>

ወሎ የማን ናት? (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

ወሎ የማን ናት?

ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

 

ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳ ወሎ ኦሮሞ ነው ሲል፥ ታሪክ ላይ ተደግፈን ስለ ወሎ ባለቤትነት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከመሞከር በፊት የጥያቄው ጤንነት ይታሰብበት።

 

ጭር ሲል አልወድም ሆነና ነገሩ፥
ጫጫታው ይድራልኝ አለ በመንደሩ።

ያለ አዕምሮ ጠብ ጫሪ፥ “ወሎ ኬኛ”
ባለ አዕምሮ አቃፊ፥ “ኢትዮጵያ ሀገሬ ነው። ወሎ ወገኔ ነው”

ትላንት አዲስ አበባ
ዛሬ ወሎ
ነገ ደንቢ ዶሎ
ሰው መሆን ቀሎ

ሕፃን፥ ሁሉም የእኔ ነው ብሎ ያላዝናል።
ጎልማሳ፥ እንዴት በአብሮነት እንኑር ብሎ ይመክራል።
ሽማግሌ፥ ለተተኪው ትውልድ ሰላም እንዲበዛ ይተጋል።

ጣና ኬኛ
ወለጋ የኛ
ኬኛ የኛ
የኛ ኬኛ
ኢትዮጵያኛ

ኢሜል፥ Z@myEthiopia.com

Filed in: Amharic