር ሳይቀር ለአባይ አስቋጥራ የምትልክላት ኢትዮጵያ ናት።
•••
መጀመሪያ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኩል የሠለስቱ ምዕትን ቃል አጣማ፤ ፍትሃ ነገሥቱን ሰርዛ ደልዛ ለ1600 ዓመት ያህል በእጅ አዙር እንደ ቅኝ ግዛት ዓይነት አስመስላ ልትገዛን ሞከረች። ምስጋና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሊቃውንት ይግባቸውና በመንፈስ አጋዥነት እየረቀቁ፣ እየተመራመሩ፣ ግብጻውያኑ ከቡራኬ ባላለፈ ምንም ማድረግ እንዳይችሉ አድርገው፣ አንዳንዴም አስረው እየመለሱ፣ በመጨረሻ በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተገላገልናቸው።
•••
ግብጽ እናት ኢትዮጵያን ጠቅልላ ማግባት ሲያቅታት ልጆቿን እየጀነጀነች ከእናታቸው ነጥላ ለማግባት በማስኮብለል ለማግባትም ሞክራለች። በዚህ በኩል መጨረሻ ላይ ጋብቻቸው ይስመር አይስመር ባይታወቅም አንዱ ሲሳካላት፣ አንዱ ከሽፎ፣ አንዱ ግን በመንገድ ላይ ነው። መጀመሪያ ሐረር የተባለች ቆንጂዬ የኢትዮጵያን ልጅ ለማግባት እዚያው ሐረር ድረስ ሄዳ ገሌ ሆና ነበር። በመቀጠል ኤርትራ የተባለች በሰሜን የምትገኝን ኢትዮጵያ እንደ አንገት ጌጥ የምትኮራባትን ልጇን ቦንብና ክላሽ ሁሉ አስታጥቃ ከእናቷ አቆራርጣ ከቤት አስወጣቻት። አሁን ፍቅራቸው በምን ዐይነት ሁኔታ እንዳለ ግን አይታወቅም። በመጨረሻም በከፍተኛ ኢንቨስትመንት አሁን ደግሞ ኦሮሚያ ከምትባል የኢትዮጵያ ልጅ ጋር እፍ ያለ ፍቅር ላይ ወድቃ፣ ልጂት ኦሮሚያንም ቀልቧን አስታ እፍ ያለ ፍቅር ላይ ወድቀው ይታያሉ።
•••
ዘማዊዋ ግብፅ ኦሮሚያ ቢቻል እናቷ ኢትዮጵያን ጠቅልላ ብትውጥላት ደስተኛ ናት። እናም ለዚያ ሲባል ሁሉም ኬኛ የሚል ፕሮጀክት ለኦሮሚያ ቀርጻላት ሁለቱም በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። አክሱም ራሱ ኬኛ አካሱማ ነበር ስሙ ይሉልሃል። ከጣልያን ሲሲሊ ቱርክና ህንድም ይሻገራል የኬኛ ፕሮጀክት።
•••
ግብጽ ለአዲሷ ፍቀረኛዋ ለኢትዮጵያ ልጅ ለኦሮሚያ ከፍተኛ ማማለያም፣ መደለያም ገጸ በረከት እያቀረበችላት ልቧን ቀጥ አድርጋ ሰቅዛ ይዛታለች። ኦሮሚያም ልክ እንደ ኤርትሪያ ከእናቴ ጓዳ ከእምዬ እቅፍ ልውጣ፣ ልውጣም እያሰኛት ነው።
•••
ግብጽ ለአዲሲቷ ኦሮሚያ የራሷን ባንዲራ ቀለሙን እንኳ ከነ አቀማመጡ ሳይቀር ምንም ሳትቀይር ሰጥታለች። ቀለሙም፣ ቅርጹም አንድ ዓይነት የሆነ ባንዲራ ነው የሰጠቻት። ባንዲራው ልዩነቱ በባንዲራው ላይ ያለው ምልክት ብቻ ነው። የግብጹ መሃሉ ላይ ንስር አሞራ ሲኖረው የኦሮሚያው ግን የኦዳ ዛፍ፣ የዋርካ ዛፍ ነው። ዛፍ ደግሞ የንስር አሞራ ማረፊያ ነው። አሞራዋ ግብጽ ኦሮሚያን እንደዛፍ ልትዘፈዘፍባት፣ ቤት ጎጆዋንም ልትቀልስባት፣ ልትሰፍርባት የፈለገች ይመስላል። በግብጽ ግብጻውያን የኢትዮጵያን ባንዲራ ሳይሆን የኦሮሚያን ባንዲራ የያዘ ያከብራሉ። ይወዳሉም። በዲሱ የኦሮሚያ ወሃቢያ እስላም ዘንድ የኢትዮጵያ ስሟም፣ ባንዲራዋም ጽዩፍ ነው።
•••
ግብጽ ለባንዲራዋ ከነ ንሥሩ ትርጉም ሰጥታ በይፋ ለዓለም ህዝብ አሳውቃለች። ለኦሮሚያ ለሰጠችው ባንዲራን ግን ምንም ዓይነት ትርጉም አልሰጠችም። እስከአሁን ቀለሙ ብቻ ነው በጨርቅ ተሰፍቶ ለኦሮሞው ወገኔ ተሰጥቶት የሚለብሰው። ባንዲራው ከግብጽ እንደመጣለት እንኳ አብዛኛው የኦሮሞ ወገኔ አያውቅም።
•••
ድሮ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኩል ገብታ ኢትዮጵያን ቅኝ መግዛት ያልተሳካላት ግብጽ አሁን በኦሮሞ እስላም በኩል ገብታ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከጫፍ የደረሰችም አስመስሏታል። የኦሮሞና የግብጽ ፍቅር በአቢይ አህመድና በአልሲሲ ወላሂ፣ ወላሂ አልክድህም መሃላ የጸናና የተጋመደ ነው። አሁን ኦሮሞ በሀገረ ግብጽ የንጉሥ ያህል ነው ይባላል። ዝርዝሩን ለብቻው እመለስበታለሁ።
•••
ከዚህ እንደመግቢያ ጦማር በኋላ ሟቹን የሙስሊም ብራዘር  መሪ የነበረውን የሟቹን ዶክተር ፎቶ ለጥፈው የሚያለቃቅሱ የኦሮሞ ሙስሊሞችን እንደ አሸን ሲርመሰመሱ ልታዩ ትችላላችሁና እንብዛም አትደነቁ። ልዩ ምልክታቸውም የሚያቅለሸልሽ ስድብ መለጠፍ ነው። እነሱ የግብጽ ቅጥረኛ የወሃቢያ እስላም ናቸው። መልስም አትስጧቸው።
• እኔ ግን ወደ በኋላ በሀገረ ግብጽ የኢትዮጵያንና የኦሮሚያን ዜጎች ፍጥጫ ይዤላችሁ እመለሳለሁ። እስከዚያው በቸር ያቆየን።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ነሐሴ 5/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic